እስኪ እነዚህን ጥያቄዎች እንመልስ። ከ 5ኛው እንጀምራለን።
5፣ ፀሐይ እና ጨረቃ ከኛ ቢርቁም እንኳ ልናያቸው ይገባ ነበር፣ በምሽትም ቢሆን ይላል።
መልሱ የሚሆነው ጨረቃ እና ፀሐይ ከምድር አንጻር ትንሽ ናቸው። ስለዚህ ሲርቁን በጣም ትንሽ ይሆናሉ ከእይታም ይሰወራሉ። ስለዚህ ልናያቸው የማንችለው ለዚህ ነው ከፍላት ኧርዝ አንጻር።
4፣ ጸሐይ እና ጨረቃ ክብ ሆነው ምድር ዝርግ እንዴት ሆነች።
በመጀመሪያ ክብ የሚለውን ቃል በደምብ እናጥራው። ክብ የሆኑ ነገሮችም ዝርግ ወይም ጠፍጣፋ መሆን ይችላሉ። (እዚህ ጋር ዝርግ እና ጠፍጣፋንም እንለይ፣ ምድር ዝርግ እንጂ ጠፍጣፋ ናት አንልም።) ለምሳሌ ሰሃን ጠፍጣፋ ነው። ነገር ግን ክብ ነው። ሲዲ ወይም ቪሲዲ ዲስክ ጠፍጣፋ ነው። ግን ክብ ነው። ምድርም ላይዋ ዝርግ ይሁን እንጂ (ጠፍጣፋ አላልንም)፣ ክብም ነች። ይህንንም ኢሳያስ "የምድር ከበብ ላይ ይቀመጣል" ብሎ የገለጸበት አለ።
ሌላው ወሳኝ ነጥብ ደግሞ፣ ጸሐይ እና ጨረቃ ክብም ሆኑ፣ ድቡልቡልም ሆኑ ከምድር ቅርጽ ጋር አያገናኘውም። ለምሳሌ የፑል መጫወቻ ጠረጴዛ ላይ የፑሎቹ ኳሶች ድቡልቡል ናቸው። ነገር ግን ያ ማለት ጠረጴዛው ድቡልቡል ነው ማለት አይደለም፣ የሁለቱ ቅርጽ የተለያየ እና አንዱ አንዱን የማይወስን በመሆኑ። ሰዎች ይህን ጥያቄ የሚጠይቁበት ምክንያት፣ በተለምዶ ስለ ህዋ ከምንማረው ነገር ጋር አያይዘው ነው። በትምርት እና በሚዲያ የሚነገረን የዓለም አፈጣጠር ድቡልቡል ጨረቃ ዱቡልቡል ምድር ላይ ትዞራለች፣ ድቡልቡሏ ምድርም ደግሞ ድቡልቡል ፀሐይ ላይ ትዞራለች የሚለው ነው። እናም ሰዎች "አይ፣ ምድር ድቡልቡል ወይም ኳስ ቅርጽ አይደለችም፣ ዝርግ ነች" ሲባሉ፣ ያንኑ ድሮ የሚያውቁትን ስርአት ይጠቀሙና፣ "ስለዚህ ዝርግ ወይም ጠፍጣፋ ምድር (ለነሱ ልዩነቱ ግልጽ አይደለም) ድቡልቡሏ ፀሐይ ላይ ትዞራለች" ብለው ያስባሉ። ስለዚህ በነሱ እየታ፣ ጸሐይ እና ጨረቃ ድቡልቡል ከሆኑ ምርድም ድቡልቡል መሆን አለባት ማለት ነው።
ነገር ግን እውነታው ጸሐይ እና ጨረቃ ራሳቸው ምድርን የሚዞሩ መሆናቸው ነው። ምድር ድቡልቡል ኳስ አይደለችም ስንል በጸሐይ ላይም አትዞርም ማለታችን ነው። ይልቁንስ ጸሀይም ጨረቃም ምድርን ይዞራሉ፣ ምድር የዓለም ወይም የዩኒቨርስ ማዕከል ናት ማለታችን ነው።