እስቲ ትንሽ ስለ አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ እናውጋ።
አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ምንድን ነው ዓላማው? ብዙ ሰዎች እንደ ሰው የሚያስብ አልፎም ከሰው የማሰብ አቅም በላይ ያለው ማሽን ለመፍጠር ነው ይላሉ። ግን አስተውሎ ላሰበ ሰው ይህንን የሚፈጥሩበት በቂ ምክንያት የለም። ግን በሳይንስ ፊክሽን ላደገ ትውልድ ትልቅ ግኝት ወይም የስልጣኔ ጥግ መስሎ ሊታይ ይችላል። ነገር ግን አሁን ያሉ ትላልቅ ይህንን የሚሰሩ ድርጅቶች የሰውን የማሰብ ችሎታ በከፊሉ ለመስራት እንኳ በቢሊዮን እና ትሪሊዮን የሚቆጠር ፈንድ ሲጠይቁ ይታያል። ቃል የገቡትን ውጤት በተግባር ሲያሳዩ ግን አይታይም። ይህ ለምን ይሆን? ብለን መጠየቅ አለብን።
በመሰረቱ አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ እንዴት ነው የሚሰራው? ብለን ስንጠይቅ የምናገኘው፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዳታ ሰብስበው "ሞዴል" የሚባለውን ያሰለጥኑታል። ከዚያ ሌላ ዳታ አምጥተው ደግሞ ሞዴሉ በትክክል ይገልጸዋል ወይ ማለትም ምንነቱን በትክክል ለይቶ ያውቃል ወይ የሚለውን ቼክ ያደርጋሉ። ታዲያ መጀመሪያ የሚገባለት ዳታ በበዛ ቁጥር የሞዴሉ ጥንካሬም በዚያው ልክ ይጨምራል። ለዚህ ነው ቻት ጂ ፒ ቲ ጠንካራ የሆነው። መላው ኢንተርኔት ላይ ያለውን፣ እያንዳንዱ ሰው ዌብሳይት ላይ የጻፈውን እና የተናገረውን ሁሉ ሰብስበው በዛ ዳታ ላይ ስላሰለጠኑት ነው አሁን ላይ የሚገርም ብቃት ያየንበት። ከቴክኒካል ነገሮች እስከ ፈተና መልስ፣ እስከ የህይወት ምክር ድረስ ሲሰጥ የታየው ቀድሞውኑ ለነዚህ ነገሮች ሌሎች ሰዎች በኢንተርኔት ላይ ያሰፈሩትን አምጥቶ ስለሚያሳይ ነው። ከኮምፒውተር የሚለየው ደሞ ከዚያ ከባህር የሰፋ መረጃ ውስጥ ለይቶ ሰዎች በጠየቁት ልክ መመለስ መቻሉ ነው።
ይህንን ስናስብ ነው አርቴፍሻል ኢንተልጀንስ ምናልባትም ለምን እንደተፈለገ የሚገባን። አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ሚሊዮን እና ቢሊዮን ሰዎች ካስቀመጡት ዳታ ውስት አንድ ልዩ ጥያቄ ሲጠየቅ ለዛ መልስ የሚሆውን ከዚያ እንደ ባህር ከሰፋው ዳታው ውስጥ አውጥቶ መመለስ መቻሉ ነው። ልክ አንድ ሰው በአመታት እድሜው ካወቀው እና ከተማርው ውስጥ ሰዎች የጠየቁትን መርጦና ለይቶ እንደሚናገር ማለት ነው። ታዲያ ኮምፒውተሮች ይህ ችሎታ ሲቸራቸው እጅግ አደገኛ ያደርጋቸዋል። እንዴት?
ብዙ ሰዎች አሁን ላይ መረጃቸውን ኢንተርኔት ላይ አስቀምጠዋል። በክፉም በደጉም ብጽሁፍም በቪዲዮም በድምጻቸውም ጭምር አስቀምጠዋል። አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ደግሞ ይህንን ሁሉ አበጥሮ ዘርዝሮ ማስቀመጥ ይችላል። ስለዚህ ያንን የሚቆጣጠሩ ሰዎች አበበ የሚባል ሰው በጥር 2015 ምን ተናገረ ብለው ቢጠይቁት፣ "መንግስትን የሚተች ነገር ተናገረ" ወይም "ስለ ኮንስፓይረሲ ቲዮሪ እንዲህ እንዲህ ብሎ ጻፈ" ብሎ ሊመልስላቸው ይችላል። ከዚያም፣ ይህ አበበ ምን አይነት ሰው ነው? ባህሪው እንዴት ነው? ብለው ቢጠይቁት፣ "ከሚናገራቸው ነገሮች እና ከሚጽፋቸው ጽሁፎች ተነስቼ ሳይ፣ አበበ ወጣት ወንድ ነው፣ እገር ኳስ ይወዳል፣ ከሙዚቃ ይህ እና ይህ የሙዚቃ አይነት ይመቸዋል፣ የፖለቲካ እይታዎቹ እንዲህ እና እንዲህ ናቸው" ወዘተ ብሎ ሊዘረዝር ይችላል።
ይህን ከማድረግ ምን ይከለክለዋል? ምንም? ብዙ የቻት ጂፒቲ ተጠቃሚዎች ጂፒቲ እስከ ዛሬ ከሱ ጋር ካወሩት ንግግሮች ተነስቶ ስለነሱ ህይወት አብጠርጥሮ እንደሚናገር ያውቃሉ፣ ይህ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ታዲያ መንግስታት ይህንን አይነት ቴክኖሎጂ አይጠቀሙም ብሎ ማሰብ የዋህነት አይሆንም? እነ ቻይና ገና ድሮ ይህንን እንደጀመሩ ይታወቃል። ቻይና ራሷን አልፋ መላውን አለም በዚህ አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ እንደምትሰልል ይታወቃል። የዚህ ምርጥ ምሳሌ ቲክቶክ ነው። ቲክቶክ ምን እንደምንወድ ምን እንድምንጠላ በደምብ አብጠርጥሮ ያውቃል። እነ ፌስቡክ ጉግል እና ትዊተርም እንዲሁ።
አሁን ላይ ደግሞ ሌላ አደገኛ ነገር እየተፈጠረ ነው። ትላልቅ የቴክኖሎጂ ካምፓኒዎች ከመንግስታት ጋር ሆነው ህዝብን መግዛት እና የፖለቲካ ተጽዕኖ ለማሳደር መስራት ከጀመሩ ቢሰነባብቱም አሁን ላይ ግን ግልጽ እየሆነ መጥቷል። "ኦሊጋርኪ" የሚባለው የመንግስት አስተዳደር፣ ፈላስፋው ፕላቶ እንደሚነግረን ጠቂት ሰዎች ያሉበት ስብስብ ሃገርን ሲመራ ነው። አሁን ላይ በተለይ አሜሪካ ወደዛ እየሄደች ነው። እነ ኢሎን ማስክ በግልጽ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎቻቸውን ይዘው ወደ ፖለቲካው ገብተዋል። ይህም የአውሬው ሰራተኞች በቴክኖሎጂ ተጠቅመው ዓለምን የመግዛት ህልማቸውን ወይም ቴክኖክራሲ የሚባለውን እያሳኩበት ያለበት መንገድ ነው።
በዚህም እንደ አርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ባሉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎች የዜጎችን እያንዳንዷን እንቅስቃሴ መቆጣጠር፣ መሰለል እና መመዝገብ ላይ ነው። አሁን ላይ ብዙ አይነት አፕሊኬሽኖች አሉ። አንድ ሰው በቀን ስንት ሰአት ተኛ፣ መች ተኝቶ መች ተነሳ፣ በቀን ስንት እርምጃ ተራመደ፣ የት ደርሶ ተመለሰ፣ ሴቶች መች ምች የወር አበባቸውን አዩ ይህንን ሁሉ የሚከታተሉ አፕሊኬሽኖች መጥተዋል። ሰዎችም በገዛ ፈቃዳቸው እንዲህ አይነት የግል መረጃቸውን እንዲሰብስብ አሳልፈው ይሰጣሉ። ታድያ ነገ ላይ ስራአቱ ሲቋቋም ማን እነሱን ይቃወማል? ምን እንደበላህ ምን እንደጠጣህ፣ ምን እንደምትወድ ምን እንደምትጠላ በምን ፍጥነት እንደምትሮጥ ሁሉ ያውቃሉ። የት ታመልጣለህ እንዴትስ ብለህ ታመልጣለህ? እድል የለህማ። ነጻነትህን ቀድመህ አሳልፈህ ሰጥተሃላ!!