እንኳን ለአድዋ የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! አባቶቻችን ትልቅ ዋጋ ከፍለው ነፃ ሀገር ለኛ ያስረከቡበት፣ በየትኛውም ዓለም ፊት ወተን ደረታችንን ነፍተን የምናወራበትን ክብር የሰጡን ቀን ነው። በእምነት በጸሎት በቅዳሴ፣ እግዚአብሔርን ይዘው፣ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተገን አድርገው፤ እርሱም ረድቷቸው ኢትዮጵያን ነፃነቷን ያስጠበቁበት ቀን፤ ለመላው ጥቁር ህዝብ ኩራትና ምሳሌ እንድንሆን፣ በነጮቹም ዘንድ እንደንከበር ያደረጉጓት ቀን ነው።
አንዳንዶች ግን ዛሬ ከንቱ ሆነው፣ የተከፈለውን ዋጋ ዘንግተው ምነው ጣልያን ቀኝ በገዛን ይላሉ። ባርነትን ስለማያውቁ ይመኙታል። ሌላው አፍሪካምኮ ቀኝ ተገዝቷል። ግን ምን የተሻለ ነገር አገኙ? ከኛ የተሻለ ሀብት እድገት የላቸውምኮ። ግን ሀገራቸው ሀብታቸው ሁሉ የነጮች ነው። በእጃችን ያለው ነገር ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ስለማይገባን ግን ለፈረንጅ ባርያ መሆንን እንመኛለን። ያሳዝናል።
ግን እኛ የተሰጠንን ክብር እናድንቅ። ቦታም እንስጠው። የተራዳንን እግዚአብሔርን፣ የርሱን አገልጋይ ሰማዕቱን ጊዮርጊስንም እናመስግን። የተከፈለልን ዋጋ እጅግ ውድ ነውና ከልባችን እናስበው።