Forward from: አዲስ ምልከታ🌍
በዚህች ዓለም ላይ አዲስ ነገር የለም። ጠቢቡ ሰሎሞን እንዳለው ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም። አዲስ ሀሳብ የለም። ከዚህ በፊት ሰዎች ያላሰቡት ሀሳብ፣ አሁን እኛ የፈጠርነው የለም። ድሮ የነበሩ ሀሳቦች ናቸው ዛሬም ያሉት።
ስለ ህዋና ፕላኔቶች ወዘተ ያሳመኑን በዋናነት ፊልም ሰርተው ነው። ሰዎች ፈጣን መንኩራኩሮች ሰርተው ሲሄዱ፣ ሌሎች ዓለማትን ሲያገኙ፣ በዛ ላይ ኤሊየኖችን ሲያገኙ ወይም እነዛ ኤሊየኖች ሲመጡ የተሰሩ እጅግ በርካታ ፊልሞችን አይተናል። በዚህም ነው ስለ ስፔስ ለማመን የበቃነው።
ነገር ግን እነዚህ ፊልሞች አዲስ ሀሳብ፣ ወይም አዲስ ምናብ (imagination) አላመጡም። ከጥንት የሰው ልጅ ታሪክ የነበሩ ሀሳቦችና ክስተቶችን ነው ቀይረው የስፔስ ፊልም የሰሩበት። እንዴት? የሚለውን እንይ።
👉በፊልሞቹ ሁሌም ሰዎች ፈጣን መንኩራኩሮች ሰርተው እጅግ ሰፊ በሆነው ህዋ ውስጥ ይሄዳሉ።
እነዚህን መንኩራኩሮች ምን ብለው ነው የሚጠሯቸው? Space ship
ship ምንድን ነው? መርከብ። ልክ መርከቦች በሰፊው ውቂያኖስ/ባህር እንደሚሄዱ ሁሉ እነዚህም space-ships "በሰፊው ህዋ" ይሄዳሉ የሚለው ሀሳብ ከሱ ይወሰዳል።
👉 ነጮች በመርከብ እየሄዱ ዓለምን "explore" ሲያደርጉ ወይም ሲያስሱ እንደነበረው ሁሉ እነዚህ ፊልሞች ላይም "space"ን "explore" ያደርጋሉ (ያስሳሉ)።
👉 በመርከብ ሲሄዱ የተለያዩ ደሴቶችን እንደሚያገኙ (discover እንደሚያረጉ) ሁሉ፣ በዚያም የተለያዩ ከነሱ (ከነጮች) የተለየ መልክ አለባበስ፣ አነጋገር ያላቸው ህዝቦች ያጋጥሟቸው እንደነበረ ሁሉ፣ በፊልሞቹ ላይም የተለያዩ ፕላኔቶችን ያገኛሉ (discover ያረጋሉ) በነዚህም ላይ ከነሱ (ከሰው ልጆች) የተለዩ "ኤሊየኖች"ን ያገኛሉ።
👉 በሌላ ጊዜ ደግሞ ሌሎች ህዝቦች መርከብ ሰርተው፣ ባሕር ተሻግረው መጥተው እንደሚወሯቸው ሁሉ፣ በፊልሞቹ ላይም፣ የተለያዩ "ኤሊየን" ወይም "UFO"ዎች "space-ship" ሰርተው በመምጣት ምድርን ይወራሉ።
👉 ከዚህም በላይ፣ ኤሊየኖቹ (UFOዎቹ) ሁሌም ሰውነታቸው አካሎቻቸው የሰው አይነት መልክ ያላቸው ናቸው። እንደ ሰው አይነት ቁመና፣ ሁለት ዓይም፣ ፊታቸው እንደ ሰው ያለ፣ እጅና እግራቸውም ከሞላ ጎደል ከሰው ጋ የተመሳሰለ ነው። እንጂ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ፣ መልኩና ቅርጹ የተለየ፣ በምናባችንም በሀሳባችንም አስበነው የማናውቀውን አይነት ፍጡር አሳይተው አያውቁም።
እንደውም እነዚህ ኤሊየኖች ሰው መምሰላቸው በዙ የሳይንስ ፊክሽን ወዳጆች ያሳስባቸዋል። እናም ኤሊየኖች የሰው መልክ የመምሰላቸውን ክስተት ስም ሰጥተውታል፦ Anthropomorphism ብለው። ቃሉ ሌሎች ክስተቶችንም የሚወክል ቢሆንም ለዚህኛው ዓውድም ይጠቀሙታል።