Hello Doctor
❓Hello selam nachu fit lay miweta bgurn endet matfat yechalal ken wedeken eyebeza ena getstayen eyabelashew slehone meftehe btsetugn des ylegnal❔
ጤና ይስጥልኝ ውድ የHello Doctor ተከታታዮቻችን እደምን አመሻችሁ በያላችሁበት ሰላማችሁን እየተመኘን ለእናተ ይጠቅማል ብለን ያሰብንውን የኛን መረጃ እንሆ ይከታተሉን።
#ቡግር ምንድነው?
ቡግር በቆዳ ላይ የሚገኙ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ የቆዳ ሴሎች ሲሞሉ ወይም ሲደፈኑ የሚከሰት የቆዳ ችግር ነው፡፡
ብዙውን ጊዜ ቡግር ነጭ ወይም ጥቁር አናት አንዳንዴም ቀያይ ነጠብጣቦች በቆዳ ላይ ሊታዩ ይችላሉ፡፡
ነጠባጣቦቹ መጠናቸው ሊለያይ ይችላል፤ ህመም ሊኖራቸውም ላይኖራቸውም ይችላል፡፡
ብዙውን ጊዜ ቡግር በፊት ላይ ይወጣል፤ እንዲሁም በአንገት፣ ደረት፣ ትከሻ እና ጀርባም ላይ ሊወጣ ይችላል፡፡
ቡግር በማንኛውም ሰው ላይ ሊታይ ይችላል፡፡
እንደሚስተዋለው ከሆነ ግን ቡግር በጉርምስና ወይም በወጣትነት እድሜ ውስጥ ያሉት ላይ ይበረታል፡፡
በዚሕ ጊዜ የመጣ ከሆነ እድሜ በጨመረ ቁጥር እንዲቀንስ ይጠበቃል፤ ጥቂቶች ላይ ግን አብሮአቸው ይኖራል፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ግን አንዳንድ ጊዜ ቡግር በሆርሞን ችግር ምክንያት ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፡፡
በእርግዝናም ወቅት የመከሰት እድል አለው፡፡
#ምልክቶቹ_ምንድናቸው?
· ነጭ አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
· ጥቁር አናት ያላቸው ነጠብጣቦች
· ትናንሽ ቀያይ ህመም ያላቸው ነጠብጣቦች
· ቀያይ ጫፍ ላይ ትንሽ መግል ያላቸው ነጠብጣቦች
· ተለቅ ያሉ ጠጣር ህመም ያላቸው እብጠቶች
· ህመም ያላቸው መግል የያዙ ከቆዳ ስር ያሉ እባጮች
#ቡግር በምን ምንክንያት ይመጣል?
- ለቡግር መከሰት ዋና ዋና የሚባሉት ምክንያቶች፤
- ቅባትማ የቆዳ አይነት
- የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት እና በሞቱ ሴሎች መዘጋት
- ባክቴሪያዎች
- የአንዳንድ ሆርሞኖች ስራ መጨመር (ለምሳሌ Androgen)
ከላይ እነደጠቀስነው ብጉር ቅባት አመንጪ እጢዎች (Sebaceous gland) በሚበዙበት የቆዳ ክፍል አካባቢ ነው፡፡
እነዚህም ፊት፣ ግንባር፣ ደረት፣ የላይኛው የጀርባ ክፍል እና ትከሻን ያጠቃልላል፡፡
የፀጉር ቀዳዳዎች ከቅባት አመንጪ እጢዎች ጋር የተያያዙ ናቸው፡፡
የእነዚህ ቀዳዳዎች ግርግዳ ሲያብጡ ነጣ ያለ አናት ይኖራቸዋል፤ ወይም ደግሞ አናታቸው ክፍት ከሆነ ሲጠቁር ይችላል፡፡
በዚህ ጊዜ ቀዳዳዎቹ በባክቴሪያ እና ቅባት ይሞላሉ፡፡
ቀያይ ከፍ ከፍ ያሉ ውስጣቸው ነጭ የሆኑ ነጠብጣቦች የሚፈጠሩት ደግሞ የፀጉር ቀዳዳዎች በቅባት ከመዘጋታቸው በላይ በባክቴሪያ ሲጠቁ ነው፡፡
#ቡግርን ምን ሊያባብሰው ይችላል?
· የሆርሞን መለዋወጥ ወይም መዛባት
· አንዳንድ መድሐኒቶች
· አመጋገብ (የተጠበሱ ምግቦች፣ በካርቦሀይድሬት የበለፀጉ ምግቦች)
· ጭንቀት ወይም ውጥረት
· ሸካራ ሳሙና መጠቀም እና በጣም የሞቀ ውሃ መጠቀም
· የፀጉርና ቆዳ መጠበቂያ ውጤቶች በተለይ በውስጣቸው የሚያሳክክ ንጥረ ነገር የያዙ ከሆነ
#ተጋላጭነት
- የጉርምስና የእድሜ ክልል
- የሆርሞን መዛባት
- የዘር ተጋላጭነት
- ቀባትማ ነገሮችን በቆዳ ላ መጠቀም
- ቆዳን የሚፈገፍጉ (የሚፈትጉ) ነገሮች
- ጭንቀት
#ቡግርን መከላከል ይቻላል?
ቡግርን በዘላቂነት መከላከል ባይቻልም እንዳይባባስ የሚወሰድ እርምጃዎችና ጥንቃቄዎች ግን አሉ።
ከነዚህም መካከል ፦
· በዝግታ ወይም በጣም ሳያሹ መታጠብ ለቆዳዎ ጤንነት አስፈላጊ ነው። በጣም ማሸት፣ መጥረግ፣ መፈተግ ወይም መፈግፈግ ተገቢ አይደለም።
· በጣም እንዳያልብዎ መጠንቀቅ። ላብ እንዲያልበን የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ካደረግን በኋላ ወዲያው መታጠብ።
· ፀጉርዎ ቅባት ካለው ወይም ከበዛበት መታጠብ
· ጭንቀትን አለማብዛት
· አንዳንድ የፀጉር መንከባከቢያ ምርቶችን መጠቀም ማቆም፤ እንደ ጄል፣ ክሬምና የመሳሰሉት
· ፊትዎን ቶሎ ቶሎ ከመንካት መቆጠብ
· ለስላሳ የኮተን ልብሶችን መጠቀም፤ በተለይ ከቆዳ ጋር ንክኪ ያላቸው ከሆነ
· ከቅባት እና ኬሚካል ጋር ያለዎትን ግንኙነት መቀነስ ለምሳሌ እንደ ፔትሮሊየም ያሉትን
#ሀኪም ጋር መቼ መሄድ አለቦት?
በቤት ውስጥ ማድረግ የሚመከሩ መንገዶች የማይሰሩ ከሆነ የቆዳ ሀኪሞት ጠንከር ያሉ መድሐኒቶችን ያዝሎታል፡፡
ሴቶች ላይ ቡግር ለብዙ አመታት ሊቆይ ይችላል፤ በአባዛኛው የወር አበባ ከመምጣቱ ከአንድ ሳምንት በፊት ይመለሳል፡፡ እንዲህ አይነቱ ቡግር ብዙውን ጊዜ የወሊድ መቆጣጠሪያ የሚወስዱ ሴቶች ላይ በራሱ ይጠፋል፡፡
አዋቂዎች ላይ በድንገት የሚወጣ፣ በፍጥነት የሚበዛ ቡግር ተጓዳኝ የጤና እክልን ሊያመላክት ስለሚችል ምርመራዎች መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
Hello Doctor
ለወዳጆ ያጋሩ
Join 👇
@Hellodoctor11👩⚕
@Hellodoctor11👩⚕
@Hellodoctor11