እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር የአፈፃፀም ስምምነት ውል (performance contracting agreement) ተፈራረመ።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አግልግሎትን ተደራሽነት፣ ጥራት እና አግባብነትን መሠረት ባደረጉ ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (KPIs) ላይ ያተኮረ የአፈጻጸም ስምምነት ውል በዩኒቨርሲተው ፕሬዝደንት በጋርዳቸው ወርቁ(ዶ/ር) አማካኝነት ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ተፈራርሟል።
ዶ/ር ጋርዳቸው እንደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የትምህርት ጥራትን በማስጠበቅ ብቃትና ጥራት ያለው ዜጋ ማፍራት፣ችግር ፈቺ ምርምር እና ማህበረሰብ አግልግሎት መስጠት የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ መሆኑንን ጠቅሰው የስምምነት ውሉ መሰረት ያደረገባቸው ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲው ተግባራዊ ሲደረጉ እንደቆዩ ገልጸዋል። በቀጣይነት በገቡት ስምምነት መሠረት ስራዎችን በየደረጃው ላሉ ስራ ክፍሎች እና ሠራተኞች በማውረድና ጠንክሮ በመስራት ከፍተኛ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሠራ ጨምረው ተናግረዋል።
የቁልፍ ስራዎች አፈጻጸም ውሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይንሳዊና ዓለም አቀፋዊ መለኪያዎች ላይ ያተኮረ እድገት እንዲኖራቸው እንደሚያስችል የተገለጸ ሲሆን ስምምነቱ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለው የክትትልና ግምገማ ስርዓት እንዲኖርና ዩኒቨርስቲዎች በተልዕኳቸው ላይ አትኩረው እንዲሰሩ እንደሚደረግ በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ተገልጿል።
ስምምነቱ የተፈረመው ትምህርት ሚኒስቴር ከሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር የአፈጻጸም ስምምነት ውል በተፈራረመት ወቅት ሲሆን የትምህርት ሚኒስትሩን በመወከል የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲን በመወከል ደግሞ ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ ፈርመዋል።