የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በታላቅ ድምቀት ተጠናቀቀ።
ጥር 27/2017 ዓ፣ም፤አዲስ አበባ
"ስፖርት ለአንድነት እና ለጋራ ዕድገት"በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከጥር 17-27 /2017 ዓ፣ም ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ሲጠናቀቅ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በአጠቃላይ ውጤት 9ኛ ሆኖ አጠናቋል።
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዚህ ፌስቲቫል በ4 የስፖርት አይነቶች ማለትም በእግር ኳስ፣በአትሌቲክስ፣በወርልድ ቴኳንዶ እና በባህላዊ ስፖርት ተሳትፎ በባህላዊ ስፖርት ቡብ ጨዋታ ዋንጫ እና ማዳሊያ በማግኘት አንጋፋ እና ነባር ዩኒቨርሲዎችን በመፎካካር በውድድሩ ከ49 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 9ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ስኬታማ ውድድር አሳልፏል።
ይህ ውጤት ከ4ኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ቀዳሚ ሲያደርገው በአማራ ክልል ከሚገኙ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከወልዲያ እና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲዎች በቁጥር 3ተኛ ደረጃ ላይ ሆኖ አጠናቋል ።
የዚህ ስፖርት ፌስቲቫል አጠቃላይ አሸናፊ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን የፀባይ ዋንጫ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ወስዷል ።
በፌስቲቫሉ በባህላዊ ስፖርት ቡብ ጨዋታ ሴት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፣በቡብ ወንድ ደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ፣በገበጣ ሴት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፣በገበጣ ወንድ ወልዲያ ዩንቨርሲቲ ፣ ፣በወርልድ ቴኳንዶ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ፣በእግር ኳስ ወሎ ዩንቨርሲቲ፣በቼዝ ሴት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣በቼዝ ወንድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣አትሌቲክስ ወንድ ሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ እና አትሌቲክስ ሴት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ አሸናፊ ሆነዋል።
ያለህን ዕምቅ አቅም ለይተህ ተጠቀም!