ለአዲስ መምህራንና ሰራተኞች የትውውቅ ሥልጠና (Induction Training) ተሰጠ፡፡
የካቲት 19/2017ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በብቃት እና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አዘጋጅነት በቅርብ ጊዜ ወደ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በዝውውር እና በቅጥር ለተቀላቀሉ አዲስ መምህራንና ሰራተኞች የትውውቅ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
በትውውቅ ስልጠናው ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ልማት ም/ ፕሬዝዳንት ወሀቤ ብርሃን(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው ይህን ዓላማ ለማሳካት የሰው ሀብት ልማት ወሳኙ በመሆኑ ዩኒቨርሲቲው ብቁ ፣በዲስፒሊን የታነጸ መምህርና የአስተዳደር ሰራተኛ እንዲሆኖር ይህ ስልጠና አስፈላጊ
መሆነኑ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ወሀቤ አያይዘውም የዛሬው ስልጠና የተቋሙን ራዕይ ፣ ተልዕኮ፣ እሴት፣ ህግና ደንብ
ዙሪያ ያተኮረ መሆኑን ገልጸው ሁሉም አዳዲስ መምህራን እና ሰራተኞች ለተቋሙ ስኬት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
ሥልጠናውን የሰጡት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ብቃት እና ሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ አቶ ሀብታሙ
ጥላሁን ሲሆኑ ስለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዓላማ፣ ርዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው
የሚተገበሩ የመንግስት አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎች ዙሪያ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል። ስራ አስፈጻሚው ስለ ለሠራተኞች የሚገቡ ጥቅማጥቅሞች፣ የሠራተኞ መብትና ግዴታ፣ የሥራ አፈጻፀም፣ ዲስፕሊንና ቅሬታ አቀራረብን
የተመለከተም ስልጠና ሰጥተዋል ።
በመጨረሻም በትውውቅ ስልጠናው በተሰጡ ርዕሶች ዙሪያ ጥያቄ እና አስተያየት የተሰጠ ሲሆን ሲሆን በስልጠናው 100(አንድ መቶ) የሚሆኑ አዲስ መምህራንና ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።