እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ።
-----
የመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ሁለቱ ተቋማት በጋራ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።
በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ክንዴ ብርሃን (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ከእንጅባራ ጠቅላላ ሆስፒታል እና ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈራረሙን አስታውሰው የጤና ሳይንስ ተማሪዎችን በንድፈ ሃሳብ ከሚማሩት በተጨማሪ በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት ከአቅራቢያ ሆስፒታሎች ጋር ለመስራት በሚያግዝ መልኩ የስምምነት ሰነዱ ፊርማን አስፈላጊነት ተናግረዋል።
የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ አዳነ ገበየሁ በበኩላቸው የሰምምነት ሰነዱ የአካባቢውን ማህበረሰብ ጤና ከማሻሻሉ በተጨማሪ የሆስፒታሉን ደረጃ የሚያሳድግልን ነው ሲሉ ተናግረዋል።
የስምምነት ሰነዱ አጠቃላይ ሃሳብ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በሆኑት ዳንኤል አዳነ (ረ/ፕሮፌሰር) የቀረበ ሲሆን ዓላማውም በሁለቱ ተቋማት መካከል የመማር ማስተማርን፣ጥናትና ምርምርን፣የማህበረሰብ አገልግሎትን፣የመድሃኒትና የቁሳቁስ ድጋፎችን እና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ያካተተ ነው።
በስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የዩኒቨርስቲው ከፋተኛ አመራሮች እና የቻግኒ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ኃላፊዎች እንዲሁም የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን እና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
የካቲት 20/2017 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ