በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኪነ-ጥበብ ምሽት ተካሄደ፡፡
-----
የካቲት 30/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የአገው ጥናት ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ የኪነ -ጥበብ ምሽት በደማቅ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡
የፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) የአገው ጥናት ኢንስቲትዩት የተቋቋመው በአገው ባህል፣ ቋንቋ እና ታሪክ ላይ ጥናት ለማድረግና ለማስተማር መሆኑን ጠቅሰው የአገው ባህል፣ ቋንቋ እና ታሪክ የዩኒቨርሲቲው አንዱ የትኩረት መስክ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም ኪነ-ጥበብ የአንድን ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ክንዋኔዎች ለማስተማር የሚያገልግል በመሆኑ የዩኒቨርሲተው ማህበረሰብ ኪነ-ጥበብን ተጠቅሞ እየተዝናና መማር ይችል ዘንድ ይህ የኪነ-ጥበብ ምሽት በዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በአገው ጥናት ኢንስቲትዩት አማካኝነት
መዘጋጀቱንም ጨምረው ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ክንዴ አክለውም የዛሬው ኪነ-ጥበብ ምሽት ሆነ በቀጣይ ለሚደረጉ የኪ-ጥበብ ዝግጅቶች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ኪነ-ጥበብን ፣ የማህበረሰብን ባህል ለማስተዋወቅ፣ ልማትን ለማሳለጥ፣ የህዝብንና ሀገርን አንድነት ለማጽናት፣ እየተዝናኑ ለመማር እና ለመሳሰሉ በጎ ዓላማዎች ማስፈጸሚያ መሳሪያነት ሊጠቀማቸው እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid0M2eVHGwN51Y56XibsQTXS6NWWKWHqEJq3QhHGpVJerrrJjE3xPK3PKauiJy3tCbel/?app=fbl