በሀገረ ማሌዥያ የሚገኘው ትልቁ አል ቡሃሪ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ሙሉ ወጪያቸውን ተሸፍኖላቸው መማር ለሚፈልጉና በጦርነት ለተጉዱ አካባቢ ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል አዘጋጅቶል ነበር ።
መስፈርቱን ያሟሉ 5 የትግራይ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች ዛሬ ማሊዢያ ተጉዘዋል።ይህንን ዕድል ያገኙት አምስት የትግራይ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች በመቐለ ዩኒቨርስቲ እና በመቐለ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ይህንን ዕድል እንዳገኙ ኢንጂነር ሷሊህ እና ሌሎችም በመተባበር ያሳኩት መሆኑ ተገልጿል።
ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ተምረው ራሳቸው፣ ህዝባቸውንና ሀገራቸው እንደሚጠቅሙ ተስፋ የተጣለባቸው ሲሆን በሂደቱ ላይ በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በጊዜያቸውና በሌላም የተባበሩን ግለስቦችና ተቋማት ምስጋና ቀርቧል።
በዚህ ወቅት የትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ከነዩኒፎርማቸው ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሒጃብ ለብሰው ለማማር የተከለሉ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቹም ፎርም የመሙላት እድል ተነፍገው እንደሚገኙ የሚታወቅ ነው።
እነዚህ የውጭ የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደ ማሌዥያ ያቀኑ የትግራይ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ለተደረጉ ተማሪዎች የስነልቦና ከፍታ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተማሪዎችን እንዳይማሩ ላደረጉ አካላት ደግሞ ሂጃብ ምንም ማድረግ እንደማይከለክል ማሳያ ይሆናሉ ተብሏል።
@islam_in_school