"ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ መልበስ አይቻልም!" - ዲላ ዩኒቨርሲቲ
ላለፉት 3 አመታት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በነፃነት ይለበስ የነበረውን ኒቃብ ያለ ሕግ እና መመሪያ ከወር በፊት ከልክሎ የነበረው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ እንደነበር ይታወቃል:: በሰሞኑም ለብሳችሁ አትገቡም በማለቱ ሙስሊም ተማሪዎች ከግቢ ውጭ ከመስጂድ ማደራቸው ይታወሳል::
የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም በዛሬው እለት ከሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረገው የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር "ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ በግቢ ውስጥ ለብሶ መግባትም ሆነ መንቀሳቀስ አይቻልም!" የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተማሪዎች አሳውቀዋል::
በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ተጨባጭ ያልሆነ እና እምነቱን የሚዳፈር ምክንያት በማቅረብ የሚደረግ የመብት ጥሰት መቆም እንዳለበት:: ኒቃብንም ሆነ የትኛውንም ኢስላማዊ አለባበስ የደህንነት ስጋት አድርጎ ማሰብም ሆነ ማቅረብ ሀይማኖቱን ከማንቋሸሽ ተለይቶ አይታይም:: ኒቃብ በሐይማኖት እንዲለበስ የታዘዘ የእምነት ልብስ ሲሆን በሕግ ደግሞ የማይከለከል የነፃነት መገለጫ ነው::
በአላህ ፈቃድ መሠል ጥላቻ ተኮር የመብት ጭቆናዎች በዚህ ትውልድ ታሪክ ይሆናሉ ••• ነፃነት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም!
©️EHEMSU
@islam_in_school