❗ጥቅምት 17 | ቅዱስ እስጢፋኖስ❗
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
ጥቅምት 17 ማዕረገ ዲቁናን በሐዋርያት እጅ በአንብሮተ እድ የተሾመበት ዕለት ነው።
🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት፡- እስጢፋኖስ ማለት ‹‹መደብ›› ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ‹‹አክሊል›› ማለት ነው፡፡
🔵👉 ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ ሁለት ወንድ ልጆችንም ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ይህ ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡
🔴👉 እስጢፋኖስም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ7ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡
🔵👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጀመሪያ ከታላቁ የኦሪት ምሑር የእነ ቅዱስ ጳውሎስ መምህር ከነበረው ከገማልያል የኦሪትን ሥርዓት ጠንቅቆ የተማረ ምሑረ ኦሪት ነው፡፡ ትንቢተ ነቢያትን ያውቅና የአዳኙን መሢሕ መምጣት በጸሎትና በተስፋ ሲጠባበቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችንን መንገድ ሲጠርግ ቢያገኘው ደቀ መዝሙር ሆነና በትጋት ሲያገለግለው ቆየ፡፡
🔴👉 ከ6 ወራት በኃላ ክብር ይግባውና ጌታችን በዮሐንስ እጅ ተጠመ፡፡ ከጌታችንም ጥምቀት በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ይመጣ ዘንድ ያለው መሢሕ እርሱ መሆኑን በአንክሮ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስንም ቅዱስ እስጢፋኖስ ራሱን ጌታችንን አግኝቶት የአንደበቱን ቃል የእጁን ተአምራት አይቶ ይመን በማለት ወደ ጌታችን ዘንድ ላከው፡፡
🔵👉 ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ እርሱም አስቀድሞ ጌታችን ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተምሯልና ጌታችንም 72ቱን አርድእት ለስብከተ ወንጌል ሲያሰማራቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኃላ ወንጌልን በአዋጅ ይሰብክ ጀመረ፡፡ ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታችን ዕርገት በሁኃላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህ ማኅበርተኞቹን እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ክርስትናን አስፋፋ፡፡
🔴👉 የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡ በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› እያለ ስለገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡
🔵👉 ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ ‹‹የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ›› ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ 22፡20፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡
🔴👉 ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና ‹ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና› የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት፡፡›› ሐዋ 6፡8-15፡፡
🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡
🔴👉 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡
🔵👉 እስጢፋኖስም ‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል› ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም ‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው› ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ የሐዋ 7:52-60፡፡
🔴👉 የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር 1 ቀን ነው፡፡ መእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀብረውታል፡፡ ጥቅምት 17 የተሾመበት በዓሉ ሲሆን መስከረም 15 ቀን ደግሞ ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡
(ምንጭ፡- የመስከረምና የጥቅምት ወር ስንክሳር)
❗የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ምልጃ ተራዳኢነቱ በረከቱ ሁሉ በሁላችን ላይ ይደርብን❗
🔷👉አንብበው ጨርሰዋል? እንግዲያውስ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ሼር በማድረግ ወንጌን ያዳርሱ!!
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም
ሆለታ
ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom
🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w
🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube