ነፍስ ኄር አለቃ ኪዳነ ወልድ
(1864-1936)
#Henock Yared Fenta በ#ሔኖክ ያሬድ ፈንታ እንደከተቡት።
ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በዕለተ ሰኞ ነሐሴ 22 ቀን 2009 ዓ.ም. ባዘጋጀው ዓመታዊ መሰናዶ፣ በሕይወት ዘመን የሥነ ጽሑፍ የላቀ ባለውለታ ዘርፍ፣ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌን ተሸላሚ አድርጓል፡፡
ነፍስ ኄር አለቃ ኪዳነ ወልድ (1864-1936) በተለይ በመጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ዐቢይ ሥራቸው በብዙዎች ዘንድ ይታወቃሉ፡፡ ይህንን ሥራቸው በያዘው ጥልቅ ሐሳብ አንፃር ያዩት አንዳንድ ባለሙያዎች ከኢንሳይክሎፒዲያ ጋር ያመሳስሉታል፡፡
ክብረት ይስጥልን ሆሄ!!!
ኪወክ ሐውልታቸው - መጽሐፋቸው!
በኢትዮጵያ ሕዋ እንደተወርዋሪ ኮከብ ብቅ ብለው ካለፉት እሙራንና ማዕምራን (ታዋቂዎችና አዋቂዎች) መካከል በ19ኛው በ20ኛው ምእት ዓመት ውስጥ የኖሩት አለቃ ኪዳነ ወልድ ከፍሌ አንዱ ናቸው፡፡ ዘንድሮ ከተወለዱ 145ኛ ዓመት፣ ካረፉ ከአፀደ ሥጋ ከተለዩ 73 ዓመት ሞልቷቸዋል፡፡
ሥራዎቻቸው በቤተክህትም ሆነ በቤተመንግሥት ይሁንታንና ይበልታን ያገኘ፣ እስከዘመናችን ድረስም በማጣቀሻነት በማስተማሪያነት፣ ዘርፈ ብዙ አገልግሎት እየሰጠ ለመሆኑ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ከመዠመርያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ ድርሳኖች ውስጥ ሳይጠቀሱ ያለፉበት ጊዜ የለም፡፡
ለየድርሳናቱ (ቴሲስ ዲዘርቴሽን) ምልዐት ከኪዳነ ወልድ የጽሑፍ ጎተራ ያልዘገነ ያልቀመሰ፣ ያላTaጣመ አይኖርም፡፡ የግእዝ ቋንቋን ከሌሎች ሴማዊ ቋንቋዎች ጋራ እያገናዘቡ በመመርመር የፊሎሉጂ ጥናት በማድረግ ረገድ በፋና ወጊነት በአገሬው ሊጠቀሱ ቢችልም፣ በዘመናችን የሳቸውን ፈለግ ተከትሎ ንፅፅራዊ ጥናት ስለመቀጠሉ የተሰማ የተጻፈ ነገር አለመኖሩን የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጀመረውና ግእዝና ዐረቢኛን ብቻ መሠረት ያደረገው የፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል ወደ ሌሎቹም ተዛማጅ ቋንቋዎች ይሸጋገር ይሆን?
ለውጭ አገር ዕውቆች ከኮንፊሽየስ ጀምሮ ክብር የሚሰጠው ዩኒቨርስቲያችን ለኪወክ (ኪዳነወልድ ክፍሌ) የሚሰጠው መቼ ይሆን?
በቀኃሥ ዘመን ለብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ በመወዘክር የማንበቢያ እልፍኝ እንደተሰየመው ለኪወክስ የሚሰይም ማን ይሆን?
***
በመሚል ሄኖክ ያሬድ ፈንታ የከተቡትን ጽሑፍ አጋራናችኹ።