"ሊያብብ ሲል"
ሱስ ሳይበላው፣ ሲጋራ መግዣ መለመን ሳይጀምር፣ ጉስቁልና ሳያፈዘው፣ ለልብሱ መቆሸሽ ደንታ ቢስ ከመሆኑ በፊት፣ ሰዎችም ሲጣራ ባልሰማ መሄድ ሳይጀምሩ፣ ቃል አባይ ከመሆኑ በፊት፣ ክብሬ ማለት ሳያቆም፣ ለትንሽ ለትልቁ መላክ ሳይጀምር በፊት…
ቆንጆ፣ ተወዳጅ እና ዘናጭ ነበር።
ከጓደኞቹ በላይ ድምቅ ያለ ልጅ ነበር፤ የፀጉሩን ፍሪዝ በመስታወት አስር ጊዜ እያየ አስር ጊዜ ያስተካክል ነበር።
ሕልመኛ ነበር። እንደ ሁሉም ወጣት ሀብታም መሆን፣ አዋቂ መሆን፣ ቤተሰቦቹን የመርዳት ሕልም ነበረው።
የተንሸዋረረ አራድነት አሳስቶት የለኮሳት ሲጋራ፣ ለሳቅ ብሎ የተጎነጫት አረቄ፣ ለሙድ ብሎ የቀነጠሳት የጫት ቅጠል ስትደጋገም አፈዘዘችው፤ ሕልሙን፣ ወጣትነቱን፣ ክብሩን አረገፈችው።
ማንም ብርቱ ነኝ ቢል ታግሎ የማያስመልሳትን ወጣትነቱን ለማያውቀው ጣዖት እየሰዋት ነው።
ጥግ ላይ ተቀምጦ፤ ዘመን ሄዶ ዘመን በመጣ ቁጥር የሚመጡ ለውጦችን ከዳር በትዝብት እየተመለከተ
'ጊዜው እንዴት ነው የሚሮጠው?'
የሚል ይመስለኛል።
"አዎ! እሱ ጋ ያመኛል!"
ገጽ-41
(አድኃኖም ምትኩ)