በዚህ ዓመት ፣ ብንጣላ መታረቂያ
ብንታረቅ ለመጣያ ፥ ትንሸ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ቦታ መሠደጃ ፥ ምናለበት ፤
ለምናልባት ብንተውለት?!
በአንጎላችን መላወሻ ፣ ትንሽ ቦታ እንተውለት
‹‹ምናልባት›› የምንልበት!!
ልክ እንደአምና ለዚህ ዓመት ።
ብንጣላ መታረቂያ ፥ ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሠር ይቅር ማያ ፥ ትንሽ እንተው ! መጠለያ ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ስራ ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ ፤
በልባችን ደግ በኩል ፣ የጳጉሜ አይነት ፥ እንፈልግ ባዶ ቦታ ።
----------------------------
ነብይ መኮንን - ጳጉሜ 5 2005 ዓ.ም
ብንታረቅ ለመጣያ ፥ ትንሸ ቦታ መጠለያ
ትንሽ ቦታ መሠደጃ ፥ ምናለበት ፤
ለምናልባት ብንተውለት?!
በአንጎላችን መላወሻ ፣ ትንሽ ቦታ እንተውለት
‹‹ምናልባት›› የምንልበት!!
ልክ እንደአምና ለዚህ ዓመት ።
ብንጣላ መታረቂያ ፥ ብንታረቅ ለመጣያ
ብንታሠር ይቅር ማያ ፥ ትንሽ እንተው ! መጠለያ ፡፡
ጥግ ድረስ የለም ስራ ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ ፤
በልባችን ደግ በኩል ፣ የጳጉሜ አይነት ፥ እንፈልግ ባዶ ቦታ ።
----------------------------
ነብይ መኮንን - ጳጉሜ 5 2005 ዓ.ም