~አንዳንዴ… የሆኑ ሰዎች ካንተ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር ይጠጉሀል። ካገኙ በኋላ ቀስ ብለው እየተንሸራተቱ ከናካቴው ይተውሀል። በቃ ምርር ብሎህ «ሰው በቃኝ!» ብለህ እራስህን ለማስታመም ስትሞክር ደግሞ የሆኑ የሚገርሙ ሰዎች ወደ ሕይወትህ ይገባሉ። ይወዱሀል፣ ይናፍቁሀል፣ ያስቡልሀል። አንተ ግን ለነዚህ ሰዎች የሚገባቸውን ፍቅርና ክብር መስጠት ይከብድሀል። ተጠቅመው የጣሉህ ሰዎች እየታወሱህ ትፈራለህ። ፍቅር የሚሰጡህ ሲመጡ የራሳችሁ ጉዳይ የሚል አቀባበል ታሳያቸዋለህ፣ አብዝተው አይዞህ እያሉ ሲንከባከቡህ ምን ፈልገው ነው ብለህ ትጠራጠራለህ። ብቻ ምንም ነገራቸው አይዋጥልህም። አንዳንዴ…ለማይገባቸው ሰዎች ያለህን ሁሉ ትሰጣቸውና ለሚገባቸው ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት ብቻ ይቀርሀል።
አንዳንዴ… በትክክል ላንተ የሚጨነቁና የሚያስቡ ሰዎች ላይ ያኔ ባንተ ላይ ያሻቸውን የሰሩ ሰዎች ትሆናለህ። ደግሞ ያማል! እምነት እና ፍቅር የንግድ ፍቃድ አይደለም በቀላሉ አይታደስም።እክል የገጠመው ፍቅር እና እምነት በጊዜ ውስጥ ነው የሚታደሰው። ምክንያቱም ቁስልህ መድረቅ ያስፈልገዋልና።
አንዳንዴ… አወ አንዳንዴ…
=t.me/AbuSufiyan_Albenan