َ አ ْ ል ُ ኩ ُ ኑ ْ ዝ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል ቁርኣንና ሀድስን፣ [በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን እና የታማኝ የሱና ዑለማዎች አስተምሮቶች ፈታዋወች ሙሐደራዎች የሚለቀቅበት የሰለፉነ አስሷሊህ ዕምነት የሚቀርብበት ቻናል ነው።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


~አንዳንዴ… የሆኑ ሰዎች ካንተ የሚፈልጉት ነገር ሲኖር ይጠጉሀል። ካገኙ በኋላ ቀስ ብለው እየተንሸራተቱ ከናካቴው ይተውሀል። በቃ ምርር ብሎህ «ሰው በቃኝ!» ብለህ እራስህን ለማስታመም ስትሞክር ደግሞ የሆኑ የሚገርሙ ሰዎች ወደ ሕይወትህ ይገባሉ። ይወዱሀል፣ ይናፍቁሀል፣ ያስቡልሀል። አንተ ግን ለነዚህ ሰዎች የሚገባቸውን ፍቅርና ክብር መስጠት ይከብድሀል። ተጠቅመው የጣሉህ ሰዎች እየታወሱህ ትፈራለህ። ፍቅር የሚሰጡህ ሲመጡ የራሳችሁ ጉዳይ የሚል አቀባበል ታሳያቸዋለህ፣ አብዝተው አይዞህ እያሉ ሲንከባከቡህ ምን ፈልገው ነው ብለህ ትጠራጠራለህ። ብቻ ምንም ነገራቸው አይዋጥልህም። አንዳንዴ…ለማይገባቸው ሰዎች ያለህን ሁሉ ትሰጣቸውና ለሚገባቸው ሰዎች የተሳሳተ አመለካከት ብቻ ይቀርሀል።

አንዳንዴ… በትክክል ላንተ የሚጨነቁና የሚያስቡ ሰዎች ላይ ያኔ ባንተ ላይ ያሻቸውን የሰሩ ሰዎች ትሆናለህ። ደግሞ ያማል! እምነት እና ፍቅር የንግድ ፍቃድ አይደለም በቀላሉ አይታደስም።እክል የገጠመው ፍቅር እና እምነት በጊዜ ውስጥ ነው የሚታደሰው። ምክንያቱም ቁስልህ መድረቅ ያስፈልገዋልና።
አንዳንዴ… አወ አንዳንዴ…
=t.me/AbuSufiyan_Albenan


የጁሙዓ ኹጥባ (ምክር)
➴➴➴➴➴
=========

🖇 ርዕስ፦«ትክክለኛው/እውነተኛው ስኬት»በሚል ርዕስ
⤵️العنوان: "الفوز الحقيقية".
➴➴➴➴➴
========
ከተዳሰሱ ነጥቦች መካከል:-
👉 ትክክለኛ/እውነተኛ የሆነው ስኬታማነት፣

👉 ስኬታማ ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ፣

👉ትልቁ ስኬታማነት ምን እንደሆነ፣

👉 በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ የሆነው ምንድነው ትክክለኛ/እውነተኛው ስኬታማነት መተዋወስ አስፈላጊ ስለመሆኑ፣

👉ለቀጣዩ ህይወታችን ለአኼራችን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ፣

👉ሁላችንም እንደምንሞት እያወቅን ለዚህ ለምንሞትለት ዝግጅት አለማድረጋችን፣ መዘጋጀት አለብን፣

👉 ትክክለኛው ስኬት ምን እንደሆነ፣

👉 የስኬት ባለቤቶች መገለጫዎች/ባህሪያት ምን እንደሆነ፣

👉እነዚህ የትከክክለኛ ስኬት ባለቤቶች ደመወዝ/ምንዳ ምን እንደሆነ፣

👉 የዱኒያ ጥፍ ጥና ሳያታልልህ ትክክለኛ/እውነተኛ ከሆነውን ስኬት እንዳያታልልህ መዘጋጀት፣

👉 ለትክክለኛው ስኬት/ለጀነት መዘጋጀት እንዳለብን፣

👉ዘላለማዊ የሆነውን ፀጋ ለማግኘት መዘጋጀትእንዳለብን፣

👉ይህንን ፈውዝ/ስኬት ለማገኘት በዱዓዕ፣ከሽርክና ከሙሽሪክ፣ከቢዲዓናከሙብተዲዕ መራቅ እንደሚኖርብን፣
➴➴➴➴➴
==============
🎙በኡስታዝ ሰዓድ ዓብዱለጢፍ ሀፊዘሁሏህ
🎙لآستاذ سعد بن عبد الطيف -حفظه الله-

➴➴➴➴➴
ይ ደ መ ጥ
===============
🗓ሰኔ‐ 07‐ 10 - 2016E.C
🕌ባህር ዳር ከተማ
🕌 بمدينة بحردار [إثيوبيا]؛ في مسجد البخاري
#size መጠን 30.28 MB
#length 30:24 min
➴➴➴➴➴
=========
🕌መስጂደል ቡኻሪ
🌎ባህር ዳር፣ ኢትዮጲያ
➴➴➴➴➴
========
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصير


🌸የተወስኑ ቃላቶች ወደ ጀነት
የተወሰኑት ደግሞ ውደ እሳት
ሊመሩን ይችላሉ‥
๏ የምትናገሩትንም ሆነ የምትፅፉትን
ልብ ብላችሁ አድርጉት ።

(مَا يَلْفِظُ مِنْ قَوْلٍ إِلَّا لَدَيْهِ رَقِيبٌ عَتِيدٌ)
" ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ
ተጠባባቂና ዝግጁ የሆኑ (መላእክት)
ያሉበት ቢሆን እንጂ ፡፡"
🦋............🌹..........🦋


•┈•ኢድ ሙባረክ 𝔈𝔦𝔡 𝔪𝔲𝔟𝔞𝔯𝔢𝔨

┊┊┊⇣
┊┊⇣
┊⇣
https://t.me/kunuzzza
❥:::::::::::: #ኢድ_ሙባረክ!
𝓔𝓲𝓭 𝓶𝓾𝓫𝓪𝓻𝓮𝓴:::::::::❥

እንኳን ለ1445 አ. ሂ የዒድ አል-አደሀ  በአል አላህ በሠላም አደረሰን አደሰሳችሁ!
🎀 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
🎈 عيد مبارك
🎁 كل عام وأنتم بخير

أتمنا لكم عيد سعيد جداً!
لتكن كل أعمالكم الخيرة مقبولة عند الله!

➧. ኢዳችሁ የደስታ ይሁን!
መልካም ስራችንን ሁሉ አሏህ ይቀበለን!

https://t.me/kunuzzza


ነገ የአረፋን ቀን ፆም ፆመው ከሚቀበላቸው ያድርገን

ነብዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የአረፋን ፆም አስመልክተው እንዲህ ብለዋል:-

የአረፋ ቀን ፆም ያለፈን የአንድ አመት ሀጥያት እና ወደፊት የሚመጣን የአንድ አመት ሀጥያት ያስምራል::


አጋር ጠፋ ብለህ ወንድሜ አትከፋ
መንገዱ ላይ ከሆንክ ሐቅ ይወጣል ይፋ


🦋 ሁሉም ነገር ተለይቶሽ  ሸሽቶሽ  እርቆሽ  ይሄዳል!  የአለማቱ ጌታ አላህ  ብቻ ካንች ጋር ይቀራል!!
ስለዚህ ከአላህ ጋር  ሁኝ
ሁሉም ነገር ካንች ጋር ይሆናል እና!!!
كُــــــن مَــــــع الله كَــما يُــــريد يَـــكُــن مَــعَك فَــوقَ مــا تُــــريد‏


☑️  የጁሙዓህ ኹጥባ
    ➖➖➖➖➖➖➖

{ የዙል ሒጃህ 10 ቀናቶች }

⤔ የዙል ሒጃህ 10 ቀናት ደረጃ
⤔ የኡዱሒያ ህግጋት በአጭሩ


🕌በወ/ዶ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ

= በድጋሜ የተለቀቀ

🎙 በአብዱረሕማን አቡ ዑሰይሚን

t.me/abuUseyminabdurehman
t.me/abuUseyminabdurehman


ተወሒድ ሲኖርህ ሁሉንም እኩል ታያለህ ከዘርህ ድንህን ታስቀድማለህ! ከተአሱብነት ትርቃለህ፣ በትዉልድ ከምታገኘው ወንድምህ በሱንና ላይ ያገኘኸውን ታስበልጣለህ።


ወደ ጠንቋይ ቤት መሄድ እና አይነቶቹ

አጭር ምክር
ሙሐመድ ሲራጅ ሙ/ኑ
https://t.me/MedrestuImamuAhmed


https://t.me/Muhammedsirage


አዝካሩ ሰባህ (የጠዋት ዚክር)

"አልሀምዱሊላህ"

ነግቶ ከተነሳሁ ከትንሿ ሞት
እድልን ካገኘሁ ዛሬም ለተውበት
ምስጋና ይገባው ለአርሹ ባለቤት
ሚስኪኒቷን ነፍሴን ህያው ላደረጋት
‼️

https://t.me/Menhaje_Aselefiy
https://t.me/Menhaje_Aselefiy


ባለቤትሽን ስለ መልካምነቱ ማመስገንሽ ፍቅራችሁን ከማጎልበቱና እሱን ለበለጠ መልካምነት ከማበረታታቱ ባሻገር አላህን ማስደሰት ነው!!

قال  صلى الله عليه وسلم : (لا ينظر الله إلى امرأة لا تشكر لزوجها و هي لا تستغني عنه) رواه النسائي و صححه الألباني في الصحيح 289

የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ «ከባሏ የማትብቃቃ ስትሆን ባሏን የማታመሰግን ሴት፣ አላህ በእዝነት አይኑ አይመለከታትም።” ኢማሙ ነሳኢ ዘግበውታል፤ አልባኒም ሰሒህ ብለውታል


ዒድ ሙባረክ !



تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال


አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ

እሄው ውዱ እና የተከበረው ወር ሊያልቅ ትንሽ ግዜ ቀሩት
ለሰራበት ሰው ሀቁንጠብቆ ለፆመው በመልካም ሲመሰክርለት
ግን ሀቁን ጠብቆ ላልፆመው እንዲሁ በመዘንጋት እና በዛዛታ ላሳለፈው ድግሞ ምስክር ይሆንበታል

ሰዎች ሆይ በዚህ በተከበረ ወር ምን እንደሰራችሁ አሰተንትኑ ይህ ወር የተከበረ እንግዳ ነው እሄው ማለቂያው ተቃርቧል እንግዳ ደግሞ አስተናገጁን በጥሩ ታስተናገደው ያመሰግናል ከዚህ በተቃራኒ ከሆነ ግን… 

አደራ ረመዷን ከሚወቅሰን እና ከሚታዘበን ሰዎች እንዳንሆን
ከወዲሁ ባለቸው ግዜ እራሳችንን ሂሳብ እናድርግ ግዚያችንን ኸይር በመስራት ከሆነ ያሳለፍነው አላህን እናመስግን ኸይር ስራችንን  እንዲቀበለንም እንለምነው የተረፈውንም በምልካም እንጨርሰው
ግን ወሩን በመዘናጋት ከሆነ ያሳለፍነው በተረፈችው ግዜ እንቶብት አላህ የቶበተኞችን ቶበት ይቀበላል 

ያለፈው አልፏል በቀረችው ትንሽ ቀን በኸይር ስራ፣በተውበት እና በስቲግፋር እንቻኮል ምናልባት አላህ እስካሆን ለተዘናጋነው ነገር ማካካሻ ሊያደርግልን ይችላል

ይህ የተከበረ ወር ቀኑ በፆም፣በዚክር፣በቁራአን እና በተለያዩ ኸይር ስራ ሌቱ በሶላት ያሸበረቀ እና የተዋበ ነበር
ግን ማንም ነገር አብረህው ብትኖር መለያየት የማይቀር ስለሆነ እሄው ረመዳንም ሊሰናበተን ቆርጦ ተነስቷል

ወዳጆቹ በመሄዱ ምክኒያት ልባቸው በሀዘን ተሞልቷል ጉንጫቸው በእንባርሷል አንገታቸውን ትጋዜው አስደፍቷቸዋል የተከበረ የተላቀ እንግዳ ሊሄድ ቆርጦ ሲነሳ እንዴትስ አይታዘን እንዴትስ አይለቀስ

ይች የተከበረችና ውድ የሆነች ሌት እና ቀን እሄው በጣም ፈጥና ተጓዘች ወይ!ቁጭታችን በዚች ሌት እና ቀን ማለቅ

በዚህች ወር በሰራው ስራ ምክኔያት አላህ የማረው፣ዱኒያ አኼራውን ያስተካከለለት እና ከእሳት ሁር ያለው ብዙ ነው
ያ አላህ ከነዚህ ውብ ባሪያዎችህ በራህመት እዝነትህ አድርገን

አላህ ይጠብቀን እና ከነዚህ የአላህ ባሪያዎች በተቃራኒ ደግሞ ቀኑን በእንቅልፍ ሌቱን በዛዛታ በማላያእኒ ያሳለፉ በፆማቸው ረሀብ እና ውሃ ጥምን ብቻ ያተረፉ ስንቶች ናቸው? 
የረመዳን ጣእምነዋን ጭራሽ ሳይቀምሷት ልታልቅ ያለች ባቸው ዝንጎዎች ብዙ ናቸው አላህ ከንደነዚህ አይነቶቹ ይጠብቀን

እንዲህ የሆናችሁት ወንድም እና እህቶች ንቁ በቀረቸው ቀን ጥፋታችሁን አስተካክሉ ወደጌታችሁ ተመለሱ

አላህ የሱን ውዴታ ካገኙት፣ የፆምን ሀቅ ጠብቀው ከፆሞት ከእሳት ሁር ከተባሉት ያድርገ  እንድሁም አድሚያችንን አርዝሞለን አሮመዳንን ደግመን ደጋግመን የምናገኘው ያድርገን አሏሁመ አሚን!
https://t.me/kunuzzza


ዘካተል ፊጥርን በተመለከተ የተነሱ ጥያቄዎች

በኡስታዝ አህመድ አደም ሀፊዘሁሏህ




التوحيد هو الإسلام:
📜

👏 የዱዓ አደቦች

ዱዓ ፈጣሪያችን አላህ(ሱወ) የምንማፀንበት፣ ሐጃችን(ጉዳያችን) አላህን በመጠየቅ የምንፈታበት የዕባዳ አይነት ነው፡፡ ይህ ትልቅ
ዕባዳ ደግሞ ለአላህ እንጂ ለማንም አይገባውም፡፡ ተናንሰን፣ ዝቅ ብለን ጉዳያችን ለሀያሉ አላህ(ሱወ) ከማቅረባችን በፊት ማሟላት
ያለብን ነጥቦች የሚከተሉ ናቸው፡-

🔖 1. ጥሪት ያለች ዱዓ ለአላህ ማድረግ (ኢኽላሱ ሊላህ)
🔖 2. አላህ በማመስገንና በማወደስ ከዛም በነቢያችን ሰለዋት በማውረድ ዱዓን መጀመር በዚሁም መጨረስ

🔖 3. ቁሪጥ ያለ ዱዓ ማድረግ፤ ተቀባይነት እንደምያገኝ ደግሞ እርግጠኛ መሆን

🔖 4. በዱዓ ችክ ማለትና ለመልሱ ግን አለመቸኮል

🔖 5. በዱዓ ቀልብን መሰብሰብ

🔖 6. በምቾትና በችግር ጊዜ ዱዓ ማድረግ

🔖 7. አላህ እንጂ ሌላን አካል ላይለምን

🔖 8. በቤተሰቡ፣ በልጁ፣ በገንዘቡ፣ በራሱ ላይ ዱዓ እንዳያደርግ

🔖 9. ድምፅን ዝቅ አድርጎ ዱዓ ማድረግ

🔖 10. በሰራው ወንጀል አምኖ መሃርታ(ይቅርታ) መጠየቅ፤ አላህ የዋለለትን ፀጋ አምኖ ምስጋና ማድረስ

🔖 11. በዱዓ ላይ መተናነስ፣ መፍራት፣ መከጀል በልባችን ላይ ማሳደር ...

🔖 12. የተጣሉ (የተበዳደሉ) በማስታረቅ ወደ አላህ መመለስ

🔖 13. ሶስት(3) ጊዜ መደጋገም

🔖 14. ወደ ቅብላ አቅጣጫ መዞር

🔖 15. ዱዓ በሚያደርግበት ጊዜ የመዳፍ እጅ ወደላይ ማንሳት(ከፍ ማድረግ)

🔖 16. ከዱዓ በፊት ውዱእ ማድረግ

🔖 17. በዱዓ ድንበር አለማለፍ

🔖 18. ዱዓ ስጀምር ከነፍሱ(ከራሱ) መጀመር

🔖 19. በመልካም ስሞቹና መልካም ባህሪያቶቹ፣ በመልካም ስራው ወደ አላህ መቃረብ

🔖 20. እምበላው፣ እምጠጣውና እምለብሰው ከሐላል መሆኑን

🔖 21. ወንጀል ለመፈፀም ወይም ዝምድና ለማቋረጥ ተብሎ ዱዓ
አለማድረግ

🔖 22. በኸይር ማዘዝና ከመጥፎ ነገር መከልከል

🔖 23. ከወንጀል መራቅ

🔖 24. ዱዓ ተቀባይነት ይኖረዋል የተባለባቸውን ሰዐቶችና ቦታዎች መምረጥ ሲሆን እነሱም ብዙ ናቸው፡፡

ከሌሎች ጊዚያ የበለጠ ዱአችን ተቀባይ የሚሆኑባቸው ግዝያቶች
🔹- እኩለለሊት
🔹- አዛን ሲደረግ
🔹- በአዛንና በኢቃም መካከል ባለችው ጊዜ
🔹- በሶላት ወቅት
🔹- በሱጁድ ወቅት
🔹- በጁም አቀን(ከሰላተል ዓስር በኃላ)
🔹- በረመዷን በተለይ በለይለቱል ቀድር
🔹- ውዱእ ካደረጉ ቡኋላ
🔹- የዘምዘም ውሃ ከመጠጣት በፊት
🔹- በሐጅ ወቅት በተለይ በአረፋ ቀን
🔹- ዝናብ ሲጥል

አላህ ዱአችንን ይቀበለን።

┄┄┉┉✽‌»‌🌹✿🌹»‌✽‌┉┉┄┄
   ሼር 👇JoiN👇 & Share


ጡባ ሊል ጉረባእ የሰለፍዮች መድረሳ በሀበሻ ቻናል
https://t.me/tubaliligurebae
https://t.me/tubaliligurebae
قال ابن تيمية رحمه الله:
ولا يحل لأحد أن يتكلم في الدين بلا علم، ولا يعين من تكلم فيه


Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ዘካ የሚሰጠው ለምን አይነት ሰው ነው?
~
ዘካ የሚገባለሐቆች 8 ናቸው። በቁርኣን እንዲህ ተዘርዝረዋል:–

(إِنَّمَا الصَّدَقَاتُ لِلْفُقَرَاءِ وَالْمَسَاكِينِ وَالْعَامِلِينَ عَلَيْهَا وَالْمُؤَلَّفَةِ قُلُوبُهُمْ وَفِي الرِّقَابِ وَالْغَارِمِينَ وَفِي سَبِيلِ اللَّهِ وَابْنِ السَّبِيلِ ۖ فَرِيضَةً مِنَ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌ)

"ግዴታ ምጽዋቶች (የሚስሰጡት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሰራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱ፣ ጫንቃዎችንም (በባርነት ተገዢዎችን) ነፃ በማውጣት፣ በባለ እዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ በመንገደኛም ብቻ ነው፡፡ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፡፡ አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡" [አተውባህ: 60]

መጠነኛ ማብራሪያ

① ድሃ ማለት:– ለመኖር (ልብሱ፣ ጉርሱ፣ ትዳር ለመመስረት፣ ለመማር፣) ምንም ነገር የሌለው ወይም ትንሽ ነገር ያለው ማለት ነው። እነዚህን ፍላጎቶች ለማሟላት ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
② ምስኪን ማለት: – ለመኖር የሚሆን ነገር በተወሰነ መጠን ያለው ሲሆን የሚበቃው ግን አይደለም።
③ ዘካ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች:– ዘካ እንዲሰበስቡ በመሪ የሚላኩ ሰዎች ናቸው። ዘካ ሶስት ነገሮችን ይፈልጋል። መሰብሰብ፣ መጠብበቅና ማከፋፈል። በሶስቱም ዘርፍ ላይ የሚሰማሩ ሰራተኞች ሃብታም ቢሆኑ እንኳ ዘካ ይሰጣቸዋል።
ልብ በሉ! ለዚሁ ስራ በመንግስት የሚሾሙትን እንጂ የግለሰቦች ወኪሎችን አይመለከትም። ደሞዝተኛ ሰራተኛም እዚህ ውስጥ አይገባም።

④ ልቦቻቸው (በእስልምና) የሚለማመዱ የተባሉት ሁለት አይነት ናቸው።

አንደኛ፡- ሙስሊም ያልሆነ ሰው ነው። ሙስሊም ባይሆንም ለተሻጋሪ ፋይዳ ሲባል ነው ሊሰጠው የተፈቀደው።
– ቢሰጠው ይሰልማል ወይም ሌላ ፋይዳ ይገኝበታል ተብሎ ተስፋ የሚጣልበት ከሆነ፣
– የሚያደርሰው ጉዳት ኖሮ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ

ሁለተኛ፡- ሰለምቴ ነው።
– በዲኑ እንዲጠነክር ወይም ለሌላ ሰው መስለም/ መጠንከር ሰበብ ይሆናል ተብሎ ከተገመተ፣
– በሙስሊሞች ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ በዚህ ማስቆም የሚቻል ከሆነ። [መጅሙዑል ፈታዋ፣ ኢብኑ ተይሚያ: 28/290]

⑤ እራሳቸውን ከአሳዳሪዎቻቸው በመግዛት ነፃ ለማውጣት የሚጣጣሩ ባሪያዎች ዘካ ከሚገባቸው ናቸው።

የታገቱ/ የተማረኩ ሙስሊሞችን ማስለቀቅም ከዚሁ ውስጥ ይካተታል።

⑥ ባለ እዳ:– የተጣልሉ ሰዎችን ለማስታረቅ አስቦ እዳ የገባ ሰው ሃብታም እንኳን ቢሆን ዘካ ሊሰጠው ይችላል።
በራሱ ጉዳይ እዳ የተጫነው ከሆነ በኑሮው ባይቸገር እንኳ እዳውን ለመክፈል ሊሰጠው ይችላል።
⑦ በአላህ መንገድ የሚሰራ ማለት:– ለጂሃድ ዘማች ማለት ነው። ለትጥቅ፣ ለስንቅና አጠቃላይ ዝግጅት ዘካ ይሰጣል።
⑧ መንገደኛ:– አገሩ መግቢያ ከዘካ ገንዘብ ይሰጠዋል።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 26/2013)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


የኛ ነገር ... ከሐላል እየፆምን በሐራም እናፈጥራለን!
~
ፆማችንን ከሐራም ነገሮች እንጠብቅ። ግብይታችን በየትኛውም መልኩ ከሰው ሐቅ ጋር እንዳይነካካ እንጠንቀቅ። አይናችንን ካልተፈቀደ አካል እንስበር። ስልኮቻችንን ወደ ሐራም እንዳያደርሱን እንቆጣጠር። በረመዷን ከሰው ጋር ያለንን ቅልቅል እንቀንስ። በተለይ ደግሞ የምላሳችንን ነገር እናስብበት። ፆማችን አጉል መርራብ እና መጥጠማት እንዳይሆን እንጠንቀቅ።
ታላቁ ታቢዒይ የሐያ ብኑ አቢ ከሢር ረሒመሁላህ ፆመኛ ሆኖ ሃሜትና ነገር ማሳበቅ ላይ ስለሚሰማራ አካል እንዲህ ይላሉ፦
"ሰው ንፁህ ከሆነ ሐላል (ምግብና መጠጥ) እየፆመ ቆሻሻ በሆነ ሐራም - በወንድሙ ስጋ - (በሃሜትና ነገር ማሳበቅ) ያፈጥራል።"
ምንጭ ፦ [አልሒልያህ፣ አቡ ኑዐይም፡ 3/69]

#ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Shaikh Mohammed Zeyn Adem Asalfi(hafizahu Allah) Official channel
ጨረቃ ታየች
‏عاجل:

‏رؤية هلال رمضان في سدير..
‏وغدا الإثنين أول أيام رمضان بالسعودية إن شاء الله .
በሱኡዲያ እና ተመሳሳይ ሀገሮች ነገ ሰኞ የመጀመሪያው የረመዳን ቀን ይሆናል።
ኢን ሻአ አላህ።

20 last posts shown.

819

subscribers
Channel statistics