ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተጠናቀቀ በ48 ሰዓታት ውስጥ ተጠርጣሪዎችን ችሎት ላለማቅረቡ አሳማኝና በቂ ምክንያት ሳያቀርብ መቅረቱ ተሰማ፡፡
አሻም ዜና | ሰኔ 3 ቀን 2016 ዓ.ም
ከሦስት ወራት በላይ በአዋሽ አርባ ታስረው የቆዩት ተጠርጣሪዎች በዛሬው ዕለት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹን መርማሪ ፖሊስ ሊያቀርባቸው ይገባ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በተጠናቀቀ 48 ሰዓታት ውስጥ መሆኑን ከጠበቆቹ አንደኛው ለአሻም ነግረዋታል፡፡
መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ለምን በ48 ሰዓታት ውስጥ ሳያቀርብ እንደቀረ ለተጠየቀው በሰጠው ምላሽ የመንገዱን ርዝመት መሆኑን አስረድቷል፡፡ ይሁንና ከተጠርጣሪዎች ጠበቃ በኩል ከአዋሽ አርባ አዲስ አበባ ለመድረስ የሚወስደው ጊዜ አንድ ቀን ብቻ ቢሆንም ተጠርጣሪዎቹ ግን ችሎት የቀረቡት በዛሬው ዕለት መሆኑን ጠቅሰው ምክንያቱ አሳማኝ እንዳልሆነ ተከራክረዋል፡፡
የግራ ቀኙን ያዳመጠው የአራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርምሮ ብይን ለመስጠት ለነገ በስቲያ ሰኔ 5 ቀን 2016 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
አሻም ለኢትዮጵያችን!!