እናት ፓርቲ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ከሰስኩ ባለው የክስ አቤቱታ መርታቱን አሳወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ/የንብረት ግብር ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ያለው ግብር "ሕገ ወጥ መኾኑን" በመግለጽ እናት ፓርቲ ክስ መመሥረቱን አስታዉሶ ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት ዛሬ ጥር 9ቀን 2017 ዓ.ም.ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ ሚያዝያ 3ቀን 2015 ዓ.ም. የወጣውና "ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ ወስኖልኛል ሲል በማህበራዊ ገፁ አስታውቋል::