ብቸኛው የዓይነ ሥውራን ቤተ መጻሕፍት የፍርድ ቤት ዕግድ ተጥሶ መፍረሱ ተነገረ
***
ከ50 ዓመታት በላይ ያስቆጠረውና ብቸኛው የዓይነ ሥውራን ቤተ መጻሕፍት በወንዝ ዳርቻ ልማት እንዳይፈርስ የሚል የፍርድ ቤት ውሳኔ ቢተላለፍበትም በኃይል መፍረሱን የአካል ጉዳተኞች ማኅበር አስታወቀ፡፡
ቤተ መጻሕፍቱን ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የሚወጡ ዓይነ ሥውራን በብቸኝነት ይገለገሉበት እንደነበር፣ የአዲስ አበባ አካል ጉዳተኞች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ገለታው ሙሉ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር ችሎት ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በዋለው ችሎት ከ50 ዓመታት በላይ ለዓይነ ሥውራን በማገልገል ላይ ያለው ቤተ መጻሕፍት ምትክ ሳይሰጠው እንዳይፈርስ ዕግድ የጣለ ቢሆንም፣ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን በመጣስ መፍረሱን አቶ ገለታው ተናግረዋል፡፡
ከፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ፍትሐ ብሔር 2ኛ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነት ችሎት ባስተላለፈው ፍርድ ላይ እንደተመለከተ፣ የኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ብሔራዊ ማኅበርና የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያዎች አካል ጉዳተኞች ማኅበር አንደኛና ሁለተኛ ከሳሽ ሆነው የቀረቡ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጉለሌ ክፍለ ከተማ መሬት ልማት አስተዳደር ጽሕፈት ቤት እንዲሁም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ተከሳሾች ሆነው መቅረባቸውን በመጥቀስ መዝገቡን መርምሮ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉን ሰነዶች ያስረዳሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኝ ከ1967 ዓ.ም. በፊት ጀምሮ ለዓይነ ሥውራን ሲሰጥ የነበረና በበጎ አድራጎት ድርጅቶች የተመሠረተ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ብቸኛ ዓይነ ሥውራን የሚያነቧቸው የተለያዩ የብሬል መጻሕፈት የሚገኙበትና ዓይነ ሥውራን የሚያነቡበት የእስክሪን አንባቢ ሶፍትዌር የተጫነባቸው ኮምፒዩተሮች፣ የዲጂታል ቤተ መጻሕፍት እንዲሁም የቀለም ጽሑፍ የሚያነቡበት በአጠቃላይ ለዓይነ ሥውራን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም መሆኑን ችሎቱ በሰጠው ብይን ላይ ተመላክቷል፡፡
ይህም በሕገ መንግሥቱ ለአካል ጉዳተኞች የሚደረግ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች ጥበቃ መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን በማስቀመጥ፣ ይህ ቤተ መጻሕፍትና የብሬል ማዕከል የሚያገለግልበት ቤትና ይዞታ በተጠሪዎች በተያዘው በወንዝ ዳር ልማት ሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ሥራ ለማዋል፣ የማዕከሉን ቦታና ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚፈርስ መሆኑን የጉለሌ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ደብዳቤ መጻፉን የፍርድ ወረቀቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
ነገር ግን ተግባሩ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 4 ላይ የተቀመጡ ጥበቃ የተደረገላቸው የትምህርት መረጃ የማግኘትና ተደራሽ አገልግሎት የማግኘት መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶችን የሚጥስ መሆኑን ይገልጻል፡፡
ከሳሾች የዓይነ ሥውራን ጉዳይ ለወንዝ ዳር ልማት ልዩ ሁኔታ ሊሆን አይችልም ብሎ ፍርድ ቤቱ፣ ቤተ መጻሕፍቱ እንዳይፈርስ ወይም ከመፍረሱ ቀደም ብሎ በአቅራቢያው ተመጣጣኝ የሆነ ቤተ መጻሕፍት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡ ከሳሾች በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ዓይቶ የመወሰን ሥልጣን የለውም የሚል መሆኑ የተመለከተ ሲሆን፣ ቦታውን መንግሥት ለልማት ከፈለገው ምትክ ቦታ መስጠት እንዲችል የይዞታው ባለቤት ስለመሆናቸው ማስረጃ ሊያቀርቡ እንደሚገባ የጠየቀ ሲሆን፣ ከሳሾች የይዞታ ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ እንዳልቻሉ ተመላክቷል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የሚገኝ በክርክሩ የተመለከተውን የዓይነ ሥውራን የቤተ መጻሕፍትና ተያያዥ አገልግሎቶችን፣ ለዓይነ ሥውራን የሚሰጠውን ቦታና ይዞታ ማፍረስ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 እና 41 (4)፣ (5) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞች ስምምነት አንቀጽ 9፣ 21 እና 24 ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተረጋገጠውን የመማር፣ መረጃ የማግኘትና ተደራሽ አገልግሎት የማግኘት መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች የሚጥስ ስለሆነ፣ በልዩ ሁኔታ ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ መጻሕፍት በአቅራቢያው ሳይዘጋጅ ሊፈርስ አይገባም በማለት አዋጅ 1234/13 አንቀጽ 11(3) መሠረት ወስነናል›› ሲል በፍርዱ ያስቀመጠ መሆኑን ለማየት ተችሏል፡፡
ይሁን እንጂ ይህንን ውሳኔ በመተላለፉ ቤተ መጻሕፍቱ መፍረሱን አቶ ገለታው ተናግረዋል፡፡ ቤተ መጻሕፍቱ በአገሪቱ ብቸኛና ምትክ የሌለው መሆኑን ጠቅሰው መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡#reporter