የቴምብር ቀረጥን በተመለከተ ፓርላማው ያወጣው ህግ በህግ አስፈጻሚው ህግ-በመተርጎም ሰበብ እንዲቀየር ሆኗል፡፡ግልጽ ህግ ግን ለትርጉም አይቀርብም!!
#Birhanu Beyene
- ከህግ አተረጓጎም መርኾች አንዱ "ህግ ግልጽ ከሆነ አይተረጎምም" የሚል ነው፡፡ በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሰረት የዋስትና መበት አዋጅ ቁ. 1147/2011 አንቀጽ 89 እንዲህ ይነበባል፡- "በዚህ አዋጅ መሰረት የዋስትና መብትን ለመመስረት የሚደረግ ስምምነት ወይም ግብይት ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ነው፡፡"
- ይህ ድንጋጌ ግልጽ ስለሆነ ሊተረጎም አይገባም ፡፡ ይሁንእንጂ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር በቀን 16/8/2015 በተጻፈ ሰርኮላር ከኢንቨስተርሮች ፣ ኤክስፖርተሮች እና ምናልባትም ነጋዴዎች በቀር ሌሎች ሰዎች በአዋጁ መሰረት የመያዣ ውል ቢገቡም የቴምብር ቀረጥ መክፈል አለባቸው ብሏል፡፡ ይህ ግልጽ ህግ መተርጎም ግን አዲስ ህግ እንደማውጣት ነው( ህግ የማውጣት ስልጣን ደግሞ የፓርላማው ነው፣የገንዘብ ሚኒስቴርን አይደለም፡፡)
- በመሆኑም አንድ ነጋዴም፣ ኢንቨስተርም ፣ ኤክስፖርተረም ያልሆነ ተጠቃሚ(consumer) ወይም በግብርና የሚተዳደር ግለሰብ(የሚያበድረው ካገኘ 😁 ) መኪና በብድር ቢገዛ እና አበዳሪው መኪናዋን በመያዣ ቢይዝ የቴምበር ቀረጥ የመኪናውን ዋጋ 1% እንዲከፍል እየተደረገ ነው፡፡ በተንቀሳቃሽ ንብረት ላይ የሚመሰረት የዋስትና መበት አዋጅ ቁ. 1147/2011 አንቀጽ 89 ግን በግልጽ ቋንቋ "በዚህ አዋጅ መሰረት የዋስትና መብትን ለመመስረት የሚደረግ ስምምነት ወይም ግብይት ከቴምብር ቀረጥ ነጻ ነው፡፡" ሲል ያስቀምጣል፡፡ ህጉ የዚህ ድንጋጌ ተፈጻሚነት ለነጋዴ፣ ኢንቨስተር እና ኤክስፖርተር ብቻ ነው የሚል ገደብ የለውም።