"የኮንዶሚንየም ቤት ዕድለኛ በሞተ ጊዜ ሟች አስቀድሞ ለቤቱ ሲመዘገብ ዕድሜያቸው 18 ሞልቷቸው የነበር የሟች ልጆች በሟች ስም የወጣውን ዕጣ አይወርሱም" በሚል የሚደነግገው የአ/አ/ከ/አስ. 'የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎችና ለልማት ተነሺዎች ለማስተላለፍ የወጣው መመሪያ ቁ. 1/2008 አንቀጽ 44' በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 40(1, 2) የተደነገገውን ዜጎች የግል ንብረታቸውን ማውረስን ጨምሮ ያላቸውን ሙሉ የባለቤትነት መብት የሚጥስ እንዲሁም በወራሾች መካከል የዕድሜ ልዩነት በመፍጠር በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 25 የተሰጣቸውን በሕግ እኩል ጥበቃ የማግኘት መብት የሚሸራርፍ በመሆኑ ተፈጻሚነት የለውም" በማለት የፌደሬሽን ም/ቤት የሰጠው የሕገ መንግሥት ትርጉም ውሳኔ::👴🏽
-የፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 76/11- መስከረም 27/2012 👴🏽
-የፌደሬሽን ም/ቤት መ/ቁ. 76/11- መስከረም 27/2012 👴🏽