አቶ አብዲ ሙዲን ይባላሉ የነቀምት ከተማ ነዋሪ ሲሆኑ በአነስተኛ ንግድ ስራ ይተዳደራሉ ፡፡ ከስራቸው ጎን ለጎን አልፎ አልፎ ሎተሪን የመቁረጥ ልምድ ያለቸው ሲሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አድማስ ዲጂታል ሎተሪን አዘውትረው ይቆርጣሉ ፡፡ ሎተሪውን ከመውደዴና አንድ ቀን ይመጣል በሚል ተስፋ በ28ኛው ዙር አድማስ ሎተሪ ላይ 31 ጊዜ ቆርጫለሁ ይላሉ አቶ አብዲ ፡፡ ከ31 የዕድል ቁጥሮችም አንዷ የዕድል ቁጥር መልካም ዜና ይዛ መጣች እና ዕድልኛ ስላደረገቻቸው በ1ኛ ዕጣ የ4 ሚሊየን ብር ቼካቸውን ተረክበዋል ፡፡ በደረሳቸውም ገንዘብ የንግድ ስራቸውን እንደሚያስፋፉበት ገልጸውልናል ፡፡