10 ሚሊዮን ብር ለሁለት ጓደኛሞች!
ጓደኛሞቹ የገና ስጦታ ሎተሪን የ1ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብሩን ለሁለት ተካፍለውታል፡፡
ጓደኛሞቹ ገደፋው ከበደ እና ሙላቱ መንግስቴ በስራ ቦታቸው አካባቢ ካዛንችስ ብዙውን ጊዜ ቁርስ በሚበሉበት ምግብ ቤት ቁርስ እየበሉ ሎተሪ አዟሪ ወዳሉበት ይመጣል፡፡
ሙላቱ መንግስቴ ለረጅም አመታት የሎተሪ ደንበኛ ሲሆን ገደፋው ሎተሪ አልፎ አልፎ እንደሚቆርጥ ይናገራል፡፡ ሙላቱ በኪሱ ያለው 20 ብር ብቻ በመሆኑ የገና ስጦታ ሎተሪ አንድ ትኬት ብቻ ገዝቶ የተቀሩትን ሁለት ትኬቶች ጓደኛውን ቁረጥ ይለዋል፡፡ ገደፋው እያንገራገረ 40 ብር ከፍሎ ሁለቱን ትኬት ይወስዳል፡፡
የገና ስጦታ ሎተሪ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ሲወጣ ገደፋው ከበደ በሁለቱ ትኬት የ6.66 ሚሊዮን ብር፣ ሙላቱ መንግስቴ በአንድ ትኬት የ3.33 ሚሊዮን ብር እድለኛ ሆነዋል፡፡ ገደፋው ከበደ ህንፃ በሚገነባበት አንድ ጥግ ቦታ በምትገኝ አነስተኛ የሽሮ ቤት የሚተዳደር ሲሆን ሙላቱ መንግስቴ በጎዳና እየተዘዋወረ መጽሐፍ ይሸጣል፡፡
ጓደኛሞቹ የደረሳቸውን ገንዘብ በምን ስራ ላይ እንደሚያውሉት ለጊዜው እንዳላቀዱ፤ሆኖም ተመካክረን የኛንና የቤተሰብን ህይወት የሚለውጥ ስራ እንጀምራለን ብለዋል፡፡
መልካም የስራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ይህን ሊንክ ይጫኑ፡ https://linktr.ee/etiopianlotteryservice