#ኢየሱስ_የእድሜ_ልክ_ወዳጅ
✨#በሁኔታዎች_ላይ_ያልተመሰረተ_ፍቅር_ያለው_ኢየሱስ_ብቻ_ነው። ምድራዊ ወዳጅነቶች ሁኔታ የጀመራቸው ሁኔታ የሚገድባቸው ናቸው። ዛሬ ሰው ከእኛ ጋር ሊሆን ይችላል ነገ ደግሞ ሊርቅ ይችላል። ዛሬ ሊረዳን ይችላል ነገ ግን አቅሙ ሊያልቅ ይችላል። ኢየሱስ ግን ከዚህ የተለየ ወዳጅ ነው።
✨#ብዙ_ሰው_ወዳጄ_በሚለው_ሰው_ተፈትኗል_ልቡም_ተሰብሯል። ትላንት በችግሩ የቆማችሁለት፣ ብርቱ ፈተናውን የተካፈላችሁት ሰው በእናንተ የሀዘን ሰዓት ጎናችሁ ላይሆን፣ በእናንተ የፈተና ወቅት ፈተናው ከጎዳችሁ በላይ ወዳጄ ያላችሁት የጎዳችሁ ይበልጣል። በቃ ከእንግዲህ ሰው አያስፈልገኝም እንዳትሉ ሰው የሆነው ኢየሱስ አለ። እርሱ በሐዘናችሁ አብሯችሁ ነው፤ ስትከብሩ የሚፈልጋችሁ ስትዋረዱ የሚጥላችሁ አይደለም። ማንም ሳይረዳችሁ ሁሉ ጀርባ ሲሰጣችሁ በሙሉ ፍቅሩ ከእናንተ ጋር የሚሆነው ኢየሱስ ነው።
✨ወዳጄ ያላችሁት ስትወድቁ እንዳላየ ያልፋችኋል ኢየሱስ ግን እጁን ይዘረጋላችኋል። ችግራችሁ ወዳጅ ሲያርቅባችሁ ኢየሱስ ግን በችግራችሁ ጊዜ ወደእናንተ ይመጣል።
ብሎናል። ስለዚህ ልባችን ሲሰበር፣ መንገድ ሲጨልም፣ እንባችን ሲፈስ ማንም የለኝም አትበሉ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ነው።
✨ኢየሱስ ወዳጅ የሆነን ማንም በእርሱ ልክ ወዳጅ እንደማይሆንልን፣ ማንም ሊወደን በማይችል ማንነት ወዶን፣ ሁልጊዜ አጥፊ፣ የስህተቶች መነኻሪያ መሆናችንን እያወቀ፣ ከነ ጉዳችን ከነችግራችን አብሮን ሊሆን የወደደ ወዳጃችን ነው።
✨#እድሜ_ልክ_የፈረመ_ወዳጅ_የላችሁም። ባሻው ሰዓት ከሕይወታችሁ ለመውጣት በጨረታው አይገደድም። ኢየሱስ ብቻ ከመቃብር ባሻገር፣ ከሞትም ባለፈ፣ ከዘመናትም ተሻግሮ ለዘላለም የተወዳጀን ወዳጅ ነው።
✨ምድራዊ ወዳጆቻችሁን አትግፉ ሕይወታችሁ ላይ አሻራ ያሳረፉትን አትግፉ እንዲህ አይነት ወዳጅ ባይኖራችሁ እንኳን ከወዳጅ በላይ የሆነ ወዳጅ ኢየሱስ እንዳለ አትርሱ። ደስ ብሏችሁ ዋሉ።
@lovedbychrist

" እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ"