የእግዚአብሔር ፀጋ (God's Grace)


Channel's geo and language: Ethiopia, English


“ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤”
— ቲቶ 2፥11

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Statistics
Posts filter




መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20:15 (AMH)
••••••••••
¹⁵ እንዲህም አለ። ይሁዳ ሁሉ፥ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ፥ አንተም ንጉሡ ኢዮሣፍጥ፥ ስሙ፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል። ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተነሣ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።

@lovedbychrist
@lovedbychrist


ሰሞኑን ሮሜ መፅሐፍ እያጠናሁ ነውና የገረመኝን ላካፍላችሁ
👇👇👇

ይህ የሮሜ ሰዎች 4፡20 ጥቅስ፣ የአብርሃምን እምነት ጥራት እና ከእግዚአብሔር ጋር የነበረውን ጥልቅ ግንኙነት የሚገልጽ ድንቅ ክፍል ነው። አብርሃም "የእምነት አባት" የተባለበትን ምስጢር በዚህ ጥቅስ ውስጥ ማየት እንችላለን።

ይህንን ጥቅስ ስንመረምረው አራት ዋና ዋና የእምነት መርሆችን እናገኛለን፡

1. ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት
እምነት ማለት ለችግሩ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ታላቅነት ትኩረት መስጠት ነው። አብርሃም የገጠመውን ሁኔታ (የገዛ ሰውነቱን መሞት እና የሣራን ማህፀን መዘጋት) እያሰበ አልተጨነቀም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር "የተናገረውን የመፈጸም ችሎታ" (Omnipotence) በማሰብ ለእግዚአብሔር ክብር ሰጠ። እኛም በፈተና ውስጥ ስንሆን ለእግዚአብሔር ክብር መስጠትን ስንለማመድ፣ ችግሮቻችን በእግዚአብሔር ፊት ምን ያህል ትንንሽ እንደሆኑ እንረዳለን።

2. ስለ ተስፋው ቃል "አጥብቆ መረዳት" (Full Persuasion)
አብርሃም "በጥርጣሬ" እና "በእርግጠኝነት" መካከል ሲመላለስ አልነበረም። "አጥብቆ እየተረዳ" የሚለው ቃል እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ሙሉ በሙሉ እንደ እውነት መቀበልን ያሳያል። እምነት ማለት ስሜታችንን ወይም ሁኔታዎችን ሳይሆን፣ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ መጨረሻ ባለስልጣን መውሰድ ነው። እግዚአብሔር ተናግሯል፤ ስለዚህ ይሆናል ብሎ ማመን ነው።

3. አለማመንን አለመቀበል
ጥቅሱ "በአለማመን ምክንያት... አልተጠራጠረም" ይላል። ይህ ማለት ፈተና አልነበረውም ማለት አይደለም፤ ነገር ግን ፈተናው ሲመጣ በአለማመን ላይ "አልቆመበትም"። ጥርጣሬ ሊመጣ ይችላል፣ ነገር ግን በእምነት የጸና ሰው በጥርጣሬ ውስጥ አይኖርም። አብርሃም ሁኔታውን ተመልክቶ ጥርጣሬውን በመተው፣ በእግዚአብሔር ተስፋ ላይ ራሱን አረጋጋ።

4. በእምነት መበርታት (Growing in Faith)
አብርሃም በእምነት "በረታ"። እምነት አንድ ጊዜ ብቻ የሚደረግ ሳይሆን፣ እያደገ የሚሄድ ጉዞ ነው። እግዚአብሔርን ይበልጥ ባወቅን እና የተስፋውን ቃል ባሰብን ቁጥር፣ በእምነት እንበረታለን።

---

### ከዚህ ጥቅስ ለህይወታችን የምንወስደው ትምህርት፦


#ተስፋን_በችግር_ላይ_መትከል፦ በአብርሃም ዙሪያ የነበሩት ነገሮች ሁሉ "የማይቻል" በሚመስሉበት ወቅት ነው እምነቱ የጎላው። የምትጠብቀው ተስፋ ዘግይቷል? ወይስ የማይቻል መስሎ ይታይሃል? አብርሃም እንዳደረገው ሁኔታውን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል ተመልከት።

#የማመስገን_ሃይል፦ "ለእግዚአብሔር ክብር እየሰጠ" የሚለው ቃል የሚያሳየው፣ አብርሃም ተስፋው ገና ሳይፈጸም ማመስገን እንደጀመረ ነው። ምስጋና የእምነት መገለጫ ነው። ገና ሳይታይ እንደታየ አድርጎ ማመን ነው።

#አለመጠራጠር፦ የሰው ልጅ ተፈጥሮ ማየት ይፈልጋል፤ ነገር ግን እምነት "ያልታየውን" እንደታየ መቁጠር ነው። ዛሬ የምትጠራጠረው ነገር ካለ፣ አብርሃም እንደተረዳው እግዚአብሔር የተናገረውን የመፈጸም ችሎታ እንዳለው እመን።
@lovedbychrist
@lovedbychrist


መኖር መብት አይደለም የእግዚአብሔር ምህረት እንጂ!!

#መልካም_ሰንበት
@lovedbychrist
@lovedbychrist


#ክፉ_ሀሳብ! የሚውልበት አእምሮ #የሀጢአት_ቢሮ_ነው
እግራችን ለጥፋት እንዳይፈጥን በሀሳባችን እንቀደስ።

መልካም ምሽት
@lovedbychrist
@lovedbychrist




አልተጋነነም
ድንቅ አምልኮ
ዘማሪ አዲሱ ተረፈ
Kingdom Sound
@lovedbychrist
@lovedbychrist


#እንዲህ_ፀለይኩላችሁ።🙌

የህይወታችሁ እስራት ይበጠስ ።
የአመታት ፍርሃታችሁ እንደሰም ይቅለጥ።
የተቆለፈባችሁ የውድቀት በር በታላቅ ድምፅ
ተነቅሎ ይውደቅ ።
ትላንት በእግራችሁ ላይ የነበረ ሰንሰለት ዛሬ ለድላችሁ መረገጫ ይሁንላችሁ ።
ከጥላቻ እስር ከጭንቀት ግዛት ከሽንፈት አዙሪት ከዚህ ሰአት ጀምሮ ነፃ ሁኑ ።
አድማስን የሚቀድ ክንፍ ይሰጣችሁ
የተሸሸገው ብርሃናችሁ ለአለም ይብራ ።
እግዚአብሔር እንደባለስልጣን የምታዙበት እንደባለቤት የምትጠይቁበት የመረዳት ኃይል ውስጥ ያስገባችሁ ።

@lovedbychrist
@lovedbychrist


#እግዚአብሔር_ይመስገን!


ሰላም እንዴት ናችሁ? ዛሬ ረጅም መንገድ ተጉዤ እና በዛ በምጓዝበት ጊዜ በብዙ ሀሳብ ተውጬ ነበር እና ልክ ስደርስ መዳረሻዬ ጋር ስልኬን ከፍቼ እያየሁኝ ይሄን መዝሙር አየሁና መስማት ጀመርኩኝ። እና ለኔ እንደ መልእክትም ሆነልኝ። የእውነት ወዳጆቼ እግዚአብሔር ያየናል፣ እግዚአብሔር ያየናል ተባረኩ።
በዚህ ድንቅ መዝሙር ተባረኩበት።


አይዞህ!! ያይሀል!
ድንቅ መዝሙር
ዘማሪ አቤኔዘር ታገሰ
@lovedbychrist
@lovedbychrist


እግዚአብሄር መልካም ነው የሚል #ስብከትና እግዚአብሔር መልካም ነው የሚል #ህይወት በቃል ኪዳን ተጣምረው ሲኖሩ ውበታቸው ብቻ ሳይሆን የህይወት ፍሬያቸው እጅግ ያስቀናል:: አፍ አውጥቶ እያወራ ብዙዎችን ይማርካል:: ለዘመን ተድላን ለዕድሜም ልማትን ይጨምራል::

@lovedbychrist
@lovedbychrist


በወሳኝ ጊዜ መኖራቸው በሚያስፈልጋችሁ ሰአት የቅርብ ያላችኋቸው ወይም አይን የጣላችሁባቸው ሰዎች ዞር ሲሉ ፣ የጠበቃችሁባቸውን ነገር ለመወጣት ባልተገኙላችሁ ባልረዷችሁ ጊዜ ከማዘን ይልቅ እንዲ አስቡ!!!! ፈፅሞ ነገራችሁ ከምትወዷቸው ከሚወዷችሁ ከቅርብ ከሩቅ ወዳጆችችሁ ጋር የተያያዘ አይደለም ።#ማድረግ #እየፈለጉ እግዚአብሔር #አልፈቀደላቸው እንደሆነስ? ከሀሳባቸው ዘወር አድርጓችሁ እንደሆነስ ? በእርሱ ላይ #እንድትተማመኑና #እንድትደገፉ እያመቻቻችሁ ከሆነስ?#አይናችሁን #ከሰው ላይ አንሱና የእርሱ ፈቃድ ብቻ በህይወታችሁ እንዲከናወን አብዝታችሁ ወደ እርሱ ቅረቡ
መድሀኒት ከእርሱ ዘንድ ብቻ ነው። እርሱ የከፈተውን ማንም አይዘጋውም የዘጋውን ማንም አይከፍተውም ።
#ነገራችሁን_ከሰው_ደጅ_አትጠብቁ

@lovedbychrist
@lovedbychrist


የኔ ፈጥኖ ደራሽ ሳዝንም አጽናኜ
ስወድቅ የሚያነሳኝ አለው ባይ መድኔ
ድጋፌ ሆነልኝ አፍቃሪ ወዳጄ
#ጌታ_ኢየሱስ_ነው_ረዳት_ዘመዴ

"
#የምድረበዳ_ወዳጅ_የኔ_ኢየሱስ🥺🥰


#ኢየሱስ_የእድሜ_ልክ_ወዳጅ

#በሁኔታዎች_ላይ_ያልተመሰረተ_ፍቅር_ያለው_ኢየሱስ_ብቻ_ነው። ምድራዊ ወዳጅነቶች ሁኔታ የጀመራቸው ሁኔታ የሚገድባቸው ናቸው። ዛሬ ሰው ከእኛ ጋር ሊሆን ይችላል ነገ ደግሞ ሊርቅ ይችላል። ዛሬ ሊረዳን ይችላል ነገ ግን አቅሙ ሊያልቅ ይችላል። ኢየሱስ ግን ከዚህ የተለየ ወዳጅ ነው።

           ✨
#ብዙ_ሰው_ወዳጄ_በሚለው_ሰው_ተፈትኗል_ልቡም_ተሰብሯል። ትላንት በችግሩ የቆማችሁለት፣ ብርቱ ፈተናውን የተካፈላችሁት ሰው በእናንተ የሀዘን ሰዓት ጎናችሁ ላይሆን፣ በእናንተ የፈተና ወቅት ፈተናው ከጎዳችሁ በላይ ወዳጄ ያላችሁት የጎዳችሁ ይበልጣል። በቃ ከእንግዲህ ሰው አያስፈልገኝም እንዳትሉ ሰው የሆነው ኢየሱስ አለ። እርሱ በሐዘናችሁ አብሯችሁ ነው፤ ስትከብሩ የሚፈልጋችሁ ስትዋረዱ የሚጥላችሁ አይደለም። ማንም ሳይረዳችሁ ሁሉ ጀርባ ሲሰጣችሁ በሙሉ ፍቅሩ ከእናንተ ጋር የሚሆነው ኢየሱስ ነው።

         ✨ወዳጄ ያላችሁት ስትወድቁ እንዳላየ ያልፋችኋል ኢየሱስ ግን እጁን ይዘረጋላችኋል። ችግራችሁ ወዳጅ ሲያርቅባችሁ ኢየሱስ ግን በችግራችሁ ጊዜ ወደእናንተ ይመጣል።
" እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ"

ብሎናል። ስለዚህ ልባችን ሲሰበር፣ መንገድ ሲጨልም፣ እንባችን ሲፈስ ማንም የለኝም አትበሉ ኢየሱስ ከእናንተ ጋር ነው።

       ✨ኢየሱስ ወዳጅ የሆነን ማንም በእርሱ ልክ ወዳጅ እንደማይሆንልን፣ ማንም ሊወደን በማይችል ማንነት ወዶን፣ ሁልጊዜ አጥፊ፣ የስህተቶች መነኻሪያ መሆናችንን እያወቀ፣ ከነ ጉዳችን ከነችግራችን አብሮን ሊሆን የወደደ ወዳጃችን ነው።

       ✨
#እድሜ_ልክ_የፈረመ_ወዳጅ_የላችሁም። ባሻው ሰዓት ከሕይወታችሁ ለመውጣት በጨረታው አይገደድም። ኢየሱስ ብቻ ከመቃብር ባሻገር፣ ከሞትም ባለፈ፣ ከዘመናትም ተሻግሮ ለዘላለም የተወዳጀን ወዳጅ ነው።

          ✨ምድራዊ ወዳጆቻችሁን አትግፉ ሕይወታችሁ ላይ አሻራ ያሳረፉትን አትግፉ እንዲህ አይነት ወዳጅ ባይኖራችሁ እንኳን ከወዳጅ በላይ የሆነ ወዳጅ ኢየሱስ እንዳለ አትርሱ። ደስ ብሏችሁ ዋሉ።

@lovedbychrist
@lovedbychrist


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ኦሪት ዘፍጥረት 39:2 (AMH)
••••••••••
² እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት ነበረ።

@lovedbychrist
@lovedbychrist


ወደ ሮሜ ሰዎች 4:20 (AMH)
••••••••••
²⁰ ለእግዚአብሔርም ክብር እየሰጠ፥ የሰጠውንም ተስፋ ደግሞ ሊፈጽም እንዲችል አጥብቆ እየተረዳ፥ በእምነት በረታ እንጂ በአለማመን ምክንያት በእግዚአብሔር ተስፋ ቃል አልተጠራጠረም።

@lovedbychrist
@lovedbychrist


#በዚህ_ሳምንት

በነገር ሁሉ ትከናወኑ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእናንተ ላይ ትሁን ከዚህም የተነሳ መፍጠን ይሁንላችሁ!!!
@lovedbychrist
@lovedbychrist


ሽንገላ #ስውር እስር ቤት ነው፣
ባለቤቱ ፈቅዶ እስካልተፈታ ድረስ እንደታሰረ ይኖራል።
ሽንገላ
#እርቅ የሌለው ጠብ ነው ሸንጋይ እራሱን አጋልጦ እስካልዳነ ድረስ በልቡ እየተጣላ ይኖራል
ሽንገላ በቅዱሳን መሀል
#ከልካይ አጥር ነው
ጉብኝትን ያርቃል ።
ሽንገላ
#የተንኮለኛ ሰው ወጥመድ ነው።
ምቹ ጊዜ ሲያገኝ በክፋቱ ያጠምዳል።

የሸንጋይ ሰው እጆች
#ለመከራ ያቅፋሉ
አሳልፈው ይሰጡሀል።
ከሽንገላ ለመራቅ ልባችንን
#በእውነተኛ ሚዛን እናስመዝነው እርሱም #የእግዚአብሔር #ቃል ነው ።ያኔ በሰውም በእግዚአብሔርም ፊት በደህና እንመላለሳለን !!!!!

#ለእኔ_ሕይወት_ክርስቶስ_ነው
SHARE |
@lovedbychrist
SHARE |
@lovedbychrist


አመሰግናለው
ድንቅ መዝሙር
ዘማሪ ዳጊ ጥላሁን
@lovedbychrist
@lovedbychrist
@lovedbychrist


#እግዚአብሔር_ወደ_ፊት_ትልቅ_ነገር_ሲያሳየን_ሰይጣን_ደግሞ_ዛሬን_በትንሽ_ነገር_ሊጥለን  #የማይፈነቅለው_አለት_የለም

ነገርግን፦ፀጋው አለ ያስችለናል እግዚአብሔር ላሳየን ነገር እንፋለማለን።
👉ይልቅ በጌታ እና በሀይሉ ችሎታ መበርታቱ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነዉ
የጠላት ሽንገላ
#እምቢ እያልን ወደ ታየልን ድላችን ወደ ፊት እንሩጥ

   "የተወደዳችሁ በርቱልን
@lovedbychrist
@lovedbychrist

20 last posts shown.