.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 17
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahunናሆም ዶርም ሲገባ ናታኔም አልሰማውም ። ምክንያቱም ናታኔም በረንዳ ላይ ጀርባውን ለዶርሙ በር ሰጥቶ እያነበበ ነበር። ናሆም የሚቀይረውን ልብስ ቀይሮ ሊወጣ ሲል ናታኔም ደግሞ ቀና ሲል አይን ለአይን ይገጣጠማሉ ። ናታኔም ብድግ ብሎ "እንዴ ናሆም ደህና ነህ አሁንማ ተጠፋፋን እኮ ወንድሜ " አለ " በጣም ደህና ነኝ ወንድሜ ልክ ነህ በጣም ነው የተጠፋፋነው ግን ደግሞ ያው አንተም ስታነብ ነው የምትውለው እኔም ማንበብ ስለጀመርኩ ነው ።በል አሁን ቶሎ መውጣት አለብኝ " " ናሆም ወደየት ነው እንዲህ የምትቻኮለው? ቀስ በል እንጅ" አለ ናታኔም ወደ ናሆም እየተጠጋ " እየውልህ ወንድሜ ቶሎ መሄድ አለብኝ ቀጣይ ሳምንት የሚዘጋጅ የስነፅሁፍ ምሽት አለ ስለዚህ መዘጋጀት አለብኝ ለዛ ነው ወንድሜ " " ታቀርባለህ ?" አለ ናታኔም " አወ አቀርባለሁ " አለና ናሆም ትቶት ወጣ።
መቅደላዊት በንዴትም በእልህም ወዲያና ወዲህ ትንጎራደዳለች። አይኖቿ ፀሀይ ለመሞቅ ወጥተው የተቀመጡ ይመስላሉ" ናሆም እንኳንም መረቤ ላይ ተጠመድክ ይሄን ነበር የምፈልገው ።አሁን የጨዋታው አሸናፊ ማን እንደሚሆን እናያለን ። አታስብ ቃል እገባልሀለሁ ትክክለኛዋን መቅደላዊት ታያለህ። አወ " አለች ራሷን አያወዛወዘች ስለዚህ ቀጣይ ማድረግ ያለብኝ ነገር ቢኖር ይሄ ነው " አለችና ጠረምጴዛው ላይ የተወሰነ ፅሁፍ የማይመስል ደግሞም ስዕልም የማይመስል ነገር ሞነጫጨረች እና በአንድ እጇ ወገቧን ይዛ አውራ ጣቷን ከንፈሯ ላይ አስጠጋችው።
ባሩክ ሰባ ደረጃ አለፍ ብሎ ከበቀለች አንዲት ትንሽየ ዛፍ ስር ተቀምጦ ወጭ ወራጁን ይመለከታል ። kissing square በመባል የሚታወቅ ቦታ ነው። አንዳንድ ካፕሎች እየመጡ እዚህ ቦታ የሆድ የሆዳቸውን ሲጫወቱ ያመሹና
"ሲመሽ ወደ ማታ ማታ ማታ፣
አቤት የአንቺ ፍቅር ሲበረታ "
ብሎ ድምፃዊ ቴወድሮስ ካሳሁን እንደዘፈነው ።እነዚህ ካፕሎችም ደንገዝገዝ ሲል ጨለማው ለአይን ሲነሳ ከንፈር ለከንፈር ይያያዛሉ። ከዚያ ለያዥ ለገናዥ ያስቸግራሉ።በዙ ቆነጃጅት የከንፈር ድንግልናቸው የሚወሰደው እዚህ አካባቢ ነው። አንዳንድ ቦዘኔ እና በሰው ደስታ የሚደሰቱ ስራየ ብለው እዚህ አካባቢ በመምጣት የማታ ትዕይንትን ያለ ገቢር ክፋይ ይመለከታሉ ።ያለ ክፍያ ሲኒማን እንደማየት ይቆጥሩታል። ሰባ ደረጃ ደግሞ ስንቱን ደምበር እየሆነ ያስመልሰዋል ።ከሁሉም ብሎኮች ያሉት ወንዶች በመንገዳቸው ባይገናኝም እንኳ ሰባ ደረጃን ሳይሳለሙ አይሄዱም ።አንዳንዶች በዚህ ደረጃ ላይ ሲወጡ ሲወርዱ ከየካቲት ወይም ከስድስት ኪሎ ወደ ፒያሳ የሚወርዱበት ትክክለኛው ሰባ ደረጃ ይመስላቸዋል። በርግጥ ይሄን አካባቢ ለሚያዘወትር ሰው እና ለሚመሰጥበት ሰው ተነቦ የማያልቅ መፅሐፍ መፃፍ ይችላል።ባሩክ ከወዲያኛው መስመር መቅደላዊት ስትመጣ ሲያይ ከተቀመጠበት ይነሳ እና ወደ እሷ ይሄዳል። መቅደላዊት ስለ ባሩክ ሰምታለች ለሴት ባለው ከልክ ያልፈ ድፍረት እና ንቀት ትናደዳለች።ወደ እሷ አቅጣጫ እየመጣ እንደሆነ ስታይ ጉዞዋን ገታ አድርጋ ባለችበት ቆመች ባሩክ እየተጠጋት መጣ ። " ሰላም እንዴት ነሽ መቅደላዊት ባልሳሳት አንቺ ነሽ?" አልተሳሳትክም ፈላስፋው ባሩክ እስጢፋኖስ " አለች መቅደላዊት በጥላቻ አይን እየተመለከተችው " ወይ ይቺ አለም ምን አይነት ሰወች ነን የምንኖርባት ግን? ብሎ ከራሱ ጋ አወራ እና "መቅደላዊት የአንቺ እንዲህ መሆን የኔ ጉዳዬ አይደለም እንኳን አንቺ በህይወቴ ላይ ቅንጣት ታህል ቦታ የሌለሽ ሴት ይቅርና በህይወቴ ውስጥ ሰፊ ቦታ ያላቸው ሰወች እንኳ ምንም ቢሉ ግድ አይሰጠኝም ።እዚህ የመጣሁት የአንቺን የተዘፈዘፈ ፊት ለማየት አይደለም ለዚህም ብየ የምጠቀምበትን ጊዜየን አላጠፋም ።አውቃለሁ የዚህ ጊቢ ሴቶች በእኔ በኩል ጤናማ አመለካከት የላችሁም።እሱ ለእኔ ምይም ነው ሰው እንዲወደኝ አለያም እንዳይጠላኝ ሀሰት የምሸርብ ሰው አይደለሁም።እስከሚገባኝ እና እስከማውቀው አንቺ በእኔ ላይ የምትናደጅበት አመክንዮ አለ ብየ አላስብም ።ምን አልባት በሌሎቹ ጓደኞችሽ ካልሆነ። አሁን እሱን ልተወውና የመጣሁበትን ብየሽ ልሂድ ምን አልባት በሀሳብ ላንግባባ እንችላለን በሚል እሳቤ የምታደርጊውንና የምታደርጊውን ምክንያት ፣ ውጤት በተገቢው ሁኔታ እዚህ ደብዳቤ ላይ አስፍሬልሻለሁ። እኔ እና አንቺ የተለያየን አመለካከት እንዳለን አውቃለሁ ግን በናሆም ጉዳይ አንድ ነን ።እርዳታየን የጠየቀኝ ናታኔም ነው። ፖስታውን ስታነቢ ማንም እንዳያይሽ ተጠንቀቂ በተረፈ ቀጣይ እሁድ ናሆም የሚሳተፍበት የስነፅሁፍ ምሽተሰ አለ ከፈለግሽም ሀሙስ የሂስ ምሽት አለ መምጣት ትችያለሽ " አለ እና ባሩክ ትቷት ሄደ ። መቅደላዊት ለተወሰነ ርቀት እስኪሄድ በአይኗ ከሸኘችው በኋላ ስልኳን አውጥታ ወደ ናታኔም ደወለች " አቤት መቅዲ " አለ ናታኔም " አልገባኝም ናታኔም ምን እያሰብክ እንደሆነ ለምንድነው በዚህ ጉዳይ ላይ ባሩክን ያስገባኸው? በእኔ ስለማትተማመን ነው? ወይስ ሌላ ያሰብከው ነገር አለ? " አለች " ለዛ አይደለም አንቺ እንዳሰብሽው አይደለም። ታቂያለሽ አንቺ በዚህ ጉዳይ ላይ ተዋናይ እንጅ ፀሀፊም ዳይሬክተርም ተዋናይም እንዳትሆኚ ብየ ነው። ጊዜሽን እንዳይወስድብሽ ከትምህርትሽ እንዳትዘናጊ በዛ ላይ ባሩክ አሪፍ የማንበብ ልምድ እና የማስተዋል አቅም ስላለው ናሆምን በቀላሉ ለማጥመድ ይቀለናል ። ከዚህ በኋላ ባሩክ የሚሰጥሽን ስክሪፕት ናሆም ላይ መተወን ብቻ ነው የሚጠበቅብሽ ። ገባሽ አይደል መቅዲ? " አለ አወ ገብቶኛል ጥሩ ያሰብክ ይመስለኛል ። ባሩክ ግን ደስ ስለማይለኝ ነው " አለች " አውቃለሁ መቅደላዊት ስለ ባሩክ ጥሩ ያልሆነ አመለካከት እንዳላችሁ አውቃለሁ ግን ባሩክን አውቀዋለሁ የሰፈሬ ልጅ ነው የዚህን አላማም እንደነገርኩት ሳያቅማማ ስለተቀበለኝ ነው።" አለ " እሽ በቃ የሆነ ፖስታ ነገር ሰጥቶኛል ከአነበብኩት በኋላ እናወራለን ደግሞ እረስቼው ናሆም እሁድ የስነፅሁፍ ምሽት ላይ ግጥም ያቀርባል።" " ማን ነገረሽ? " " ይሄ ባሩክ ተብየህ ነዋ መረጃው እውነት ይሁን አይሁን የማውበው ነገር የለኝም " አለች " ባሩክ ባሩክ ካሰብኩህ በላይ ስራየን እያቃለልክልኝ ነው " አለ ናታኔም ጮሆ። " ማንነው ስራህን የሚያቃልልልህ? አለ በሩን ከፍቶ እየገባ።
ናታኔም ደንግጦ ቆመ........ ꧁༺༒༻꧂✎
🌺ክፍል አስራ ስምንት ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ
Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄