.
መ ቅ ደ ላ ዊ ት 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
♥️ ክፍል 18
◈ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Ambaye Getahun
ማን ነው ስራህን ያቀለለልህ? ምን አይነት ስራ ነበር የነበረህ? " ናሆም ጥያቄወቹን አከታተለበት ። " አሳይመንት ነበረኝ እሱን ሰርቶልኝ ነው " አለ ናታኔም በድንጋጤ " ታዲያ ምነው ደነገጥክ? " " በድንገት ስለገባህብኝ ነዋ " " እንደዛ ከሆነ ጥሩ ግን..... ምን አሳይመንት ነበር? እንዴት ስታወራ አልሰማህም?" አለ ናሆም " አየ ወንድሜ ለዚህ እኮ ነው እኔ እና አንተ ተጠፋፍተናል የምልህ ።ግን የስነፅሁፍ ዝግጅት አለብኝ ምናምን ብለኸኝ ነበር እኮ እንዴት ታዲያ ተመለስክ?" " ባክህ ያቺ መቅደላዊትን ከሩቅ አይቻት የሁሉም ነገር ፍላጎቴ ጠፋ " " ቆይ ግን ይቺ ልጅ ምን አድርጋህ ነው እንዲህ ጠምደህ የያዝካት?" ምን እኔ ጠምጀ እይዛታለሁ እሷ ነች እንጅ " እኮ እሷ ምን አድርጋህ ነው?" " ከንፈሩን ነከሰ ባውቅማ ኖሮ ጥሩ ነበር የማደርገውን አውቅ ነበር። ነገር ግን ልጅቱ አስመሳይ ነች በጭራሽ የሆነ ነገር እየሰራች ነው እስካሁን አላወኩም ግን ግዴለም እደርስበታለሁ።" አለ ናሆም "
መቅደላዊት ፖስታውን እያየች ይሄ ደግሞ ምን ለማድረግ አስቦ ነው? " ራሱን እንዴት ነው የሚያየው? ሲያስጠላ " አለች እየተመናጨቀች ፖስታውን በዝግታ አንስታ ከከፈተች በኋላ በጥሞና አምብባ ከጨረሰች በኋላ ፊቷ ሁሉ ተለዋወጠ። ስልኳን አንስታ ደወለች " አቤት መቅደላዊት " ከወዲኛው የስልክ ድምፅ የተሰማው የናታኔም ድምፅ ነበር። " ቆይ ጓደኛህ ምን አይነት ጅል ነው ያመዋል ልበል? ሰውን ሳያውቅ " አለች መቅደላዊት " ቆይ መቅዲ ተረጋጊና ምን እንደተፈጠረ ንገሪኝ " አለ ናታኔም ።መቅደላዊት አንድም ሳታስቀር ሁሉም በስልክ ነገረችው እና በመጨረሻ" አሁን ላገኘው እፈልጋለሁ ስልኩን ስጠኝ " አለች " እሽ 0910..........ባሩክ እስጢፋኖስ ከፈለግሽ ዲዮጋንም ማለት ትችያለሽ ።ነፃ ሁኝ ግን መቅዲ አደራሽን ባሩክ ላይ ብስጭት መቆጣት መጮህ አይሰራም ።በእርጋታ የአንቺን ሀሳብ ትነግሪዋለሽ ።ለምን የእሱን ሀሳብ በአንቺ ሀሳብ ላይ እንደመዘንሽ ይገባዋል።ወይም ለምን እንደዛ እንዳለሽ ያብራራልሻል። ይህ ካልሆነ ግን በእውነት ትቶሽ ይሄዳል ።" አለ ናታኔም በልመናም በማስጠንቀቂያም አዘል ንግግር በተወሰነም መልኩ ስለ ባሩክ ግብአት " እና መሄድ ይችላል ለእኔ ብሎ አይቀመጥ " አለች መቅደላዊት " መቅዲ ምን ሆነሻል? ናታኔም በስልክ አምባረቀ " በዚህ ጉዳይ ላይ እኮ አንቺ ነሽ ትልቁን ስራ እየሰራሽ ያለሽው ለምንድነው የምትቀልጅው?" ናታኔም እየተቆጣ ተናገራት። " እሽ ናቲ በቃ አትቆጣ እንዳልከኝ አደርጋለሁ " አለች " ጥሩ አመሰግናለሁ ስትጨርሽ ደውይልኝ " እሽ እደውልልሀለሁ ።
ባሩክ " አክሱም የተማሪወች መናፈሻ " መጨረሻ ፎቅ ላይ ሆኖ " መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ" የተሰኘውን የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ን መፅሀፍ ማንበቡን ገታ አድርጎ ያዘዛትን ወተት አንስቶ ፉት ሲል ስልኩ ጠራ። ያነሳትን ወተት አንድ ጊዜ ስቦ ወደ ነበረችበት ጠረምጴዛ መለሳትና ስልኩን ከኪሱ አወጣ ። አዲስ ቁጥር ነው ላለማንሳት ካመነታ በኋላ አንስቶ "ሀሎ" አለ ። " ሰላም ነው ባሩክ? አወከኝ?" " አላወኩሽም ወይዘሪት " አለ። " መቅደላዊት ነኝ " አለች " እሽ መቅደላዊት በጣም ነው የሚገርመው አሁን ስለ አንቺ እያሰብኩ ነበር።" " እንዴ ስለምንድን ነው ስለ እኔ እምታስበው?" የዋህነትሽን ፣ ቁጡነትሽን ፣..... ሌላም ሌላም እሱን አለማሰብ አይቻልም በዛ ላይ ........" ብሎ ዝም አለ ።" እህ በዛ ላይ .........ጨርሰው እንጅ " አለች ግን ለምንድነው ሴቶች ተጀምሮ ላልተጨረሰ ሀሳብ የምትሞቱት? ውይ ሁሉንም ማወቅ የሚፈልጉ ፍጥረቶች ቢኖሩ ሴቶች ናቸው ሊፈነዱ እኮ ነው የሚደርሱት። ምን እንደሚሻላቸው አሁን ይሄን ሳልጨርስላት ብቀር ሌቱንም ቀኑንም ስለዚህ ጀምር ሀሳብ ነው ቁማ የምታድረው ጉድ እኮ ነው። " አለ በውስጡ " እየጠበኩህ እኮ ነው "አለች ።መቅደላዊት እንዳልተፋታችው ሲረዳ " በዛ ላይ ቆንጆ ነሽ ለማለት ፈልጌ ነው።" አላት በተቻለው መጠን ግንኙነታቸውን ጤናማ አድርጎ ለመሞከር አስቧል። " ኧረ ባክህ ቆንጆ ነኝ እንዴ? አላወኩም ነበር።" አለች መቅደላዊት ምፀታዊ ንግግር ነበር። ባሩክ ገብቶታል ግን እንዳልገባው ለመምሰል " አባቴ ይሙት እውነቴን ነው " አለ ባሩክ እየሳቀ ። መቅደላዊት በሱ በኩል ያላትን የተቃረነ አመለካከት የማስተካከል አይደለም ዋና እቅዱ ናሆም ነው መቅደላዊት ጋር ያለው ጓደኝነት ጤናማ እና አሪፍ ከሆነ ናሆምን ካለበት የስነልቦና ችግር ማውጣት ይቻላል ብሎ ስላመነ ነው።እንዲህ ውድ ጊዜውን የሚያባክነው። ባሩክ ህይወቱ ማንበብ ብቻ ነው።መቅደላዊት ትንሽ ፈገግ ካለች በኋላ " ፈልጌህ ነበር " አለች " ለምንድነው ነው ልታገኚኝ የፈለግሽው?" አለ ባሩክ በደብዳቤው የተነሳ እንደሆነ ገምቷል።" እሱን ስንገናኝ እነግርሃለሁ " " ጥሩ መምጣት ከቻልሽ አክሱም ነኝ ጣራው ላይ " እሽ በቃ መጣሁ " ብላ ስልኩን ዘጋችው።
መቅደላዊት አክሱም መናፈሻ ጣራው ላይ ስትወጣ ሽቅብ የሚነፍሰው ነፋስ አንዳች ነገር የፈለገ ይመስል ቀሚሷን ለመግለብ ይጥራል ። ቅንዝራም የሆነ ነፋስ እሷ ዝቅ ስታደርግ እሱ ደግሞ ከእንደገና ይገልበዋል በስተመጨረሻ እጇን ከቀሚሷ ላይ ሳታነሳ በሁሉም አቅጣጫ ስታማትር ባሩክ በመናፈሻው ደቡብ አቅጣጫ ጥግ ላይ ሆኖ በጥሞና ሲያነብ ተመለከተችው። ለተወሰነ ደቂቃ ቆማ ብትመለከተው እሱ ግን ከሚያነበው መፅሀፍ ውጭ ሌላ የትኛውንም አቅጣጫ ለማየት የፈለገ አይመስልም ። " ባይፈላሰፍ ቆንጆ ወንድ ነበር " አለችና ባሩክ ወደተቀመጠበት ቦታ ሄደች ባሩክ ወደ እሱ የቀረበ የእግር ኮቴ እንደሰማ ቀና ሲል መቅደላዊት ደርሳለች። ሰለም ብያለሁ እንዴት ነሽ ? እጁን ለሰላምታ ዘረጋ ጨበጠችው ጨበጣት እና ፈጠን ብሎ የምትቀመጥበትን ወንበር ስቦ አስቀመጣት። መቅደላዊት በአድራጎቱ የተገረመች ትመስላለች ። የአክሱም ሀውልት ምስል ያለበትን ቲሸርት የለበሰ አስተናጋጅ መጣ እና የተለመደውን ጥያቄ ጠየቀ የመቅደላዊትን የስፕራይት ትዕዛዝ ተቀብሎ አስተናጋጁ ሄደ። " ፈጥነሽ ገው የመጣሽው " አለ " የእውነት? እኔ ደግሞ የቆየሁ መስሎኝ ነበር " አይ በጭራሽ ጥሩ ስአት ላይ ነው ቢያንስ ከዘገየሽ ራሱ የዘገየሽው ካለሽበት እስከዚህ ድረስ ለመድረስ የፈጀብሽ መንገድ ነው " አለና ምቾት እንዲሰማት አደረገ። አስተናጋጁ አንድ የውሀ ብርጭቆ ከአንድ ሎሚ ጋር የታዘዘውን ስፕራይት አስቀመጠ እና ወደ ሌላኛው አካባቢ ተሰወረ........
꧁༺༒༻꧂
✎ 🌺ክፍል አስራ ዘጠኝ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share @loverrtime
የፍቅር ጊዜ❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄