TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
ማኅበረ ጽዮን⛪️

6 Aug, 21:01

Open in Telegram Share Report

“ቤተሰብ ይሁኑ”
የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት የዩቲዩብ ቻናል - ”ሠሌዳ ሚዲያ” ሥራ ጀመረ!


የሠሌዳ ሚዲያ የስቱዲዮ ምረቃና የቻናሉ ይፋዊ  የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት የሃይማኖት አባቶች፣ መምህራንና የተከበሩ እንግዶች በተገኙበት ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀትና በመንፈሳዊ ክብር ተከናውኗል።

የትውልዱን ሕሊና በዕውቀትና በጥበብ የሚያንጹት የተወዳጁ መምህር መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች በ"ሠሌዳ ሚዲያ" መድረክ በኩል ለአድማጮችና ለተመልካቾች መቅረብ መጀመራቸው አገልግሎቱን በስፋት ለማዳረስ ተጨማሪ ዕድል እንደሚሆን ታምኖበታል።

ሠሌዳ ሚዲያ በመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የተመሠረተ የዲጂታል ሚዲያ መድረክ ሲሆን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር እውነትን፣
ጥበብንና ኦርቶዶክሳዊ ዕሴቶችን የሚያለመልምና ትውልድን የሚያጎለብት የዕውቀት ምንጭ እንዲሆን ታስቦ ሥራ ጀምሯል።

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕያው ቃሉ "ምን እንድትሰሙ፥ ተጠበቁ"(ማርቆስ 4፥24)  እንዳለው፥ ሠሌዳ ሚዲያ አድማጭና ተመልካቾች የሚያዩትንም ሆነ የሚሰሙትን በመጠኑና በጥንቃቄ እንዲመርጡ ለሚያሳስበው የዘመኑ የነፍስ ጥሪ ምላሽ የሚሆኑ የጠሩ እና የተመረጡ ይዘቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡

በሠሌዳ ሚዲያ፡-
Ø  መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች፣
Ø  የማኅበረሰብ ጉዳዮች ዳሰሳዎችና ትንተናዎች፣
Ø  የባህልና የዕሴት አንጸባራቂ አንድምታዎች፣
Ø  ከምሁራን፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ ጥልቅ ውይይቶችና ቆይታዎች
Ø  ሌሎችም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች በሚዛናዊነትና በኃላፊነት ስሜት ይቀርባሉ፦

ይህን የዕውቀትና የጥበብ ማዕድ ለመካፈል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይወዳጁን፤ ለብዙኃኑ ተደራሽ እንዲሆንም አጋር በመሆን ሰብስክራይብና ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!

YouTube:ሠሌዳ ሚዲያ
TikTok: @seledamedia
Instagram: seledamedia
Facebook: Seleda Media

ሠሌዳ ሚዲያ - ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ።
###
Youtube

https://www.youtube.com/@seledamedia.megabehadiseshetu
Tiktok

http://www.tiktok.com/@seledamedia
Instagram

https://www.instagram.com/seledamedia/

Facebook

https://web.facebook.com/profile.php?id=61591554360962
Seleda Media ሠሌዳ ሚዲያ
Seleda Media ሠሌዳ ሚዲያ. 3,727 likes · 7,891 talking about this. «ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ» (ማር 4፥24) ሠሌዳ ሚዲያ በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የተመሠረተ የዲጂታል ሚዲያ መድረክ ሲሆን፣ በመንፈሳዊ እና ማኅበረሰባዊ ጉዳዮች እውነትን፣ ጥበብንና እሴትን የሚያጎለብቱ ይዘቶችን...

1.5k 0 0 5
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot