“ቤተሰብ ይሁኑ”
የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት የዩቲዩብ ቻናል - ”ሠሌዳ ሚዲያ” ሥራ ጀመረ!የሠሌዳ ሚዲያ የስቱዲዮ ምረቃና የቻናሉ ይፋዊ የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት የሃይማኖት አባቶች፣ መምህራንና የተከበሩ እንግዶች በተገኙበት ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀትና በመንፈሳዊ ክብር ተከናውኗል።
የትውልዱን ሕሊና በዕውቀትና በጥበብ የሚያንጹት የተወዳጁ መምህር መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ትምህርቶች በ"ሠሌዳ ሚዲያ" መድረክ በኩል ለአድማጮችና ለተመልካቾች መቅረብ መጀመራቸው አገልግሎቱን በስፋት ለማዳረስ ተጨማሪ ዕድል እንደሚሆን ታምኖበታል።
ሠሌዳ ሚዲያ በመጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ የተመሠረተ የዲጂታል ሚዲያ መድረክ ሲሆን መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር እውነትን፣
ጥበብንና ኦርቶዶክሳዊ ዕሴቶችን የሚያለመልምና ትውልድን የሚያጎለብት የዕውቀት ምንጭ እንዲሆን ታስቦ ሥራ ጀምሯል።
ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕያው ቃሉ "ምን እንድትሰሙ፥ ተጠበቁ"
(ማርቆስ 4፥24) እንዳለው፥ ሠሌዳ ሚዲያ አድማጭና ተመልካቾች የሚያዩትንም ሆነ የሚሰሙትን በመጠኑና በጥንቃቄ እንዲመርጡ ለሚያሳስበው የዘመኑ የነፍስ ጥሪ ምላሽ የሚሆኑ የጠሩ እና የተመረጡ ይዘቶች የሚቀርቡበት ነው፡፡
በሠሌዳ ሚዲያ፡-
Ø መንፈሳዊ ትምህርቶችና ስብከቶች፣
Ø የማኅበረሰብ ጉዳዮች ዳሰሳዎችና ትንተናዎች፣
Ø የባህልና የዕሴት አንጸባራቂ አንድምታዎች፣
Ø ከምሁራን፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ ጥልቅ ውይይቶችና ቆይታዎች
Ø ሌሎችም መንፈሳዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች በሚዛናዊነትና በኃላፊነት ስሜት ይቀርባሉ፦
ይህን የዕውቀትና የጥበብ ማዕድ ለመካፈል በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይወዳጁን፤ ለብዙኃኑ ተደራሽ እንዲሆንም አጋር በመሆን ሰብስክራይብና ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
YouTube:ሠሌዳ ሚዲያTikTok: @seledamediaInstagram: seledamediaFacebook: Seleda Mediaሠሌዳ ሚዲያ -
ምን እንድትሰሙ ተጠበቁ።###
Youtube
https://www.youtube.com/@seledamedia.megabehadiseshetuTiktok
http://www.tiktok.com/@seledamediaInstagram
https://www.instagram.com/seledamedia/
Facebook
https://web.facebook.com/profile.php?id=61591554360962