"እናንተን ንጹሐን ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም"
"በትግራይና በፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በአማራ ክልል ባለው አለመግባባት ችግሮችን ለመፍታት በምልዓተ ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ ፊት እናንተም ባላችሁበት ይህ ችግር በዚህ ሊቀጥል አይገባውም ችግር ከመፈጠሩ በፊት የሰላም ኮሚቴ ይቋቋም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ጮሗል? አልጮህም? እናንተስ በዚያን ጊዜ ምን ትሉ ነበር?
በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን ተመልክቶ ችግሩን ለመፍታት በፌደራል መንግሥት፣ በትግራይና በአማራ ክልል ያለው ችግር እንዲፈታ እንደ ጥንቱ ታቦት ይዘን፣ መስቀል ይዘን፣ ሕዝባችንን እናገናኝ ዝም ብለን ማየት የለብንም ብሎ ቅዱስ ሲኖዶስ ሲጮህ ምን ነበር ያላችሁት አባቶች?
ደም በሚፈስበት ቦታ ላይ ሄዳችሁ አስታርቁ ትግራይ ለምን ሰላም ሆነ ነው ወይ ይህንን የምትሉ አላላችሁንም?
ቤተክርስቲያን ዝም አለች አላችሁ፤ ምነው ቤተክርስቲያን ምንም እንዳልተናገረች ደግማችሁ ደጋግማችሁ ተናገራችሁ፡፡ ያውም ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ስሕተትን ለማረም ስሕተት መደገም የለበትም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬም ጉዳዩን አይቶ ችግሩን ለመፍታት ይቅርታ የሚለውን ጥያቄም አቅርቧል፡፡ ነገም ያቀርባል በሚገባው በመልኩ በአንጻሩ ደግሞ የሠራው ያደረገው ነገር ሊቀበር አይገባውም ሊነገርለት ይገባል፡፡ ስለዚህ በዚህ ጥፋት ከሆነ እናንተም እኛም የጋራ ተወቃሾች እንሆናለን እንጂ እናንተን ንጹሐን ቅዱስ ሲኖዶስን ተወቃሽ የሚያደርገው አንዳችም ነገር የለም፡፡"
ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት
ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ