በዚህም ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት፤ ከዚያም በክብር ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር›› ብለው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ለ፲፪ ዓመታትም ኖራለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን!
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች በቤተ መቅደስ ለ፲፪ ዓመታትም ኖራለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን!
ምንጭ፡- ነገረ ማርያም