የደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርትን አስመረቀ።
በማእከለዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት የደብረ ምሕረት አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት 21 ደቀ መዛሙርትን ታኅሣሥ 27 ቀን 2017 ዓ.ም አስመርቋል ።
በመርሐ ግብሩ ላይ የማእከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ፣የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ሥልጣናት ቆሞስ አባ ዮሴፍ ፣ ከተለያዮ ቦታዎች የመጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ተግኝተዋል።
የቀዳሜ አድባራት አበራ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅኔ ምስክር መምህር ወላደ አእላፋት ጌድዎን አበበ ና ተመራቂ ደቀ መዛሙርቱ ቅኔ አቅርበዋል።
ብፁዕነታቸው ባስተላለፉ መልእክት ጉባኤ ቤቱ ያለበትን ችግር ተቋቁሞ በርካታ ደቀ መዛሙርትን እያፈራ በመሆኑ ትኩረት የሚፈልግ ጉባኤ ቤት ነው ብለዋል።
ጉባኤ ቤቱ የቦታ ጥበት እና ከከተማ በሚለቀቅ ፍሳሽ ከፍተኛ ችግር እየደረሰበት በመሆኑ በዘመናዊ መልኩ ለመገንባት የሕንጻ ዲዛይኑ ተሰርቶ መጠናቀቁም ተጠቁሟል።
በማኅበረ ቅዱሳን የጎንደር ማእከል ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት ፍቃደ ፈጠነ በጉባኤ ቤቱ ዘርፈ ብዙ ችግሮች መኖሩን ጠቅሰው ግንባታው ተጀምሮ በታቀደለት ዕለት እንዲጠናቀቅ ከሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ምእመናን ተሳትፎ ያስፈልጋል ብለዋል።