በቤተ ክርስቲያኒቱም ሆነ በሀገሪቱ ሰፊውን ቁጥር ይዞ የሚገኘው ወጣቱ ክፍል በሱስ ተይዞ መገኘቱ የማኅበረሰብ ክፍል ቤተክርስቲያንንም ሆነ ሀገርን በማገልገል ሂደት ውስጥ ያለው ሚና ቀላል የማይባል ሆኖ ሳለ ከሱስ ጋር በተያያዘ ግን እንደ ቤተክርስቲያንም እንደ ሀገርም አስጊ ሁኔታ በመድረሱ ትውልድን ለመታደግ ቤተክርስቲያን የሱስ ማገገሚያ ተቋማትን በማዘጋጀትና በማከም ሂደት ውስጥ ተሳትፎ በማድረግ የራሷን በጎ አሻራ ማሳረፍ ግድ እንደሚላት ተመላክቷል።
አገልግሎቱ እስካሁን እየሰጣቸው ባሉ የአማካሪዎች ሥልጠና የችግሩን አሳሳቢነት መነሻ በማድረግ የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን ለካህናትና በምክክር አገልግሎት ለሚሰማሩ ባለሙያዎችም በሥልጠና መልክ እያስገነዘበ እንዳለም ማወቅ ተችሏል።
ለዚህም ጥናት መፍትሔ ተግበራዊነት ማኅበረ ቅዱሳን ከባላድርሻ አካላት ማለትም ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከሀገረ ስብከት፣ከወረዳ ቤተክህነት፣ ከሰንበት ትምህርት ቤት፣ከተለያዩ ማኅበራት፣ ከባለሀብቶች ጋር በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። በቀጣይነትም የተጠናው ጥናት ውጤትና ወደ ተግባራዊ ተቋምነት በሚቀየርበት ሁኔታ ላይ አጋርና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ መታቀዱን የተገኘው መረጃ ያሳያል።