ሙስሊሞች ❲ቁርኣን📖❳ በትክክል ተጠብቋል ስንል...
1- የትኛውም የፍጡር ቃል አልተጨመረበትም ማለታችን ነው። ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ያለው ምዕራፍ፣ አንቀጽ፣ ዓረፍ-ነገር፣ ቃልም ይሁን ፊደል የአላህ ብቻ ነው። በየትኛውም ዘመን ሰርጎ የገባ ባዕድ ቃል (ፊደል) ፈፅሞ የለም።
2- ሙሉ ቁርኣን ቃል-በቃል ከነቢያችን ጀምሮ እስከ ዘመናችን ድረስ በቃል-ትውፊት (ሒፍዝ) ያለምንም እንከን ተላልፏል ማለታችን ነው። ቁርኣንን በቃላቸው ሸምድደው ወደ ቀጣይ ትውልድ የሚያስተላልፉ አንባቢዎች በሁሉም ዘመናት ነበሩ፣ ዛሬ ድረስ አሉ።
3- በእዳ-ክታብ ❲Manuscript❳ ላይ የሚታዩ ስህተቶች ሁሉም «Unintentional» በመሆናቸው በቀላሉ በአጠገቡ ባሉ ወይም በቀደሙ ጽሑፎች የሚፈቱ ናቸው። ጥንት ዘመን የኮፒ ሥራዎች በእጅ የሚሰሩ እንደመሆናቸው ግድፈቶች ይኖራሉ። እነዚያን የምናውቅበት ጥንታዊያን ብራኖች ስላሉን ምንም የሚያሳስቡ አይደሉም።
® https://t.me/mahircomp123