Forward from: ✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞
➡️ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን
እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት። "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው። የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ አዝማደ መባልዕት (የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች) መከልከልን ይመለከታል።
✨1.ዓቢይ ጾም
✨2.ጾመ ፍልሠታ
✨3.ጾመ ሐዋርያት
✨4.ጾመ ነቢያት
✨5.ጾመ ድኅነት
✨6.ጾመ ነነዌ እና
✨7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::
➡️ ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና። እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች። የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን።
➡️ ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል። ኃጢአትን ለመሥራት ፡ ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም። እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2)
➦ የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት (ዘወረደ) የሚጾመው እስከ 12 ሰዓት ሲሆን ከቅድስት (ከ2ኛው ሳምንት) እስከ ተጽኢኖ (የኒቆዲሞስ ዓርብ) ድረስ ደግሞ እስከ 11 ሰዓት ይጾማል:: በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" (እስከ ምሽት 1 ሰዓት) ድረስ ይሆናል::
➡️ አብዝቶ መብላት ፡ ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም እንዲሁ አይገባም። ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን፡ በግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን ፡ በመዓልት ቅዳሴውን ፡ በሰርክ (ምሽት) ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል።
✨1.ዐቢይ (ታላቁ) ጾም
✨2.የጌታ ጾም
✨3.ጾመ ሑዳድ
✨4.የድል ጾም
✨5.የካሳ ጾም
✨6.አርባ ጾም
✨7.የፍቅር ጾም . . .በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል።
✨1.ጾመ ሕርቃል
✨2.ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
✨3.ሰሙነ ዘወረደም ይባላል።
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
💗 እንኳን ለታላቁ "የጌታ ጾም ጾመ እግዚእ" በሰላም አደረሳችሁ!!!
➡️ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአዋጅ ምዕመናን
እንዲጾሟቸው የሠራቻቸው 7 አጽዋማት አሏት። "ጾም" ማለት "መከልከል" ነው። የምንከለከለው ደግሞ ከኃጢአትና ከክፋት ሲሆን አንድም ሰውነትን ወደዚያ ከሚወስዱ አዝማደ መባልዕት (የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች) መከልከልን ይመለከታል።
➦ 7ቱ አጽዋማት:-
✨1.ዓቢይ ጾም
✨2.ጾመ ፍልሠታ
✨3.ጾመ ሐዋርያት
✨4.ጾመ ነቢያት
✨5.ጾመ ድኅነት
✨6.ጾመ ነነዌ እና
✨7.ጾመ ገሃድ ይሰኛሉ::
➡️ በእነዚህ አጽዋማት ከዓቢይ ጾም በቀር እስከ 9 ሰዓት ድረስ መጾም ይገባል። ዓቢይ ጾም ግን የተለየ ሥርዓት አለው ስለ ጾም ሲነሳ አስቀድሞ የሚመጣው ጥያቄ አስፈላጊነቱ ነው "ጾም ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ ከመጠየቅ "ሃይማኖት ለምን ያስፈልጋል?" ብሎ መጠየቁ ይቀላል።
➡️ ምክንያቱም ከሃይማኖታዊ ትዕዛዛት ትልቁ በመሆኑ እርሱን መቃወም ሃይማኖትንና አዛዡን እግዚአብሔርን መቃወም ነውና። እኛ ሃገር ላይ የተለመደች ክፉ ልማድ አለች። የከበደችንን ነገር "አያስፈልግም" በሚል እንከራከራለን።
➡️ ደግሞ ጾምን ለመሻር ጥቅስ የሚጠቅሱ ወገኖች በጣም ይገርሙኛል። ኃጢአትን ለመሥራት ፡ ጾምንም ለመሻር ጥቅስን መጥቀስ አያስፈልግም። እኛ ግን ከፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ (ማቴ. 4:2)
አበው ቅዱሳን ጾመው (ዘዳ. 9:19, ነገ. 19:8, ሐዋ.13:3, ቆሮ. 4:11) አሳይተውናልና እንደ አቅማችን እንጾማለን።
➦ የጾሙ የመጀመሪያው ሳምንት (ዘወረደ) የሚጾመው እስከ 12 ሰዓት ሲሆን ከቅድስት (ከ2ኛው ሳምንት) እስከ ተጽኢኖ (የኒቆዲሞስ ዓርብ) ድረስ ደግሞ እስከ 11 ሰዓት ይጾማል:: በሰሙነ ሕማማት ግን የምንጾመው "እስከ ይሠርቅ ኮከብ" (እስከ ምሽት 1 ሰዓት) ድረስ ይሆናል::
➡️ ነገር ግን ሁሉም እንደ መጠኑ ነውና ከመምሕረ ንስሃ ጋር ሊጨዋወቱት ይገባል። በዓቢይ ጾም ለቻለ ቂጣ በጨው እየበላ፡ ውሃ እየተጐነጨ ሊጾም ይገባል። በእነዚህ 55 ቀናትም ከዕለተ ሆሳዕና በቀር ከበሮ አይጐሰምም። ጸናጽል አይጸነጸልም። ተድላ ደስታም አይደረግም።
➡️ አብዝቶ መብላት ፡ ሳቅ ማብዛትና ጌጥን ማብዛትም እንዲሁ አይገባም። ለቻለ ደግሞ በሌሊት ሰዓታቱን፡ በግህ ኪዳንና ስብሐተ ነግሁን ፡ በመዓልት ቅዳሴውን ፡ በሰርክ (ምሽት) ደግሞ ምሕላውን ሊሳተፍ ይገባል።
➡ በእነዚህ 55 ቀናት ፈቃደ ሥጋ ሊደክም : ፈቃደ ነፍስ ልትሰለጥን ግድ ነውና። ከሌላው ጊዜ በተሻለ ወቅቱ ምጽዋትና ጸሎት የሚደረግበት ነው። በዚያውም ላይ ነገሮችን እያመቻቹ በእነዚህ ዕለታት ቅዱስ ቃሉን መስማት (ማንበብ) ይገባል። በትዳር ውስጥ ላሉም መኝታን መለየት ግድ ነው።
➦ ከ7ቱ አጽዋማት አንዱ የሆነው ይህ ጾም=
✨1.ዐቢይ (ታላቁ) ጾም
✨2.የጌታ ጾም
✨3.ጾመ ሑዳድ
✨4.የድል ጾም
✨5.የካሳ ጾም
✨6.አርባ ጾም
✨7.የፍቅር ጾም . . .በሚሉ መጠሪያዎችም ይታወቃል።
➦ የጾሙ መግቢያ የመጀመሪያ ሳምንት ደግሞ=
✨1.ጾመ ሕርቃል
✨2.ጾመ በረከት ዘሐዋርያት
✨3.ሰሙነ ዘወረደም ይባላል።
✝️ ጾሙን የሰላም ፡ የፍቅር ፡ የምሕረት: የፀጋ :የበረከት ያድርግልን። ጾሞ ለማበርከትም ያብቃን፡፡
"አሁንስ ይላል እግዚአብሔር በፍጹም ልባችሁ በጾምም በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ። አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ: ቁጣው የዘገየ: ምሕረቱም የበዛ: ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ። "ትን. ኢዩኤል 2:12
✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞