Forward from: 💛 መንፈሳዊ ግጥሞች 💛
🍃 ወልድም አባረረኝ 🍃
-➛ ዛሬ በማለዳ ከእንቅልፌ ስነቃ፤.....................................................Click👆
-➛ ፍጹም ረስቼ የሲኦልን ሲቃ፤
-➛ እንደ ብልህ ሴቶች የሆኑ ጠንቃቃ፤
-➛ አስቀድሜ ሳልይዝ ዘይቴን በእቃ፤
-➛ ታዳሚ ለሞላው ለአማኑኤል ሰርጉ፤
-➛ አርፍጄ ወጣሁኝ የክርስቶስ በጉ።
-➛ ጠላቴ ሰይጣንም በመንገዴ ቁሞ፤
-➛ እንዲደርስ በሰርጉ ሙሽራዬ ቀድሞ፤
-➛ መንገዴን አጠረው እንቅፋት አብዝቶ፤
-➛ እኔንም ሊያጠፋኝ እራሱን አጥፍቶ።
-➛ እኔም ተሯሩጬ ለብሼ ግፋፎ፤
-➛ ለሰርጉ ደረስኩኝ መግቢያ-ሰዓት አልፎ፤
-➛ ወልድም አባረረኝ መግቢያውን ቆልፎ።
-➛ ኦ አንትሙ በውስተ-ዓለም ያላቹ፤
-➛ ጊዜያዊ ምቾትን እንደኔ ሽታቹ፤
-➛ እንዳትባረሩ ከክብር መንግስታቹ፤
-➛ እንድታርፉም ሁሌን የዛሬን ደክማቹ፤
-➛ ቀድማቹ ድረሱ ዘይትን ይዛቹ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር