💐💐ክፍል ሰባት (➐)💐💐
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿🌿
✍✍( በኑዕማን ኢድሪስ )✍✍
-
..... አንዳንድ ጊዜ ተጨማሪ ፈተና ለሌላዉ ችግር መልስ ወይም መፍትሄ ሆኖ ይገኛል፡፡ ምናልባትም የሀምዛ የመኪና አደጋ መድረስ ለሀቢብና ለፎዚያ ትዳር መስተካከልና መስመር ጥሩ አጋጣሚ ይሆናል፡፡
ማን ያዉቃል....
ፎዚያ ሆስፒታል ስትደርስ በፍጥነትና በሶምሶማ ከመራመዷ የተነሳ እያለከለከችና እጅግ በጣም ደክማ ነበር፡፡ ሀምዛ ከድንገተኛ ክፍል አልጋ ላይ ተንጋሎ ተኝቷል፡፡ እግሩ ክፉኛ ተጎድቷል፡፡ ቶሎ ሆስፒታል በመድረሱ ከሰዉነቱ የሚፈሰዉ ደም በህክምና እርዳታ ሊቆም ችሏል፡፡ ሀቢብ ደግሞ ከጎኑ ተቀምጦ እያወሩ ነበር፡፡ የሚያወሩት ስለ ሀቢብ ትዳር መበጣበጥ ነበር፡፡ "ከሞትኩም እንኳ የጓደኛዬን ህይወት ደስተኛ አድርጌ፤ ትዳሩን አስምሬለት መሆን አለበት፡፡" ብሎ ለራሱ ቃል ገብቷል፡፡ የጓደኛ ልኩ እንደ ሀምዛ ነዉ፡፡ እራሱን እያጣ ለጓደኛዉ ያስባለል፣ በአደጋ የተጎዳዉን እግሩን እያመመዉ ረስቶት የጓደኛዉን የልብ ህመም ያስታምማል፡፡
ሀቢብ ደግሞ ከዚህ ርዕስ ለመዉጣት የማያደርገዉ ጥረት አልነበረም፡፡ በወሬያቸዉ መካከል "ቆይ ግን መኪያ ሰምታለች?" እያለ ወሬ ያሰናክላል፡፡ (መኪያ የሀምዛ ሚስት ነች) 'እግርህን እንዳያምህ አትገላበጥበት!' እያለ መኝታዉን እንደማስተካከል ያደርጋል፡፡ ሀምዛ ግን ወይ ፍንክች የፎዚያን እንባ ማበስ ሽቷል፡፡
...... ፎዚያ ሆስፒታል ስትደርስ ይገጥመኛል ብላ ያሰበችዉ ነገር መጥፎ ነበር፡፡ ነገር ግን ያ ያሰበችዉ ነገር ደርሶና ሆኖ ባለማገኘቷ ጌታዋን አመሰገነች፡፡ ሆኖም የደረሰበት ነገር አስከፊ በመሆኑ በጣም እያዘነች ባሏንና የባሏን ጓደኛ 'አሰላሙዓለይኩም' ብላ ተቀላቀለች፡፡
..."አልሐምዱሊላህ ሀምዛ ... መኪና አደጋ ሲሉኝ ክፉኛ የተጎዳህ ነበር የመሰለኝ... እንዴት ነህ ግን በአላህ?' ብላ ጠየቀችዉ፡፡
ሀምዛ ስለደረሰበት አደጋና ስለገጠመዉ ሁኔታ ቀለል አድርጎ ለፎዚ ካስረዳት በኃላ... "አንቺ እንዴት ነሽ?" ብሎ ጠየቃት፡፡ ስለ ደህንነቷ ሲጠይቃት ቤቷ ሰላም እንደሌላት ያዉቋል፡፡ የሀቢብን ባህሪ ጠንቅቆ ስለሚያዉቀዉ ይሄን ለመረዳት አያዳገተዉም፡፡
.... ሀምዛ ቀስበቀስ ወደ ነገሩ እየገባ ሁለቱንም ጥንዶች መከራቸዉ፡፡ 'ትዳርን መተሳሰብ ካልተጨመረበት ህይወታችሁ ሰቆቃ፤ ትዳራችሁ እንደ ህፃን እቃቃ ያደርግባችኃል፡፡ (ሁለቱም ተመስጠዉ ያዳምጡታል፡፡ በተለይ ሀቢብ የጓደኛዉ ምክር ኑዛዜ እስኪመስለዉ ድረስ ልብ ሰጥቶት እየሰማዉ ነበር፡፡) ... ነጋ ጠባ የምትጣሉት ነገር ፍቅራችሁን እያደፈረሰ መቃቃርን ያመጣል፡፡ መናናቅን በስተመጨረሻም የከፋ ደረጃ ያደርሳችኃል፡፡ በተለይ ሀቢብ ዉድ ጓደኛዬ ለትዳርህ ቦታ ስጠዉ፤ ለሚስትህም እንክብካቤ አትንፈጋት፡፡ (ይሄንን ቃል በፎዚ ፊት በመናገሩ ዉስጧን ሀሴት ተሰማት፡፡ ሀምዛ ... ሀቢብን ተቆጥቶና ገስጾ፤ ለፎዚያ ደግሞ ትዕግስት ማደረግ አለብሽ ብሎ ንግግሩን ቋጨ፡፡)..."
..... በመካከላቸዉ ለተወሰነ ደቂቃ ዝምታ ከሰፈነ ቡኃላ ሀምዛ ወደ ፎዚያ ዞረና... "የመኪያ ስልክ ስለማይሰራ ቤት ሂጂና አረጋግተሽ ንገሪያት፡፡ በዚያም ወደ ቤትሽ ሂደሽ አረፍ በይ" አላትና ፎዚ ተነስታ ተሰነባብታ ለመዉጣት ስትሰናዳ ..."ባይሆን ወዱን ባልሽን ተዉበሽ ጠብቂዉ...እ..." ብሎ ሀቢንም ፎዚንም ፈገግ አደረጋቸዉ፡፡
..... ሀቢብ ..ሀምዛ ላይ የነበረዉን ጥርጣሬ አስወግዶ ሁሉንም ሚስጥር ለመንገር ከዉስጡ ጋር ሙግት ያዘ፡፡ በስተመጨረሻም የሀምዛ የዋህነትና ቅን አሳቢነት አሸንፎት ፎዚን ለምን ሊጠላት እንደቻለ? ለምን የቤታቸዉ ሰላም እንደደፈረሰ? ለምን የበፊት ፍቅሩ እንደተወገደና ለፎዚ ያለዉ ክብር እንደቀነሰ ሊነግረዉ ፈለገ፡፡
..... "ሀምዛ..." አለዉ አንገቱን ጎንበስ፤ አይኑን ቀለስ፤ አንደበቱን ለስለስ አድርጎ፡፡ ሀምዛም ሲጎነጭ የነበረዉን ጁስ ትቶ
..... "ወይዬ ሀቢብ..." ብሎ መለሰለት፡፡
..... "ሀምዛ በጣም ይቅርታ" አለዉ፡፡
..... "ለምኑ?"
..... "ጓደኛዬ ... ባልሆነ ነገር ጠርጥሬህ ነበር፡፡ የምትመክረኝን ነገር አልሰማ ብዬ በሌለህበት ባንተ ጉዳይ መጥፎን ሳስብ ነበር፡፡ አሁን ግን በጣም ይቅርታ ተፀፀቻለሁ ሀምዛ..." አለዉና የሀምዛን ይቅርታ ሽቶ ጠየቀዉ፡፡
..... "ኧረ ጓደኛዬ ... እኔና አንተ ስንት ነገር ያሳለፍን ሰዎች በዚች ትንሽ ነገር ይቀየመኛል ብለህ ፈራህ?? አብሽር ሀቢቢ ... ይቅርታም አያስፈልገዉም፡፡ አንተን ደስስስስ የሚልህ ከሆነ ግን... ልባዊ ይቅርታ አድርጌላሃለሁ፡፡" ብሎ የሀቢብን ልብ አስፈነደቃት፡፡ ዉስጡንም ረሃ ሰጣት፡፡ ይበልጥ በሀቢብ ልብ ዉስጥ ተወዳጅና ምርጥ ጓደኛዉ እንዲሆን አደረገ፡፡
..... "በጣም አመሰግናለሁ ጓደኛዬ..."
..... "ምንም አይደል ሀቢቢ... (ጁሱን እንደ መጎንጨት ሊያደርግ እያለ) ... ለመሆኑ ፎዚን እንዲህ የምታደርጋት ለምንድን ነዉ ሀቢቢ?" ብሎ ጠየቀዉ፡፡ ሀቢብም ከዚህ በኃላ ሀምዛን የቤቱ ጠበቃ አድርጎ ስለሳለዉ ምንም ነገር ላይደብቀዉ ለራሱ ቃል ገባ፡፡
..... "ሀምዛ ... እ ብዙ ነዉ ሚስጥሩ አሁን ግን ከአንተ የምደብቀዉ ምንም ነገር የለም" አለዉና ፎዚን የጠላባትንና የራቀባትን ምክንያት ሊነግረዉ ከተቀመጠበት ቦታ እንደ መደላደል አለ....
╔═══❖•🌺🌺•❖═══╗
ይ ቀ ጥ ላ ል
╚═══❖•🌺🌺•❖═══╝
❥............🍃💐💐🍃..............❥
@maraki_lyrics