🌻🌻ክፍል አስራ ሶስት🌻🌻
🌿🌿"ጤዛዉ ፍቅሬ"🌿🌿
✍✍( ሰሊና )✍✍
.... አንድ ሀሳብ በአንድ ግለሰብ ዉስጥ ዉሎ ካደረ ለሰዉዬዉ ጭንቀትን እንጂ ሌላ ምንንም አያተርፍም። ይሄን ደግሞ ሀቢብ በራሱ ላይ ያረጋገጠዉ ነገር ነዉ። ጉድለት አለብሽ ፤ ሙሉ አልነበርሽም 'ለምን' ተብላ የምትጠየቀዉ ፎዚያ ሆና ሳለች ከእሷ በላይ ግን እሱ ተጨንቋል። 'የትኛዉ አጠያየቅ ትክክል ነዉ?' እያለ በማሰብ ላይ ሳለ በሀሳብ መንጎዱን ያስተዋለችዉ ፎዚያ ...
... "ንገረኛ ሀቢቢ ... '' ስትለዉ ደንገጥ አለና ..'እ' አለ።
... "የፈለግከዉን ጠይቀኝ ሁቢ ... ማወቅ ያለብክን ሁሉ ... እነግረሃለሁ። ካንተ ምንም ምደብቀዉ ነገር የለኝም።" አለችዉ። እሱ እንደሆነ አፉን ይዞታል። ቅንነቷና መልካምነቷ አንደበቱን አሳስሮታል። ፍቅር አሰጣጧ ልቡን ምንም ሳያስቀር እንዲሰጣት አስገድዷታል። ምክንያቱም ፎዚያ ሲበዛ ብልህ ናት። ዛሬ ሲቀርባትና ሲወዳት ብቻ ሳይሆን ያኔም በትድራቸዉ ላይ የጨለማን ጽልመት ሲያጠላበት ፤ እንደ አባቱ ገዳይ ሲጠላትና ሲያመናጭቃት በነበረችበት ጊዜ እንኳን እሱን ከማፍቀር አልቦዘነችም ነበር። ሲወጣም ሆነ ሲገባ እንክብካቤ በማብዛት ፤ ያንን ክፉ ፊት ተቋቁማ ፤ በክፉ ንግግሩ ዉስጧ እየደማ በመቻልና በመታገስ ትዳሯን በቋፍም ቢሆን አቆይታለች።
በተለይ የአንዱ ቀን ስድቡ ልቧን ላይሽር የሰበረበት እለት የሚረሳ አልነበረም። "ርካሽ" ሲላት ስቅስቅ ብላ ያለቀሰችበት። በዉሃ ታጥቦ እንደተጠመዘዘ ጨርቅ የተንተራሰችዉ ትራስ ልብስ በእንባዋ ሲርስ የነበረችበት። ... አሁን ግን... ያንን ሁሉ ወደ ጎን ትታ ባሏ የሚሰጣትን ፍቅር መኮምኮምና ዉስጡን የሚያስጨንቀዉን ፤ ማወቅ የሚፈልገዉን እዉነቱን ነግራ ቀሪ ህይወቷን በደስታ ማሳለፍ ፤ ትዳሯን ሙሀባ ዉስጥ ነክራ የኑሮን ጥፍጥና ማጣጣም ፣ የዱንያን ፈተና በድል መወጣት - እዉን ልታደርግ የምትፈልግዉ ህልሟ ነዉ።
.... "ፎዚዬ ..." አላት በድጋሜ። ስሟን እያቋላመጠ ፤ አስሬ እያቆለጳጰሰ ከመጥራት ዉጭ ደፍሮ የሚጠይቃት ሀሞቱ ፈሰሰበት።
.... "ወይዬ ዉዴ... አታስጨንቀኛ! ,, የፈለከዉን ጠይቀኝ እኔ ምንም ቅር አይለኝም።" እያለች እንደ ህጻን ልጅ ታደፋፈረዉ ያዘች። ዉስጡ ታምቆ የቆየዉን የሀሳብ ክምር በሞቃት ትንፋሹ 'ኡፍፍፍ ...' ብሎ ካወጣ በኃላ ...
.... "ፎዚዬ መጀመሪያ ያገባሁሽ ሰሞን ላንቺ ያለኝ ፍቅር ወደር የማይገኝለትና በቀላሉ የማይተመን ነበር። እመኒኝ ማሬ...! አሁንም ያ ስሜት ዉስጤ ላይ አለ...." አይን አይኑን እያየች ጆሯዋንም ልቧንም ከፍታ ከማዳመጥ ዉጭ የሚጠይቃትንና ማወቅ ያለበት ነገር ምን እንደሆነ በዉል አላወቀችዉም። ... ንግግሩን ቀጥሏል....
"ሀቢብቲ... በጣም ነዉ የምወድሽ ፤ ከልቤም አፈቅርሻለሁ። ነገር ግን ... አንድ ዉስጤን የሚከነክነኝ ነገር አለ። የማስበዉ ሀሳብ ፤ ስላንቺ የምገምተዉ ... እንደ ሰደድ እሳት ዉስጥ ዉስጤን እየፈጀ ከሚጨርሰኝ አዉጥቼዉ በግልጽ ልጠይቅሽ እፈልጋለሁ።..." ሲናገር እዉነትም የሆነ ዉስጡን የሚረብሸዉ ነገር እንዳለ ያስታዉቅበታል። ለሷ ፍቅር እንዳይሰጣትና እንዲጠላት ያደረገዉ አሁን የሚነግራት ነገር እንደሆነ አላጣችዉም። ይበልጥ ለማወቅ ጓጓች። ዉስጥን በሚያራራ ሁኔታ ድምጿን ቀነስ አድርጋ በለሆሳስ ...
"ምንድን ነዉ እሱ የኔ ዉድ? ምንድን ነዉ ዉስጥህን የሚከነክንህ?..." አለችዉ።
... "ፎዚቲ አንቺ ከ'ኔ በብዙ ነገር ትሻያለሽ። በዚህም ላንቺ የነበረኝ ቦታ እጅግ የገነነ ነበር። በመኃል ግን ስሰጥሽ የነበረዉን ፍቅር ትቼ ፤ ሚስቴ በመሆንሽም ሁሉ ስማረር ነበር። ይሄ ሁሉ የሆነዉ ግን ባንድ ምክንያት ነዉ።..." አሁን ላይ ከሀተታዉ ይበልጥ መስማት የፈለገችዉ 'ሊጠላባት የቻለዉን ምክንያት ስለነበር..."እኮ ምንድን ነዉ ምክንያትህ?" ብላ በንግግሩ መሃል ገባች። ከዚህ በኃላ ወሬ መቀየርም አይችልም። ዳር ላይ ስለደረሰ ሊጠይቃት የሚፈልገዉን በግልጽ ሊጠይቃት ወሰነ። እንደምንም ከራሱ ጋር ታገለና "ክብረ..." ብሎ ቃሉን ሳይጨርሰዉ ስልኩ ጠራ ..."ዝ... ዝ... ዝ..." ንግግሩን አቋረጠና የደዋዩን ማንነት ሲያይ በስልኩ ላይ 'Hamza' ብሎ የመዘገበዉ ስልክ ቁጥር የጓደኛዉ ሀምዛ ነበር። ፎዚያ ዉስጧን የቁጣ ክርቢት ንዴቷን ጫረዉ። ቅስሟ የተሰበረ ያክል አንገቷን ወደ ታች ደፋችና በእጇ መዳፍ አገጯን ደገፍ አደረገች።
... "ኦህ ፎዚ... ለነሀምዛ ቆየሁባቸዉ!" ብሎ ሊያነጋግር የሚያስችለዉን ቁልፍ ተጭኖ .."ሄሎ" አለ። ፎዚን በተቀመጠችበት ትቷት ስልኩን እያነጋገረ ቁም ሳጥኑ ወዳለበት ክፍል ገባ።
.
... 'ምን ሊጠይቀኝ ነበር?' ብላ ሀቢብ ገና ከቤት ሳይወጣ ጭንቀቷን ጀመረችዉ። 'እስከ'ዛሬ ትዳሬን የበጠበጥኩት እኔዉ 'ራሴ ነኝ ማለት ነዉ?' እያለች ያሳለፋቸዉና የተጓዘችበት ከሰላም የራቀችበትን መንገድ እያስታወሰች ራሷን ትረግም ገባች። 'ቆይ ግን ምክንያቱ ምን ነበር? ክብረ ብሎ የጀመረዉ ምን ሊል ነበር??" 'የምን ክብር ነዉ?' ... በዚህ መሃል ሀቢብ ልብሱን ልብሶ ከዉስጥ ብቅ አለ። ፎዚም ተነሳችና ወደ'ሱ ተጠጋች።
... "ሀቢቢ ..." አለችዉ። አሁን ፈርታለች። ሀቢብ ደግሞ ግማሽ ያክሉን የሀሳብ ቁልል ወደ'ሷ ንዶ ስላጋባባት ትንሽ ረፍት የተሰማዉ ይመስላል። ሀሳቡን ሙሉ ለሙሉ ባይገልጽላትም ስለጀመረዉ ከሀምዛ ዘንድ ሲመለስ መጨረስ እንደሚችልና ተነጋግረዉ ችግራቸዉን እንደሚፈቱት አምኗል።
... "ወይዬ የኔ ቆንጆ ..." ብሎ ፀጉሯን ባንድ እጁ እንደመዳበስ አደረጋት። እሷም የሸሚዙን ኮሌታ እንደማስተካከል እያደረገች አይኖቿን አይኖቹ ላይ አንከባለለቻቸዉ።
╔═══❖•💕💕•❖═══╗
ይቀጥላል...
╚═══❖•💕💕•❖═══╝
❥............🍃👑👑🍃..............❥
@maraki_lyrics