የኢየሱስ ክርስቶስ በመፀሀፍት ሁሉ
ይህ ክርስቶስ ኢየሱስን በመጽሐፍት ሁሉ ማወቅ በሚለው ርዕስ ሁለተኛው የትምህርት ክፍል ነው።በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ለማተኮራችን ራሱ ክርስቶስ ኢየሱስ እና ቅዱሳት መጽሐፍት ሀሉ ምሳሌዎቻችን እንደሆነ የተገለጠበት ትምህርት ነው።
"የመጽሐፍቱ ሁለ ዋና የህይወታችንም የአገልግሎታችንም ዋና እናድርገው"
በህግጋት የተደነገገለትን፣በትረካዎች የተተረከለትን፣በቅኔዎች የተቀኙለትን፣በነብያት የተተነበየለትን፣በወንጌላት የታወጀውን፣በሐርያት በሰማዕትነት የተመሰከረለትን፣በመልዕክታት የተላኩለትን እና በራዕይ ዳግመኛ መምጣቱን የተበሰረለትን ኢየሱስን ዛሬም ለማወቅ ለመግለጥ ለማላቅ ረሃብን መነሳሳትን የሚፈጥር ትምህርት ነውና በተቻላችሁ መጠን በትጋት እንድትሰሙት እናበረታታለን።
በአካል ዓለምገና ቤቴል ቃለሕይወት ይቀርባል በአካል መገኘት ለማትችሉ በማርከን ዜማ እነሆ ተብላችኋል።
@MARKENGETA