"ኪዳናችንን እናድስ" በሚሊኒየም አደራሽ!
በመጋቢት 6 በሚሊኒየም አዳራሽ ሊደረግ የታቀደው የዘማሪት ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) የአምልኮ ፕሮግራም ዛሬ በአዘጋጆቹ በሐርመኒ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰቷል። አዘጋጅ የሆነችው የክርስቶስ ተልዕኮ ቤተክርስቲያን መጋቢ የሆኑት ዶክተር ተስፋሁን፣ እንዲሁም ከአርት ሚኒስትሪ ፓስተር (አርቲስት) ደበሽ ተመስገን፣ የፕሮግራሙን ኢቨንት ከሚሰራው ከኤልቬዜት ኤቨንት እህት ሩት ሐይሉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
መጋቢት 6 በሚሊኒየም አዳራሽ በሚደረግ "ቃልኪዳናችንን እናድስ" የተሰኘው ይህ ፕሮግራም፣ ልዩ የአምልኮ የዝማሬ ጊዜ የሚኖር ሲሆን በዚህ መርሃ ግብር ላይ ዘማሪት ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ)፣ ዘማሪት ቤተልሔም ወልዴ፣ ዘማሪት አዜብ ሐይሉ ያገለግሉናል።
በዕለቱ የዘማሪት ቃልኪዳን ጥላሁን (ሊሊ) የቃልኪዳን ጥላሁን የህይወት ታሪክን የያዘ 'የቃልኪዳን ፍቅር' የተሰኘ መጽሐፍ ተመርቆ ለህዝቡ እንዲሰራጭ አዘጋጆቹ አሳውቀዋል። በዚህ ፕሮግራም ላይ ሁላችሁም እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።
ክርስቲያናዊ መረጃ በፍጥነትመረጃም ካላችሁ በinbox ማለትም
@Gift29 ላኩልን እናሳውቃለን❤️
@Markengeta