ዘማሪ ዘዋዝ ተገኝ ከአማኝ ህብረት ተለየ!
በተለያዩ ድንቅ ዘማሬዎቹ የምናውቀው እና የምንወደው ወንድማችን ዘማሪ ዘዋዝ ተገኝ ዛሬ በልጅነት ወደ ሚያገለግልበት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መመለሱን ኦርቶዶክሳዊ በሆነ ሾው ላይ በእንባ ተናግሮዋል።
"ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር አብ ልጅ የድንግል ማርያም ልጅ ከሶስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ የሆነውን እሱን በወንጌሉ ላይ የተፃፈው ደግሞ ጉልህ ሆኖ በቅድስት ቤተክርስቲያናችን አግኝቼዋለሁ በልቼዋለሁ ጠጥቼዋለሁ እድሜ ዘመኔንም እሱን እያመለኩኝ እርሱ የሰጠኝን ስጦታዎችን እናቴን እመቤቴን ቅድስት ድንግል ማርያምን ቅዱሳኑን መለአክቱን ፃድቃኑን ስለሱ ዋጋ የከፈሉትን ሰመአቱን በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እያከበርኩኝ ........አገልግሎቴን እቀጥላለሀ!" ሲል ተናግሮዋል።
እግዚአብሔር እንደገና ይገለጥልህ!
"በህይወት መዝገብ ፃፍከኝ
በፅድቅህ ፃድቅ ሆንኩኝ
ሰርቼ ሳይሆን በስራ
ዳንኩኝ በፀጋ" ይህ ዝማሬ ከአማኙ ልብ አይጠፋም!
በማርከን ዘጋቢ Gift የተተነተነ
ክርስቲያናዊ መረጃ በፍጥነት
መረጃም ካላችሁ በinbox ማለትም @Gift29 ላኩልን እናሳውቃለን❤️
@Markengeta፡