ወንጌላዊ ተካ
ሙስሊም ነበሩ ከዕለታት በአንዱ ቀን በጠባቧ ግቢያቸው ተከራይተው የሚኖሩ የወንጌል አማኞች፥ ሠርግን ይሠርጋሉ።በሠርጉ ላይም የወንጌል አማኞች ጥቅጥቅ ብሎ ተገኝተው ነበር።አማኞች፥እርስ በርስ በምያሳዩት ፍቅርና መከባበር ልቡ እጅጉን ተሸነፈ።በዚህም ማንም የምሥራቹን ወንጌል ሳይሰብክለት አምላካቸውን ለማምለክ ወሰነ።ኢየሱስንም እንደግል አዳኙ አድርጎ ተቀበለ።ሚስቱ ግን ለሁለት ዓመታት ያህል እንብተኝነቷን ካሳየች በኋላ በስተመጨረሻም በጌታ ፍቅር ተሸነፈች።ወንጌላዊ ተካ ሞሐመድ ይባላል። የዘማሪ ይድነቃቸው ተካ ወላጅ አባት ነው። ቤተሰቦቹን ለማስተዳደር ትንንሽ ችርቻሮ ላይ ተሰማርቶ ይሰራ ነበር።አንድ ቀን ለወንጌላዊነት ጥሪ እንዳለበት አምኖ ባለበት አጥቢያ ቤ/ያን ሙሉ ጊዜ ወንጌላዊ እንድሆን ቤ/ያናቸው ሾመችው።በዚህም የችርቻሮን ሥራ በማቆሙ ቤተሰቦቹ እጅግ ክፉኛ ተጎዱ።ምክንያቱም ቤተክርስቲያናቸው መክፈል የሚትችለው በወቅቱ አንድ መቶ ሃምሳ ብር ብቻ ስለነበር።ስለዚህ ቤተሰቡን በገቢ የመደገፍ ኃላፊነት በይድነቃቸው እና ወንድሙ ላይ ወደቀ።መርካቶ ገበያ ላይ ፌስታል እያዞሩ ይሸጡ ነበር።ያገኙትን ገንዘብ ለእናታቸው ያመጡ ነበር ይድነቃቸው ከወንድሙ ጋር በመሆን።ለመብላት እጅጉን ተቸግሮ የሆቴል ፍርፋሪ ለመብላት ይመኙ እንደነበር ያስታውሳል።ትምህርት ቤት ለመሄድ ከአንድ ሰዓት በላይ በእግር ይጓዝ ነበር ይህ ሁሉ ለወንጌል የተከፈለ መሥዋዕትነት ነው።በዚህ መሐል ወንጌላዊ ተካ ሞሐመድ ለልጆቹ አንድ ነገር ደጋግሞ ይነግር ነበር።"ብርና ወርቅ የለኝም ነገር ግን ያለኝን ይህንን መጽሐፍ ቅዱስ እሰጣችኋለሁ" ይላቸው እንደነበር ያስታውሳል።
ወንጌላዊ ተካ ሞሐመድዘማሪ ይድነቃቸውን ጨምሮ ስድስት ልጆች ያሉት ሲሆን በተለያዩ አለም ተሰማርተው ትልቅ አንቱታን አትርፈዋሉ።
@Gift29
@Markengeta