ዮሐንስ 5:1-6
ቤተ ሳይዳ የተባለች አንዲት መጥመቂያ አለችና በእሷ ዙሪያ ብዙ በሽተኞች የመለአኩን መምጣት ሚጠብቁ እንዲሁም ሲመጣ ደግሞ በፍጥነት ወደሷ ገብተው ፈውሳቸውን የሚያገኙ ብዙ ነበሩ። መርሁ ዛሬ ይሁን የዛሬ ሰላሳ አመት አዛ መጥመቂያ አካባቢ መምጣትህ ሳይሆን ዋናው ጉዳይ መላእኩ ሲያናውጠው ዘለህ መግባትህ ነው መዳንን ምታገኘው። ኢየሱስ በእዚች መጥመቂያ አካባቢ ሲዘዋወር ለ38 አመት የተኛ በሽተኛ ተመለከተ። የዚህ ሰውዬ ጥበቃው ይገርመኛል በመጀመሪያ ሰው የለውም በራሱም ዘሎ መግባት አይችልም ሲቀጥል Normal ሰው ተስፋውን አብዝቶ ሚጠብቀው አንድ ወይም ሁለቴ ለሞከረው ነገር ነው 38 አመታትን እዛ ቦታ ላይ ም....ን.....ም በሌለበት በተስፋ ሲጠብቅ ነበር። ደስ ሚለው ነገር ኢየሱስም ለብዙ አመት እንደጠበቀው አይቶ ሄዶም ፈወሰው። የኔ ወዳጅ ምንም ያህል ጊዜ ይሂድ ኢየሱስን ብቻ ጠብቅ ነገሮች እንደ ማይመጣና እንዳበቃ ለማሳየት ቢሞክርም እሱን ጠብቅ።
የዛሬ መልእክት ነው መልካም አዳር!
Brother Gift! @GIFT29
@Markengeta