ልጆች ልክ እንደወላጅ (Parentification)
ወላጆች በጽኑ ሲታመሙ፣ በሞት ሲለዩ፣ በሱስ፣ በአለመግባባትና መሰል ጉዳዮች ቤተሰቡን ማስተዳደር ሲሳናቸው እና በመሳሰሉ ምክንያቶች ልጆች የወላጅን ሚና ተክተው ቤተሰብን እንዲያስተዳድሩ ሊገደዱ ይችላሉ።
ይህ ጉዳይ በሃገራችን በስፋት ይስተዋላል። በተለይም የመጀመርያ ልጆች ታናናሾቻቸውን ልክ እንደ ወላጅ ሆነው እንዲያሳድጉ ሃላፊነት ሲወስዱ ማየት የተለመደ ነገር ነው። ታናናሾቻቸውን ለማሳደግ ራሳቸውን መስዋዕት ያደረጉ ብዙ አሉ።
እነዚህን ሃላፊነቶች በሁለት ከፍለን ማየት እንችላለን:-
1. Instrumental/ቁሳዊ/ parentification- ይህ ልጆች የቤተሰብን ቁሳዊ/አካላዊ ፍላጎት እንዲያሟሉ ሃላፊነት ሲጣልባቸው ነው። ለቤተሰቡ ምግብን ማቅረብ፣ ስራ ሰርቶ ገቢ ማስገኘት፣ የቤተሰብ ቢዝነሶችን ማሳለጥ እና የመሳሰሉ ጉዳዮችን እንዲከውኑ ይጠበቅባቸዋል።
2. Emotional Parentification- ይህ ደግሞ ለቤተሰቡ ስነልቦናዊና እና የስሜት ድጋፍን የመስጠት ሃላፊነት የተጣለባቸውን ይመለከታል።
ስነልቦናዊና ማህበራዊ ዳራው ምን ይመስላል?
- ይህን ሃላፊነት በተለይም ከአፍላነታቸው ጀምረው የተሸከሙት እንደሆነ እንደ የእድሜያቸው የሚጠበቀውን ስነልቦናዊና ማህበራዊ የእድገት ደረጃዎች (psychosocial development) እንዳያሳኩ እንቅፋት ሊሆንባቸውና ለተለያዩ ስነልቦናዊና ማህበራዊ ቀውሶች ሊያጋልጣቸው ይችላል።
- በእድሜያቸው አለመብሰል ምክንያት አስቸጋሪ አጋጣሚዎችን የመቋቋምያ መንገዶቻቸው (coping) በደምብ የዳበሩ አለመሆኑ ለችግር ተጋላጭነታቸውን ይጨምረዋል። ነገሮችን በጥልቀት እንድንመዝን እና እንድናገናዝብ የሚያደረገው የአንጎላችን ክፍል (Prefrontal cortex) ስራውን በደምብ መከወን የሚጀምረው በሃያዎቹ እድሜያችን ገደማ እንደሆነ ይታመናል። አንዳንድ ቀድመው የሚበስሉ (early matures) እንዳሉ ሆነው።
- በትምህርት አለመግፋት፣ በኢኮኖሚ አለመደራጀት፣ ለጭንቀት፣ ለድብርት ህመም፣ ለአጽ ተጠቃሚነት፣ የስብዕና መዛነፍና ለመሳሰሉ ማህበራዊና ስነልቦናዊ ችግሮች የሚጋለጡት ብዙ ናቸው።
- ደግሞም በሌላ አንጻር ቤተሰብ በመምራት ሂደት የሚኖራቸው ተሞክሮ መልካም ከሆነ በራስ መተማመናቸው የዳበረ እና ችግሮችን የመቋቋም እና የመፍታት ችሎታቸው የተሻለ ሊሆን ይችላል። Internal locus of control ይኖራቸዋል።
ዶ/ር እስጢፋኖስ እንዳላማው (የአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስት)
@melkam_enaseb