.
ሄ ዋ ን 🌺
❣ :¨""""""""""""""¨:❣
" ምዕራፍ ሁለት🌺 "
♥️ ክፍል 16
◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
✍ Written by Estifanos tekka
ድንገት ፍላሹ ትዝ አለኝ ምን አልባት የዚህ ጥያቄዬ መልስ እዛ ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክ በኔ ቅዠትና በየደቂቃው ከንቅልፌ መንቃት ምክንያት እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አድሮ አሁን ሸለብ አድርጎታል ቀስ ብዬ ካጠገቡ ተነሳሁ ማክ እቤት ውስጥ ለስራ የሚጠቀመው ክፍል ገብቼ መፈለግ ጀመርኩ ምንም አልቀረኝም ላገኘው አልቻልኩም ድንገት ከኀላዬ ሄዊዬ ምን ጠፍቶብሽ ነው የሚል ድምጽ ተሰማኝ ማክ ነበር ማክ እባክህ ምን እንደምፈልግ ታውቃለህ እናም ከደበቅክበት አውጥተህ ስጠኝ አልኩት
እጄን ይዞኝ ከክፍሉ እየወጣ የኔ ቆንጆ አሁን ማሰብ ያለብን አንድና አንድ ነገር ብቻ ነው ስላንቺ ጤና ብቻ ለኔ ካላዘንሽልኝ ለምን ለልጃችን አታስቢም በኀላ ጭንቀታም ልጅ ልትወልጂ ነው አለኝ እየቀለደ ማክ ስለልጃችን ብቻ አደለም ስላንተም አስባለሁ ግን እስከመቼ ነው በዚህ አይነት ሁኔታ የምንቀጥለው እኔ በጭንቀት ልሞት ነው ሁሉንም ያባቴን ሚስጥር አውቄ ለህግ ካላቀረብኩት ሰላም አይኖረኝም እባክህ ማስረጃዎቹን ስጠኝ አልኩት እያለቀስኩ የኔ ቆንጆ ያባቴም ፍላጎት ይሄ ነው አንቺ አባትሽን አሳልፈሽ እንድትሰጪ ግን የሱን ፍላጎት እንድታሟይ አልፈቅድለትም አባትሽ ባደረገው ነገር መቀጣት ካለበት ወንጀሉን ሲፈፅም የተተባበሩትም ሰዎች አብረው መቀጣት አለባቸው ይሄን ደሞ የሚያደርገው ሰው አንቺ ሳትሆኚ እኔ ነኝ አባትሽም ሆነ ሌላውን ሰው ለቅጣት ለማቅረብ እኔ አለሁኝ ቃል እገባልሻለሁ ግን ምን አልባት ያባትሽ ጥፋት ብቻ ላይሆን ስለሚችል እስከማጣራ አንቺ ተረጋጊ እስከዛ እራስሽንና ልጃችንን ብቻ ለመንከባከብ ቃል ግቢልኝ አለኝ ማክ እንዴት ነው አባቴ ጥፋተኛ ላይሆን የሚችለው እኔ ባይኔ እኮ ነው ፎቶውን ያየሁት እንዴት ይሆናል አልኩት አሁንም እያለቀስኩ ባይንሽ አይተሻል እንዴትስ እንደተፈጠረ የምታውቂው ነገር አለ አለኝ ማክ እንባዬን እየጠረገልኝ እኮ የሁሉም ነገር መፍቻ እኮ ምን አልባት ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክዬ ፕሊስ ስጠኝና ልየው ከዛ በኋላ ባልከኝ ሁሉ እስማማለሁ አልኩት በምንም መልኩ ማክ ፋይሉን ሊሰጠኝ አልፈቀደም እኔም ከቀን ወደቀን እየተሻለኝ ቢመጣም ያባቴ ስራ ከፊቴ መጥፋት አልቻለም እርግዝናውም እየከበደኝ ሲመጣ ማክ የገባልኝን ቃል እስኪፈፅም ከመጠበቅ ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረኝም ቀናቶች ወራቶችን ወልደው የምወልድበት ጊዜ ደረሰና የምታምር ቆንጅዬ ሴት ልጅ በሰላም ተገላገልኩ ስሟን ስጦታ አልኳት ማክና ስጦታ ለኔ የህይወት ገጸበረከቶቼ ናቸው ውሎዬ አዳሬ ሁሉ ነገሬ ከልጄ ጋር ሆነ ያም ሆኖ ያባቴ ነገር አሁንም ውስጤ አለ ማክ በኔ ደስተኛነት በጣም ደስተኛ ሆኗል በጣም የሚያስቀናና ደስተኛ ቤተሰብ አለን አሁን የማክ እህት ዎንድሞችም ሊያዩኝ የደስታችን ተካፋይ ሊሆኑ መጥተዋል ሁሉም በኛ ደስተኞች ናቸው ከማክ ካንዷ እህቱ በስተቀር በቃ ደስ የሚል ቤተሰባዊ ጊዜን እያሳለፍን ነው ብቻዬን አድጌ በሰው መከበቤ እንደአዲስ የተወለድኩ አይነት ስሜት ፈጥሮብኛል ስጦታ ሁለት ወር ሞልቷታል ሙሉ ጊዜዬን ለማክና ለስጦታ መስጠት ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ አንድ ቀን አባቴ እቤት ድረስ አንኳክቶ መጣ ማክ አጋጣሚ ስራ ነበር እኔም ስጦታን እያጫወትኩ ውጪ ነበርኩ ዘበኛው ጠርቶኝ ስወጣ ገና ሳየው አንቀጠቀጠኝ ፈራሁኝም እሱ ግን ፍፁም ተረጋግቶና አሳዛኝ ሆኖ ነበር እባክሽ ልጄ አንድ እድል ስጪኝ ላናግርሽ ነው የመጣሁት እባክሽ እያለ ይማጸነኝ ጀመር ድንገት ያ ፎቶ ፊቴ ድቅን አለብኝ ማናገር እንደማልችል ነግሬው ወደውስጥ እየሮጥኩ ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ማክ ሲመጣ የሆነውን ስነግረው ባባቴ እቤት ድረስ ደፍሮ መምጣት በጣም ተናደደ ማክን እንደዛ ሲሆን አይቼው አላውቅም.... ስጦታን ለሞግዚቷ እንድሰጣትና የሱ የስራ ክፍል እንድከተለው ነገረኝ ማክ በጣም አስተዋይና ታጋሽ ነው የዛሬው ሁኔታው ግን የተለየ ነበር በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ ያለኝን ፈፅሜ ስመጣ....
እንድቀመጥ ወንበር ስቦ አስቀምጦኝ የሚነግረኝን ማንኛውንም ነገር በፀጋ እንድቀበልና ምንም አይነት እርምጃን ከሱ ውጪ እንደማልፈጽም ቃል አስገባኝ......
꧁༺༒༻꧂
✎ ምዕራፍ ሁለት🌺 ክፍል አስራ ሰባት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
━━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
✨#ህይወቴ✨
🥀 @hiwote_love_story 🥀
🥀 @hiwote_love_story 🥀
┄┄┉┉✽»🌺✿🌺»✽┉┉┄┄