ገብርኤል ማለት ወልደ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ይህንም ንጉሠ ፋርስ ከሠለስቱ ደቂቅ ጋራ አራተኛ ሆኖ በእሳት ውስጥ ሲመላለስ አይቶ አራተኛው የአማልክትን መልክ ይመስላል ብሎ የገለጸበት ስም ነው፡፡ በግዕዙ ‹‹ ወገጹ ለራብዓይ ወልደ እግዚአብኤር ይመስል›› እንዲል (ዳን ፫፡፳፭)፡፡ ንጉሡ አራተኛው የአማልክትን መልክ ይመስላል እንጂ ቅዱስ ገብረኤል መሆኑን አልገለጸም፡፡ ይህንን የገለጸው ቅዱስ ያሬድ ነው፤ "ዝኬ ውእቱ ገብርኤል ዘባጢሁ ለእሳት -የሚነደውን እሳት ያጠፋው ገብርኤል ነው" ድጓ ገጽ ፻፸፡፡
በተጨማሪም ቅዱስ ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር ወዲበ ርእሱኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል፤ ገብርኤል ማለት ወልደ እግዚአብሔር ማለት ነው፤ ጥሬ ትርጉሙ ወልደ እግዚአብሔር ይባላል አለ እንጂ በቁሙ መላእኩ የእግዚአብሐር ልጅ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ በተጨማሪም ቅዱስ ገብርኤል "መጋቤ ሐዲስ፣ አብሣሪው መላእክ" ይባላል፡፡ የተባለብትም ምክንያት ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም "ትፀንሲ ወትወልዲ ወልደ" ብሎ በስሙ ትርጓሜ ምሥጢረ ሥጋዌን በመናገሩ መጻሕፍት "ወልደ እግዚአብሔር" ሲሉ ይጠሩታል፡፡ መተርጉማን ሊቃውንትም "ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ ፣እግዚእ ወገብር" ብለው ተናግረዋል፡፡ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ" እንዲል (ሉቃስ ፩፡፲፱)፡፡ በተራዳኢነቱና በአማላጅነቱ በምእመናን ዘንድ ፈጣን ነው፡፡ ያዘኑትን ለማፅናናት የምስራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን የሚላክና ፈጥኖ የሚደርስ መላእክ ነው፡፡
በጣዖት ፍቅር እጅግ ያለመጠን ልቡ ተቃጥሎ የነበረው የባቢሎን መሪ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ወርዱ ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቅ ምስል አሰርቶ መኳንንቱን ሰብስቦ ሕዝቡ በሙሉ ለጣዖቱ እንዲሰግድ አዋጅ አወጀ፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ነበር፡፡ አስመሳዮች ለጣዖት ሰገዱ፡፡ እውነተኛ አማኞች ግን በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት ንጉስ ሆይ "አምላካችንን ክደን አንተ ላቆምከው ጣዖት አንሰግድም" አሉት ሦስቱ ወጣቶች፡፡ ንጉሱም አገልጋዮቹን ጠርቶ እሳቱ ሰባት እጥፍ እንዲነድ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ እሳቱም ሰባት እጥፍ ነደደ፡፡ ወዲያውኑ የንጉሱ አገልጋዮች አናንያ፣ አዛርያን እና ሚሳኤልን ወደ እቶነ እሳቱ ወረወሯቸው፡፡ ከእሳቱ ኃይል የተነሣ የንጉሡ አገልጋዮቹም በእሳቱ እየተጠለፉ ነደዱ፡፡ ንጉሱም በዚህ ወቅት ‹‹እነሆ እኔ በእሳቱ መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ እሳቱ ምንም አላቃጠላቸውም አራተኛውም የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡፡›› አለ፡፡
ንጉስ ናብከደነፆር በግልፅ ተመልክቶ እንደመሰከረው የነደደውን እሳት በማብረድ ለሠለስቱ ደቂቅ ቤዛ የሆናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ከዚህ በላይ እንደተገለፀው ሊቀመላእክት ቅዱስ ገብርኤል ስለ ሃይማኖታቸው መከራ የተቀበሉትን ወጣቶች የነደደውን እሳት አብርዶ በሃይማኖታቸው እንደአፀናቸው በግልጽ በነብዩ ዳንኤል ተገልጿል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት እኮ ጥንት የነበረ ብቻ ሳይሆን እስከ አለንበት ዘመን ደርሶ የመልአኩን አማላጅነት በዓይን የተመለከትነው ተጨባጭ ድርጊት ነው፡፡ የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስ ገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን መልአኩን ልናከብረውና ልናመሰግነው ይገባል፡፡ አምላከ ቅዱሳን በረከቱን ያሳድርብን
@menefesawitereka
@menefesawitereka
@menefesawitereka
t.me//menefesawitereka