ክፍል ሁለት
ሴቶችን በተለይ መልከኞችን ትዳር አልባ የሚያደርግ ዓይነ ጥላ
/ወንድ አርቅ/
ወዳጆቼ በክፍል አንድ ገርጋሪው ዓይነ ጥላና የዛር አጋንንት ከማኅፀን ጀምሮ በመጠናወት፣ሕይወታችንን እንዴት እንደሚያበላሽ አይተናል፡፡ በዚህ በክፍል ሁለት ደግሞ ዓይነ ጥላ ለሴቶች እህቶታችን የትርዳር ጠንቅ፣ለወንዶች ደግሞ ከትዳር ለመራቅ ምክንያት እንዴት እንደሚሆን እንመለከታለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጥልን፡፡
ማሳሰብያ ፦ ይህን ትምህርት ስታነቡ ውስጣችሁ ሊበሳጭ እና ዓይነ ጥላው ሊያጉረመርም ስለሚችል በትዕግስት አንብቡ፡፡
ተወዳጆች ሆይ ዓይነ ጥላ በባሕሪው ትዳር አይወድም፡፡ ለዚህም ነው ትዳር እንዳንይዝ፣የተለያየ የሕይወት መዘዝ የሚያመጣብን፡፡ ዓይነ ጥላ ልጅ አይወድም ለዛም ነው ልጆችን ከማኅፀን የሚያጨናግፈው፣ከተወለዱ በኃላ ደግሞ ሕይወታቸውን የማበላሸት ሥራ ከልጅነታቸው የሚሠራው፡፡
ብዙ ሴቶች በተለይ መልከኞች ትዳር እንዳይዙ ዓይነ ጥላው ከፍተኛ የማደናቀፍ ሥራ ይሠራል፡፡ መልክና ቁመናቸውን ይዘው ቆመው እንዲቀሩ ያደርጋቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ አንድ መልከኛ ሴትን ከቤተሰቦችዋ፣ከጓደኞችዋ ጀምሮ ‹‹አንቺ ለምን አታገቢም፣ይሄ ውበት እኮ ይረግፋል፣ሁሉም በጊዜው ነው የሚሆነው ይልቁንስ ተጠቀሚበት›› እያሉ ምክር ይሁን የቃል መውገር ይለግሷቸዋል፡፡
እነሱም ግራ እስኪገባቸው ድረስ ለምን እንዳላገቡ፣ወንዶች ለምን ለትዳር እንዳልፈለግዋቸው አያውቁም፡፡ ግን ዓይነ ጥላው በውስጥ እና በውጭ ሆኖ ይገረግርባቸዋል፡፡ የውስጥ ዓይነ ጥላው ውስጣቸው አሸምቆ ተደብቆ ለወንዶች አቃቂር በማውጣት የማጥላላት የመናቅ ሥራን ይሠራል፡፡ በዚህም የሚመጡትን ወንዶች ያባርራል፡፡
ዓይነ ጥላው መልከኛ ስለሆኑ የኩራት፣የትዕቢት፣የበላይነት፣የትፈለግያለሽ ስሜት እያሳደረባቸው ለትዳር የሚመጡትን ወንዶች በራሳቸው እየመዘኑ እንዲጠሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ምርጫቸውን በማብዛት አንዱ ላይ እንዳይረጉ ያደርጋቸዋል፡፡ዓይነ ጥላው ውስጣቸው ሆኖ ለትዳር የመጣውን ወንድ ‹‹አይመጥንሽም፣ይህንን ነው የምታገቢው፣ቤተሰብ ምን ይላል›› እያለ በሚወዳት ወንድ እንድታፍር፣እንድትሳቀቅ ያደርጋል፡፡ ዓይነ ጥላው ተመራጭ እና መራጭ እንድትሆን በኩራት መንፈስ ጠስቆ ይይዛታል፡፡ በመልኳ በቁመናዋ፣በዳሌዋ እንድትመካ እያደረጋት ወንዶችን ወደ ታች እንድታይ ይደረጋታል፡፡
ሴቶች ልብ የማይሉት ዓይነ ጥላው በውበታቸው፣በቁመናቸው፣በደም ግባታቸው እራሳቸውን ከፍ አድርገው እንዲያዩ በማድረግ የትዳር ሕይወታቸውን ከባለ ጠግነት ጋር ያያይዝባቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላ ያለባቸው መልከኛ ሴቶች ወንዶችን በመልካም በሕርያቸው፣በተክለ ሰብዕናቸው፣በውስጥ ውበታቸው፣በቀናነታቸው በታማኝነታቸው ሳይሆን በእውቀታቸው፣በሥልጣናቸው፣በዝናቸው በመመዘን የራሳቸውን ሰው እንዳይመርጡ ያደርጋቸዋል፡፡ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ ‹‹አንቺ ልጅ እባክሽ አግቢ›› ሲላት ዓይነ ጥላው የሐብት መሻት፣የባለ ጠግነት ስሜት እንዲሰማት በማድረግ ‹‹ሀብታም ካልሆነ አላገባም፣ቤት የሌለው፣መኪና የሌለው ባል ምን ይሠራልኛል›› እያሉ በዓይነ ጥላው እየታለሉ ያለ ባል ይቀራሉ፡፡ ሀብታም ባል ቢያገቡም ለባላቸው ፍቅር ከመለገስ ይልቅ በውበታቸው በመኮፈስ ትዳራቸውን ዓይነ ጥላው መረበሽ ይጀምራል፡፡
አብዛኞችን ደግሞ ዓይነ ጥላቸው የወደዱትን ሰው ጥቃቅን የስህተት ምክንያት እየፈለገ ያጨቃጭቃቸዋል፣የወደዱትን ሰው የፍቅር ምቶች ይነሳባቸዋል፡፡ ዓይነ ጥላቸው እጅጉን ከመክፋቱ የተነሳ በምንም ተአምር ለተበደሉበት ነገር ይቅርታ እንዳያደርጉ ልባቸውን ያደነድናል፡፡ በተለይ ጥፋትን በቅርበት ካዩ ይቅርታ ቢጠየቁም አሻፈረኝ በማለት ወደ ሌላ ሰው እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡ በዚህ ሂደት የቀናቸው መልካም ሰው ላይ ይወድቃሉ፣ያልቀናቸው ደግሞ ከወንድ ወንድ ይንከራተታሉ፡፡ ፍቅር እና ጸጋ እግዚአብሔር የሚጠነቀቅለትን ነው የሚፈልገው፡፡ እነሱ መጠንቀቅ ሳይሆን መጨቃጨቅ እንደ ባሕርይ ያጣባቸውና ሕይወታቸውን መና ለማስቀረት ዓይነ ጥላቸው ይታትራል፡፡
የውጭ ዓይነ ጥላው ደግሞ በሚፈልጋት ወንድ ላይ ተቀምጦ እንደ ተራራ አግዝፎ እንዲያያት፣ትበዛብኛለች ብሎ እንዲያስባት ቢያገባት እንኳን ለትዳሩ የፍቅር ስንቅ ሳትሆን ጠንቅ አድርጎ ያሳየዋል፡፡ በዚህም የወደፊቱን ትዳር በመገመት በመፍራት ‹‹እኔ ለእሷ አልሆንም›› በማለት ወንዱን ተስፋ በማስቆረጥ ያርቀዋል፡፡ ከእሷ ጋር መኖር በእሳት ተቃጥሎ እንደ ማረር አድርጎ ያሳስበዋል፡፡ እሷም ላይ እሱም ላይ ያለው ዓይነ ጥላ የመፈላለግ ድንበራቸውን በማፍረስ፣የጀመሩት ፍቅር ገና በጅምሩ በምክንያት በማቃወስ ያራርቃቸዋል፡፡ የሚያሳዝነው ዓይነ ጥላው ለጊዜው ልክ አድርጎ ያስወሰናቸውን ውሳኔ ካለፈ በኃላ፣ነገሮች ከተበላሹ በኃላ፣ሌላ ሕይወት ውስጥ ከገቡ በኃላ በጸጸት አለንጋ ይገርፋቸዋል፡፡ ‹‹ምን ሆኜ ነው? ለምን እንደዛ አደረኩ? ልክ አላደረኩም›› በማለት ባለፈ ነገር እንዲቆጩ ያደርጋቸዋል፡፡ ነገሮች ተመልሰው መስተካከል ወደማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ከገቡ በኃላ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲሰማን ያደርገናል፡፡ መበደላችን የሚታወቀን ካለፈን በኃላ ነው፡፡ ይህ አንዱ የመንፈሱ መሰርይ ጠባይ ነው፡፡ እድላችንን ከማሳጣት በኃላ በጸጸት ማሰቃየት፡፡
ልክ እንደ ሴቶቹ ወንዶቹም የዚህ እኩይ መንፈስ ሰለባ ናቸው፡፡ ወንዶቹን ደግሞ መራጭ፣ተፈላጊ አድርጎ በማስቀመጥ ሴት አውል ያደርጋቸዋል፡፡ ከሚወድዋቸው ሴቶች ጋር ከትዳር በፊት በመዘሞት በሩካቡ ሥጋ ብቻ በመመዘን እየናቅዋቸው ይሸሿቸዋል፡፡ ይህ የዓይነ ጥላ ባሕርይ የተጣባቸው ወንዶች ለትዳር ክብር ስለማይኖራቸው ዓይነ ጥላው ያለ ሚስት ያስቀራቸዋል፡፡
በተለይ ወንዶች አይነ ጥላው ብዙ ሴቶችን በማስመረጥ ብሎም በማማገጥ ያለማምዳቸውና ትዳር የሚለውን ክቡር ሕይወት ዋጋ ቢስና ከንቱ ያደርግባቸዋል፡፡ ትዳር ሲባሉ ያባለጋቸው ዓይነ ጥላ ሕይወቱን ያከብድባቸዋል፡፡ አንዳንድ ውዶች ደግሞ ትዳር የሚባለውን በትዳር ኖረው የተፋቱትን በማሰብ ለማግባት ይፈራሉ፡፡ አጋንንት የእኛን እንዳንኖር የሰው እያሳየ መጥፎ ስዕል ይስልብንና ከትዳር ዓለም እንድንርቅ ያደርገናል፡፡
ዓይነ ጥላ ያለባቸው ሴቶች በመልካቸው ይመካሉ፣ወንድ ይንቃሉ፣ወንድ ይፈራሉ፣ትዳር ይፈራሉ፣ይኮራሉ፣ፊታቸው የተቆጣ ይመስላል፣ከኩስትርና አልፎ የተከሰከሰ ፊት ይኖራቸዋል፣ሲያይዋቸው ተናጋሪና ኃይለኛ ሴት ይመስላሉ ወዘተ እነዚህ ሴቶች እንደዚህ ዓይነት የፊት ገጽታ የሚይዙት ወደው ሳይሆን ዓይነ ጥላው ወንድ እንዲርቃቸው፣ወንድ እንዳይቀርባቸው ለመተናኮል ነው፡፡
ወዳጆቼ ሰው እንዴት በአፈር ይመካል? መልክ ደስ ቢል እንጂ አያስመካም፡፡ የዛሬ መልክ ነገ በእርጅን ውበቱን አጥቶ ተቆራምቶ የሚለወጥ ነገር ነው፡፡ ግን ዓይነ ጥላው ምን ሠርቶ ይኑር? በተሠጠን ነገር ከመጠቀም ይልቅ እንዳንጠቀምበት የማባከን ሥራ ይሠራል፡፡ ጥበበኛው ሰለሞን ‹‹ውበት ሐሰት ነው፣ደም ግባትም ከንቱ ነው›› ይለናል፡፡ ሰለሞን ውበት ሐሰት ነው ያለው የማይቆይ የማይዘልቅ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ደም ግባት ከንቱ ነው ያለው ደም ግባት በህመም፣በአደጋና ከጊዜ በኃላ በሚመጣ ነገር እንዳልነበር ስለሚሆን ነው፡፡ /ምሳ 31÷30/ እንግዲህ ሐሰት እና ከንቱ የሆነ ነገር ይዘን ነው የምንኮፈሰው፣የምንመካው፡፡ እንዲህ የመኮፈስ፣የመኩራት የትዕቢት መንፈስ የሚያሳድርብን ዓይነ ጥላው ነው፡፡
ዓይነ ጥላ ሴቶችን ወንድ እያስመረጣቸው፣እያስናቃቸው፣እያስመካቸው የወጣትነት እድሜቸውን ያባክናል፡፡ የተፈላጊነታቸው ጊዜ በ