ኢትዮጵያ ምን ዓይነት ሀገር ናት?
የቀዳማዊ የሰው ልጅ (የአዳም) መገኛ
የጥንታዊ ታሪክ ባለቤት (ከዞንዶ ንጉሥ እስከ ነብር ሪፐብሊክ)
ለዓለም ሁሉ የጥንታዊ ሥልጣኔ ምንጭ (…ለግብፅ፣ ለሜሶጶጣሚያ፣ ለቻይና፣ ለህንድ፣ ለማያ ለኢንካ፣….)
የጥንታዊ ሃይማኖት መገኛ (ሐገ-ልቦና፣ የኦሪት ሕግጋት መሠረት፣… )
በዓለም ለዘማናት ያልተቋረጠ በትረ-መንግሥት የነበራት (ከኖህ እስከ ቀ/ኃይለ ሥላሴ ድረስ)
ባንድርዋ ንግርት
የቃልኪዳን
በሰማያት የተገኘ– የቃልኪዳን ንግርት ያለው
እነ ሆሜር ‹የቆንጃጅት ሀገር› ብለው በጥንት ታሪክ ያወደሷትና የመሰከሩላት
በ2800 ቅ.ክ. የሞት ቅጣት ያስቀረውን ጨምሮ 18 ፈርኦኖችን ለምድረ ግብፅ ያበረከተች ሀገር
በዓባይ ሥልጣኔ ምንጭነት ምድረ-ግብፅ ድረስ ወርዳ ታሪካዊዎቹን ፒራምዶች እነ ሶፊንክስን በታሪክ ዓምድነት የተከለች ሀገር
በታሪክ መጀመሪያ የተመዘገበች ንግሥት የተገኘችባት (ገና ጥንት በሴት ንግሥታት የተመራች) ሀገር
በዓለም የመጀመሪያው የሥነ-ጽሑፍ ቋንቋ (ግእዝ) የተገኘባትና ይዛ የምትገኝ ሀገር፡-
ሳይንሳዊነቱ ተወዳዳሪያ የሌለው የምድሪቱ ቀዳማይ ፊደል ያላት
በዓለም ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሠራ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ያላት (ምሳሌ የቅ.ላሊበላ ውቅር አቤያተ ክርስቲያናት) ሀገር፣
በዓለም ላይ የሚገኘው የአየር ጠባይ (ከውርጭ እስከ ከፍተኛ ሞቃታማ ሥፍራ) በሙሉ ተካቶ የሚገኝባት ብቸኛ ሀገር፤
የመሬት የመልክዓ ምድር ዓይነቶችም ተካተው የሚገኙባት ሀገር፤
የዓለም ሕዝብ ዘር (ጥቁር፣ ቀይና ነጭ) በማዕከላዊነት ተዋህዶ የሚገኝባት ሀገር
ለሌላው ዓለም ያበረከተቻቸው እፅዋትና ተክሎች (ዝግባ፣ዋንዛ…)፣ እንስሳትና አራዊት (ዋልያ፣የሜዳ አህያ፣…)፣ እንደ ጤፍና ቡና ያሉ የተለዩ የተፈጥሮ ሀብቶች ያሉባትና ያስገኘት
የዴሞክራሲ ሥርዓትን ለግሪኮች ያስተማረች (በአንድ በኩል ቤተ-ሕዝብ፣ ቤተ-ምልክና እና ቤተ-ክህነት ሦስቱ የሥልጣን ክፍፍል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የገዳ ሥርዓት)
የተፈጥሮ ፀረ-ቫይረስ የሆኑትን እነ በርበሬን፣ ሚጥምጣን፣ ከአፅራረ ትላትል (ኮሶ፣ መተሬ፣ እንቆቆ፣..) በምድሯ አፍርታ የምትገኝ ሀገር
ለዘመናዊ መድኃኒት ቅመማ ምንጭ የሆኙ የመድኃኒት እፅዋት ዝርዝርና አጠቃቀማቸው ተጽፎ የተገኘባት ሀገር (ለምሳሌ የጀርመን ሳይንቲስቶች የቀመሟቸው መድኃኒቶች ከኢትዮጵያ የተቀዱ ናቸው)
የዋሕድ አምላክን ፅንሠ-ሐሣብ ለዓለም ያስተዋወቀች ሀገር (ለምሳሌ አብረሃምን የባረከው መልከ-ጸደቅ ኢትዮጵያዊ መሆን፣ ሙሴን ያስተማረው …)
የአምላክን ግማደ-መስቀል፣ ተከርኦተ-ርዕስ በቅርስነት የያዘች፤ ታቦተ ፅዮንን ይዛ በመጠበቅ የኖረች ሀገር
የቅዱሳን አስደናቂ ቃልኪዳን ያላት (ለምሳሌ በአቡነ አሮን ቃልኪዳን ከአናቱ ባዶ ሆኖ ዝናብ የማያፈሰው ቤተ-ክርስቲያንና የዝንጆሮዎች አዝመራ አለመብላት… )
በቅኝ ገዥዎች ያልተንበረከከች ሀገር፣ ነጮች በዘርኝነት ተለክፈው ሊገዟት ሲመጡ በማሸነፍ የጥቁርን አሸናፊነት ያሣየችና ነጮችን ያሳፈረች ሀገር፣ የነፃነት ተምሳሌት የሆነች ሀገር
የተባበሩት መንግሥታትን ለመመሥረት ከአፍሪካ ሀገሮች አንዷና ብቸኛዋ የመጀመሪያ ሀገር፤ የአፍሪካ አንድነት ዋና መሥራችና መቀመጫ ሀገር
በልዩ ልዩ አስደናቂ ጥበባት የሠለጠኑ ልጆች ያሏት ለምሳሌ ሌባ ሻይ፣ መፍትሔ-ሥራይ፣ ምህላ፣…ታምር የሚሠሩት እነ መተት፣….
እንግዶችን በክብር በመቀበል ፍትሕን፣ እንግዳ ተቀባይነትን፣ ሃይማኖትኝነትን፣…መመሪያዋ መሆኑን ያስመሰከረች ሀገር፣
በእስልምና ሃይማኖት ትልቅ ሥፍራ ያላት (ፍትሐዊነቷ በነብዩ ሙሃመድ የተመሰከረላት፣ የመጀመሪያውን አዛን የተነገረው ቢላል፣… በጀሃድ ያለመወረር ቃልኪዳን….)
በሌሎች የዓለም አቤያተ ክርስቲያናት ያልተገኙ እንደ ኩፋሌ፣ ሄኖክ፣ ዮሴፍ ወልደኮሪዮስ፣… የብሉያት ኦርጅናል መጻሕፍት
የሚገኙባት ሀገር
ዘመናዊ ህክምና ያልደረሰባቸውን በሽታዎች የሚ
ፈውስ የፀበል ፀጋን የታደለች ሀገር
የመንፈስ አዛጦን የታደለች፡-
የሥነ-ነፍስን፣
የሀብተ-መንፈስን፣
የሥነ-ምግባር ሰናያት (ትዕግሥት፣ ትህትና፣ አፍቅሮተ-ሰብዕ፣ ንፅሐ-ኅሊና…)፣
የምድሪቱ መልካም ባህላዊ እሴቶች (ጉድፈቻ፣ ማደጎልጅ፣ የነፍስ ልጅ…)፣
የብዙ ዘመናት ድልብ ባለ መልካም ቅርስ (ይሉኝታ፣ ፈሪሃ-እግዚአብሔር፣ ይቅርባይነት፣ አትህቶ-ርዕስ…)….. መመሪዋ ያደረገች ሀገር
የቅዱሳት መጻሕፍት የሃይማኖት መርሆዎች በሕዝቦቿ አእምሮ ተፅፈው በተግባር የሚፈጸሙባት ሀገር፣
የዓለም ታላላቅ ሃይማኖቶች ተከባብረውና ተስማምተው በፍቅር የሚኖሩባሩት (ለምሳሌ እስላምና ክርስቲያኑ በፍቅርና በመተባበር በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩባት፤ ተባብረው ቤተ-አምልኳቸውን የሚሠሩባት፤ አንዱ የሌላውን በዓል አብሮ የሚያከብሩባት) ሃገር ናት፤
በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም ውስጣዊና ውጪያው ፀጋዎች፣ ረድኤቶችና ተዎህቦዎች ያሏት ሀገር፤
…….ኢትዮጵያ!!!
ስለዚህ ዕወቃት፣ ጠብቃት፣ ኩራባት…
አምደ ብርሃን !